Wednesday, December 12, 2012

ይድረስ ለሟች የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ (ጉዳዩ-ስልጣን እንዲያስረክቡ ስለመጠየቅ)

ይድረስ ለሟች የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ (ጉዳዩ-ስልጣን እንዲያስረክቡ ስለመጠየቅ)

Zenawi-Burial

ሲመረን እና ስናመር!!!

ግልጽ ፖስት ይድረስ ለሟች የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ጉዳዩ-ስልጣን እንዲያስረክቡ ስለመጠየቅ

አቶ መለስ – እኔ በፍጹም እርሶን ካረፉበት የመቀስቀስም ሆነ የማስቸገር እቅድ የለኝም ነበር፡፡ ነገር ግን አሁን ሳስበው የቅርብ ወዳጀችዎም እረፍት ስላልሰጦት እኔም ይህንን መልእክት ባስተላልፍ ቅር አይሎትም ብዩ ተነሳሁ፡፡ መቼም ባሉበት ሆነው ከፓርቲዎ እስከ ሚዲያው ድረስ ስምዎ ሲነሳ መዋሉ በስቅታ ሳይገሎት አይቀርም፡፡ አኔና እርሶ ያን ያህል አንተዋወቅም (ሆሆይ በየት በኩል………..)፡፡ እንኳን አሁን ሞተው ቀርቶ ኖረውም ቢሆን እኔን አንዲትዋን ህዝብ የሚሰሙበት ምንም አይነት አመል አልነበሮትም፡፡ እነደው ድንገት ከሞት በኋላ ባለው ህይወት ተቀይረው ከሆነ ለእርሶ ባይሆን ለሰዎችዎ ይጠቅም ይሆናልና እባክዎ ጆሮዎን ያውሱኝ፡፡

እንግዲህ እለእርስዎ የሚወራውን ስመለከተው በቅርቡ “አቶ መለስ ገነት ገብተዋል፡፡ ስማቸወም ለመለስኤል ተብሏል” የሚል የኢቲቪ ዜና ይመጣል ብዩ እየተሳቀቅኩ እገኛለሁ፡፡ በመሆኑም እንዲህ አይነቱ የእርሶንም በህይወትም ሆነ በሞት የሚያስችግር ነገር አሁንም ካሉበት ሆነው አንድ ይሉልኛል ብዩ ይህንን መልእክት ለጠፍኩ፡፡ ለመሆኑ በዜናው በሬዲዮኑ ጋዜጣው እና ሌላው ሁሉ ላይ እርሶ ሲያወሩ እንደሚውሉ አውቀዋል፡፡ እርሶ ያልተናሩበት ቲቪ፣ ያላወሩበት ሬዲዮ፣ የሌሉበት ስብሰባ ከጠፋ ሰነበተ፡፡ በህይወት እያሉ ከመሩት (አንደኛውን እሱ ይሻል ነበር) በላይ ከሞቱ የመሩት እየበለጠ ተቸግረናልና እባክዎ ስልጣኖን ያስረክቡልን፡፡ የተፈጥሮ ግዴታ ከወንበሮ ቢያነሳዎትን ሰልጣኖን ለመረከብ የሚችል ስለጠፋ ከሞት በኋላም አለማረፎ በጣም አሳዝኖኛል፡፡ እርሶን ብቻ ነውና የሚሰሙት “እበካችሁ ራሳችሁን ችላችሁ ምሩ፣ ራሳችሁን ሁኑ፣ ምንም ሆነ ምን የራሳችሁን ታሪክ ለመጻፍ እድሉን ተጠቀሙበት” በሉልን፡፡ እንዴት ነው ነገሩ? ለሰርሶም ስም ቢሆን “በህይወት እያለ 21 አመት ከሞተ በኋላ —–አመት የገዛ መሪ” መባል ለስሞ ጥሩ አይደለም፡፡ (እነዲሁም ቢኖር ስልጣኑን አይለቅም ነበር የሚለው ሃሜት ማጠናከር ይሆንቦታል፡፡)

የቀድሞ ጠ/ሚኒስተር- እንደሚታወቀው እርሶ የሌሉበት የከተማው ቦታ፣ የእርሶ መንፈስ የማይገኝበት የአዲስ አበባ ሰፈር ማግኘት ከባድ እየሆነ ነው፡፡ በየቦታው ፎቶ “በመፈከር” እና “በካድሬ” ተመስለው ከተማዋን ሞልተዋታል፡፡ እስቲ ይሰሞት ከሆነ “ተው ይህ ነገር አኮ ለፓርቲያችን ሰም ጥሩ አይደለም የግለሰብ ገጽታ ግንባታ ነው (በደጉ ዘመን እንደሚባለው)” ብለው ይገስጽዋቸው፡፡”ደግሞም እኔኑ ያስወቅሰኛል ማንንም ለመሪነት ሳያበቃ ሄደ አመራሩ ቀሽም ነበር” ያስብለኛል ይበሏቸው፡፡ ሰዎችዎ እንደሆነ አርሶ በሆነ መንገድ ካላናገሩዋቸው በስተቀር ሌላ ማንንም የሚሰሙ አይመስሉም!! ትዝ ይሎት እንደሆነ ለመልካም አርአያነት በማሰብ ስለኤችአይቪ መመርመር የተለጠፈው የአቶ አርከበ ፖስተር በሰአታት ውስጥ ሲነሳ የፓርቲ አመራሮች ግለሰባዊ ግነትን ለማስወገድ ነው ተብሎ ተወርቶ ነበር፡፡ ታዲያ ምነው? እንዲህ ከተማውን ሲሞሉት ሃይ ባይ ጠፋ?? እባክዎ ሰዎችዎን አንድ በሉዋቸው!!

አቶ መለስ – እርሶ ለፍተው “በሃይል ከሚንዱት” ሲጠብቁት የኖሩት ህገ መንግስት እኮ እርሶ በሄዱ አመት ሳይሞላው ተናደ!! ሶስት ምክትል ጠ/ሚ አነደኖረን ሰምተዋል?? ሌሎች ሃይሎቸም ቢመጡ ህገ መንግስቱን ከዚህ በላይ እንዴት እነደሚንዱት አላውቅም፡፡ እርሶ ከሞቱ በኋላም በጠ/ሚኒስትር ማእረግ እንደሚጠሩስ ሰምተዋል?? “ሃገሪትዋ ስንት ጠ/ሚስተር ነው ያላት?” ሲባል “አንድ የሚተ አንድ ያልሞተ (ከይቅርታ ጋር እኔ በግሌ አለመሞቱን አፌን ሞልቼ ለመናገር የማልደፍረው)” እየተባለ እንደሆነ እያወቁ ዝም ማለቶ አግባብ አይደለም፡፡ ይሄንንም ንገሩልን እና እስቲ “የቀድሞው” የሚል ደፋር ይምጣ!! አቶ መለስ – በደንብ ሳናጣራ ሄደው “ራዕዮን” የማንም መጫወቻ ሲሆን እንዴት ዝም እንዳሉ ገርሞኛል፡፡ ማንም እየተነሳ የእርሶን የታላቁን መሪ ራእይ አሳካለሁ ሲል ዝም መባሉ አልገረሞትም?? እርሶን የሚያህል ሰው የያዘው ራዕይ በተራ ግለሰብ የሚሳካ ነው እንዴ?? እስቲ” ራዕዬ ምን ነበር?”” እነዴት ነው በናንተ አይነት ተራ ሰው የሚሳከው?” ብለው ይጠይቁልኝ፡፡ አንደወሬው ከሆነ እኮ የእርሶ uncommonly wise ራዕይ በማንም የሚሳካ አይመስልም፡፡ በነካ እጆት” የራዕይ ዶክመንት” ብለው ይላኩላቸውና እኛንም ከዚህ ራዕይ ወሬ ይገላግሉን፡፡ (ቢያንስ ራእይ አሳካለሁ ፉከራው ይቀንስልናል) በመጨረሻም ተፈጥሮ የነጠቆትን ስልጣን ፓርቲዎ አልረከብም ስላለ አዝኛለሁ፡፡ “እባካችሁ ስልጣኔን ተረከቡ!በሞት በኋላ እንኳን ልረፍበት” ይበሏቸውና ስልጣኖን ያስረክቡ፡፡ (እንደአያያዛቸው ከሆነ ከእርሶ ውጪ ሌላ ነገር የሚሰሙ አይመስሉምና)

 

No comments:

Post a Comment