Tuesday, November 6, 2012

ማን ጸሎት ያሳርግ


(ለምለም ጸጋው)



“በቃሊቲ ማሰሪያ ቤት እነርሱ “ማረሚያ ቤት” ይሉታል። በርካታ ወገኖቻችን እንደሚገኙ
ይታወቃል። በቅርቡ ደግሞ የሙስሊም ኢትዮጵያውያን መፍትሄ አፈላላጊዎች ወደ ቃሊቲ
ተዛውረዋል። ይህ ፎቶ ህብረተሰቡ ከታሳሪዎቹ ጎን መሆኑን ያሳያል። “አያሳይም” የሚል ካለ
በደንብ ደግሞ ይመልከተው!  ፎቶውን ብቻ ሳይሆን የታሰሩበትንም ምክንያት በደንብ
ብንመለከት ደግሞ ሁላችንም ከነዚህ ወገኖች ጎን መቆማችን አይቀሬ ነው!”November 
5th, 2012”  (http://www.ethiopianreview.net/index/?p=47899)

ማን  ጸሎት ያሳርግ 

ወይ ነውር አይገዛው
አምልኮት ዓልነካው፤
የእትዮጵያን ሰው ሁሉ
በቃሊቲ አጎረው።
ይድነቃችሁ ብሎ
በየሱስ ስም ማለ፤የመለስን ወንጌል
እንደ ክታብ እርጎ
በአንገቱ ሰቀለ።
ለሁሉም ለመሆን
አዲሱ ምንስቴር በቃሊቲ ሳይቀር፤
አርብ ሰኞ ሳይል
አለ ዓላህ አክብር።
ምነው የኔ ወዳጅ
ጓዴ የጴንጤ አማኝ
አያቴ ኦርቶዶክስ
የሚያምኑ በየሱስ
የዓባቴ ወገኖች
አሉ ብዙ እስላሞች
በክርስትና መልክ እስኪ ልጠይቅህ
በቃሊቲ ቦታ ቁርስ ምሳ ሲቀርብ
ማን  ጸሎት ያሳርግ
ብለህ ታውጃለህ
ዐረ ባላህ በሉ ወይንም በየሱስ
እስከመቸ ድረስ
እንዲህ እንታመስ
አዳምጠኝ ይልቅስ ወሪውን ልንገርህ
ብቻውን አልቅሷል ዖሮሞው አባትህ
ለአማራዋ እናትህ
ተው እንጅ ዓትቀልድ ምነው ምኑ ነካህ
ከለቅሶው ያልደረስህ
አሁን ገና ገባኝ አላህን ፈርቶ ነው
ሰላም በማወጅህ
ዐረ ባላህ በሉ ወይንም በየሱስ
እስከመቸ ድረስ
እንዲህ እንታመስ
© ለምለም  ጸጋው በስልምና ሃይማኖትም ሆነ መብታቸውን ለማስጠበቅ በመናገራቸው በእስር ቤት
ለሚማቅቁ ሁሉ (http://www.ethiomedia.com/assert/4785.html) 

No comments:

Post a Comment