Monday, November 26, 2012

መቀሌ ዩኒቨርሲቲ እየታመሰ ይገኛል





መቀሌ ዩኒቨርሲቲ በተወሳሰበ ሙስና ውስጥ በመሆኑና የሙስናው ዋና ተዋናዮች ዶ/ር ክንደያ ገብረህይወት እና ዶ/ር ኣብዱልቃድር ከድር የተባሉ ምክትል ፕረዚደንቶች ይውረዱልኝ ብለው ከሶስት ወር በላይ የጠበቁት ጀርመናዊ ፕረዚደንት ችግር ላይ ናቸው።
የቦርድ ሰብሳቢው ኤርትራዊው ኣቶ ቴድሮስ ሓጎስ (የኢፈርት ቦርድ ሰብሳቢም ናቸው) ጀርመናዊውን በአካል እንዳስፈራሩዋቸው ታውቋል!
ይህ የሆነው ደግሞ ለትምህርት ሚንስትር ሳይቀር ግልባጭ ባደረጉት የአዲስ ምክትል ፕረዚደንቶች ሹመት የተነሳ ነው።
ጀርመናዊው ፕረዚደንት ከሶስት ወር በላይ/August-November/ የጠየቁትን ጥያቄ ሳይመልሱ ተኝተው የከረሙት ኣቶ ቴድሮስ ሓጎስ አውቆ የተኛ ቢቀሰቅሱት ይማታል የሚል አዲስ ዓይነት ቢሂል ፈጥረዋል! ከ300 million ብር በላይ ያባከኑን ሰዎች ገለል እንዲሉ መጠየቃቸው ሊመሰግኑ ሲገባ እንግዳውን German ሰውዬ እንደዚህ እንደውሻ የሚያስፈራሩዋቸው እነ ቴድሮስ ሓጎስ ወደ ማፍያነት መቀየራቸው ጉልህ ማሳያ ነው። ይህን ህዝብ ከመጤፍ እንደማይቆጥሩትና እንዳሻቸው መኖር እንደሚችሉ ግልፅ ማሳያ ነው። ይህ ህዝብ በሚከፍለው ግብርና በደሙ እየነገዱ የሚኖሩት እስከ መቼ ነው? ትግራይ ተማርሯል በማስፈራራት ና በጉልበት ልክ እንደ ትግራይ ህዝብ ደመኛው ለገሰ አስፋው ትግራይን ኤርትራዊው ቴድሮስ ሓጎስ እየገዙዋት ነው። የሚሰርቅን ሰው መጠየቅ ሲገባቸው ኣብሮዋቸው እንደሚሰርቅ በግልፅ በሚያሳይ መልኩ መከላከላቸው ይህ ስርዓት ምን ያህል እንደዘቀጠ፣ ወድቀቱም እንደቀረበ ያሳያል።

No comments:

Post a Comment