Thursday, November 29, 2012

ኢትዮጵያ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ምርት እድገት አሳየች!

    

አቤ ቶኪቻው

ኢትዮጵያ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ምርት እድገት አሳየች!

አቶ ሃይለማም ሲፈሩ ሲተቡ ቆይተው ዛሬ የካቢኔ ሹመት ለማደረግ ፓርላማ ብቅ ብለው ነበር አሉ። ይዘዋቸው ከመጡዋቸው ካቢኔዎቻቸው መካከል ሌላ ሁለት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮችን ይገኙበታል።

አቶ ሃይለማሪያም ሲያስቡት ሲያስቡት ለአቶ ደመቀ ብቻ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነቱን መስጠት አይችሉትም ብለው ሰጉ መሰለኝ…(መሰለኝ ነው ያልኩት) ዛሬ አቶ ሙክታር ከድር እና አቶ ደብረ ፅዮን ገብረሚካኤልን ደጋፊ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አድርገው አሹመዋል። በጥቅሉ በአሁኑ ሰዓት ሀገራችን ሶስት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች አሏተው።

እኛ ሹመቱን ከላይ ከላይ የምናየው የመንግስታችን አድናቂዎች “እሰይ ሀገራችን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እድገት እመርታ አሳየች” ብለን ካገኘን ፅዋ ካጣን ደግሞ ግንባራችንን እያጋጨን ደስታችንን እንገልፃናል።

የምር ግን አቶ ሃይለማሪያም ያኔ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ይሰሩ የነበረ ጊዜ እንደው ሰውየው መለስ ሆነውባቸው “ተሸከሙ” ያሏቸውን ሁሉ “እሺ ጌታዬ” ይሏቸው ነበር እንጂ፤ የጫኑባቸው ሸክም በእጅጉ ከብዷቸው ነበር ማለት ነው!? አዎና ይኸው አቶ ደመቀ ሸክሙን አይችሉትም ብለው የጠረጠሯቸው ከራሳቸው ልምድ ተነስተው አይመስልዎትም!?

ሌላው ጥርጣሬ የኢህአዴግ “ፈላጭ ቆራጮች” (ይሄ “ፈላጭ ቆራጭ” የሚለው ቃል ኢህአዴግ ይፈልጣል ይቆርጣል ብሎ ለማሽሟጠጥ ታስቦ የገባ ቃል አለመሆኑን በቅንፍ አሰውቀን እንቀጥል) እና የኢህአዴግ ፈላጭ ቆራጮች አቶ ሃይለማሪያምን ለአንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ብቻ አምነው መተው ምቾት አልተሰማቸውም ይሆናል!

ለማንኛውም ዶክተር ቴውድሮስ አድሃኖምን ውጪ ጉዳይ ሚኒስትርነት ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል። ዶክተሩ ከጤና ጥበቃ የተነሱት ጤና ስለነሱ ይሁን ወይስ የውጭ ጉዳዩ ስራ ህክምና ስለሚያስፈልገው አልታወቀም። ሲታወቅ እናወጋዋለን!

 

 

አፈናው ከበረታ ገና በ“ፓፒረስ”ላይ እንጽፋለን!

 

አፈናው ከበረታ ገና በ“ፓፒረስ”ላይ እንጽፋለን!

ብሩክ ከበደ

ኢህአዴግ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረ በኋላ የምዕራባውያኖቹን ቀልብ ለመሳብ የሶሻሊዝም ካባውን በብርሃን ፍጥነት አውልቆ የመናገርና የመፃፍ መብትን “ሲፈቅድ” አስቦበትና ቆርጦ እንዳልነበር በዛወቅትም ሆነ አሁን ፕሬሱ ላይ የሚያደርሰውና እያደረሰ ያለው ችግር በቂ ምስክር ነው፡፡ ለስልጣናቸው መደላደልና ለርዳታ ፍጆታ ሲሉ “ፈቅደናል” ማለታቸው ያፀደቁትንም ሆነ የሕሊናን (equity) ሕግ እንዲደፈጥጡ አስችሏቸዋል፡፡

ሕዝብ የማወቅና የማሳወቅ መብቱ ሙሉ ለሙሉ እንዲገፈፍ በየወቅቱ የተለያዩ “ውሃ አይቋጥሬ” ምክንያቶች እየተፈጠሩ አፋኝ እርምጃዎች ተወስደዋል፡፡ በዚህ ተቃርኖአዊ አያያዝም በርካታ ጋዜጠኞች ታስረዋል፣ ተደብድበዋል፣ ተሰደዋል፣ ራሳቸውን አጥፍተዋል፡፡ ምንም ነገር ባልተሟላለትና በማይሟላለት ነፃ ፕሬስ ዙሪያም ለተሰባሰቡ ጋዜጠኞች ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች ማህበር ከአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ቀዳሚ የሆነውን ሽልማት ለኢነጋማ (አቶ ክፍሌ ሙላት ይመሩት ለነበረው ማህበር) መስጠቱ በዚያ አስቸጋሪ ሁኔታ ሳይበገሩ ይሰሩ ለነበሩት የነፃው ፕሬስ አባላት እውቅና የሰጠ ነበር፡፡

የእስላም ኢትዮጵያውያን የትግል ስልት

 

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

muslim ethiopians

በአለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ እስላም ኢትዮጵያውያን ማካሄድ የጀመሩት ትግል በዓይነቱም፣ በስፋቱም፣ በአስተሳሰቡም፣ በስሜቱም እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ ውስጥ ከአገዛዙ ጋር ከተደረጉ ትግሎች በጣም የተለየ ነው፤ በመጀመሪያ ደረጃ ትግሉ ለሃይማኖት ነጻነት ነው፤ ስለዚህም በአገዛዙ በኩል የፖሊቲካ ዓላማና የፖሊቲካ መልክ እየተሰጠው ሲሆን በእስልምና ምእመኖቹ በኩል ግን ትግሉን ከፖሊቲካ የጸዳ ለማድረግ ግሩም የሆነና የተሳካ ጥረት እያደረጉ ነው፤ ሁለተኛ የትግሉ ስልት ፍጹም ሰላማዊ በመሆኑ የአገዛዙን የጉልበት ስልት እያከሸፈ ያጋለጠው ይመስላል፤ አንዱና ዋነኛው የትግሉ ሰላማዊነት መግለጫ በቤተ መስጊድ መወሰኑ ነው፤ ይህ ስልት አዲስ አይደለም፤ በብዙ የአረብ አገሮች የሚጠቀሙበት ነው።

Wednesday, November 28, 2012

ሁለተኛው የኢህአዴግ መንግስት

(ከአስራት አብርሃም)
 

እናንተ፣ ያበሻ ሰዎች ተስፋን አትቁረጡ

ከስንት አመት ወዲያ

መልሰው ሊገዙ ንጉስ ጦና መጡ

 
ይህ ግጥም አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው የተሾሙ ጊዜ በፌስቡክ ላይ የተለቀቀ ነው። የገጣሚውን ማንነት ማወቅ ባልችልም ሀሳቡን የገለፀበት መንገድ ግን ሳላደንቅ ማለፍ አልችልም። ግሩም ድንቅ ነው!
በታሪክ እንደሚታወቀው የወላይታ የመጨረሻው ንጉስ ካዎ ጦና ነበሩ። ግዛታቸውን ላለማስነጠቅ አያሌ የመከላከል ጦርነቶች አካሄዷል፤ በኋላ ላይ በአፄ ምኒልክ ጦር ተሸንፈው፣ ግዛታቸውም ለሸዋው ሰፋሪ ጦር አስረክበው ለግዞት ተዳርጓል። ከዚያ በኋላ የወላይታ የሚባል ንጉስ አልነበረም። ለዚህ ነው ገጣሚው "ተስፋ አትቁረጡ" የሚል ስንኝ ያስቋጠረው። ከወላይታ፣ ኢትዮጵያን የሚገዛ መጣ ለማለት ተፈልጎ የተገጠመ ይመስላል። እውነትም ሰውዬ ኢህአዴግ ሆኑ እንጂ ከወላይታ መምጣታቸውስ ደስ የሚል እና ተስፋ የሚሰጥ ነው። ምክንያቱም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ "አቅም እስካለኝ ድረስ የአገሪቱን ከፍተኛ ስልጣን ለመያዝ የሚያግደኝ ነገር አይኖርም" ብሎ እንዲያስብ የሚያደርግ ነውና። ክፋቱ ግን አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ወደዚህ ስልጣን የመጡት በአቅም ብቃት ሳይሆን ለቀድሞው ጠቅላይ ሚንስቴር በነበራቸው ታማኝነት መሆኑ ላይ ነው። ይህን እውነት የሰውየው ነፍስ አባት በየዋህነት ለሪፖርተር ጋዜጣ ሰጥቷል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማስተዳደር ባቃታቸው ጊዜ ለአቶ መለስ ስልክ ደውለው "ኧረ እኔ አልቻልኩም ምን ማድረግ ይሻለኛል?" ብለው ያመለክታሉ።

Tuesday, November 27, 2012

በራስ አሉላ ስም የተሰየመው ት/ቤት በመለስ ተቀየረ

 

ከኢየሩሳሌም አርአያ

በትግራይ ተምቤን – አብዪአዲ የሚገኘውና በጀግናው ራስ አሉላ አባነጋ ስም ተሰይሞ የቆየው የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ስያሜው ተቀይሮ በመለስ ዜናዊ ስም እንዲሰየም መወሰኑን ታማኝ ምንጮች አስታወቁ።

በደርግ ዘመን የተሰራውና በራስ አሉላ ስም ተሰይሞ የ 9 – 10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ሲያስተምር ከቆየ በሑላ ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ የት/ቤቱን አቅም ለማሳደግ በሚል የ11-12ኛ መመሪያ ክፍሎችን ለመገንባት በአገር ውስጥና በውጭ አገራት የሚገኙ የአካባቢው ተወላጆች ገንዘብ አዋጥተው ስራው መከናወኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል። ግንባታው ተጠናቆ ባለፈው ነሃሴ ወር ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ እንዳለ አቶ መለስ በማለፋቸው ፕሮግራሙ መሰረዙን ሲታወቅ; ከሁለት ሳምንት በፊት በተከናወነው የምረቃ ስነ-ስርአት የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት በስፍራው እንደተገኙ ማወቅ ተችሎዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት አርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ልዩ ስሙ ጃንሱማ በተባለው ቦታ ወታደራዊ ጥቃት ፈጸመ

 

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በወያኔ ቅጥረኛና ምንደኛ የልዩ ሃይል ታጣቂ ቡድን ላይ የጀመረውን የማጥቃት ዘመቻ አጠናክሮ በመቀጠል ሕዳር 15-2005 ዓ.ምEthiopian People Patriots Front - EPPF አርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ልዩ ስሙ ጃንሱማ በተባለ ቦታ ባደረገው ውጊያ 14 የጠላት ወታደሮችን በመግደልና 12 በማቁሰል ከፍተኛ ወታደራዊ ድሎችን በማስመዝገብ ግንባሩ የተሰማራበትን ግዳጅ በድል እየተወጣ መሆኑን የግንባሩ ወታደራዊ መምሪያ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዘራፊውና ከነፍሰ-ገዳዩ የወያኔ አምባገነናዊ ገዥ ቡድን ለማላቀቅ ያለው ብቸኛ አማራጭ መንገድ በትጥቅ ትግል ስርዓቱን ማንበርከክ መሆኑን ጠንቅቆ ያወቀው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ሀገርንና ወገንን ለመታደግ ቆርጦ በመነሳት በሰሜኑ የሐገራችን ክፍል ወታደራዊ ስትራቴጅውን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ ሰሞኑን አርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ልዩ ስሙ ጃንሱማ በተባለው ቦታ ባደረገው የማጥቃት ዘመቻ 26 የጠላት ወታደሮችን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ወታደራዊ የበላይነትን የተቀዳጀ ሲሆን፣ ከሞቱት 14 የልዩ ሃይል ታጣቂ ቡድን መካከል አበበ የሚባለው የቀራቅር ተወላጅና አለልኝ የሚባል የደባርቅ ተወላጅ የሆኑት ከፍተኛ አመራሮች መሞታቸውን የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ወታደራዊ መምሪያ ገልጿል።

Monday, November 26, 2012

መቀሌ ዩኒቨርሲቲ እየታመሰ ይገኛል





መቀሌ ዩኒቨርሲቲ በተወሳሰበ ሙስና ውስጥ በመሆኑና የሙስናው ዋና ተዋናዮች ዶ/ር ክንደያ ገብረህይወት እና ዶ/ር ኣብዱልቃድር ከድር የተባሉ ምክትል ፕረዚደንቶች ይውረዱልኝ ብለው ከሶስት ወር በላይ የጠበቁት ጀርመናዊ ፕረዚደንት ችግር ላይ ናቸው።
የቦርድ ሰብሳቢው ኤርትራዊው ኣቶ ቴድሮስ ሓጎስ (የኢፈርት ቦርድ ሰብሳቢም ናቸው) ጀርመናዊውን በአካል እንዳስፈራሩዋቸው ታውቋል!
ይህ የሆነው ደግሞ ለትምህርት ሚንስትር ሳይቀር ግልባጭ ባደረጉት የአዲስ ምክትል ፕረዚደንቶች ሹመት የተነሳ ነው።
ጀርመናዊው ፕረዚደንት ከሶስት ወር በላይ/August-November/ የጠየቁትን ጥያቄ ሳይመልሱ ተኝተው የከረሙት ኣቶ ቴድሮስ ሓጎስ አውቆ የተኛ ቢቀሰቅሱት ይማታል የሚል አዲስ ዓይነት ቢሂል ፈጥረዋል! ከ300 million ብር በላይ ያባከኑን ሰዎች ገለል እንዲሉ መጠየቃቸው ሊመሰግኑ ሲገባ እንግዳውን German ሰውዬ እንደዚህ እንደውሻ የሚያስፈራሩዋቸው እነ ቴድሮስ ሓጎስ ወደ ማፍያነት መቀየራቸው ጉልህ ማሳያ ነው። ይህን ህዝብ ከመጤፍ እንደማይቆጥሩትና እንዳሻቸው መኖር እንደሚችሉ ግልፅ ማሳያ ነው። ይህ ህዝብ በሚከፍለው ግብርና በደሙ እየነገዱ የሚኖሩት እስከ መቼ ነው? ትግራይ ተማርሯል በማስፈራራት ና በጉልበት ልክ እንደ ትግራይ ህዝብ ደመኛው ለገሰ አስፋው ትግራይን ኤርትራዊው ቴድሮስ ሓጎስ እየገዙዋት ነው። የሚሰርቅን ሰው መጠየቅ ሲገባቸው ኣብሮዋቸው እንደሚሰርቅ በግልፅ በሚያሳይ መልኩ መከላከላቸው ይህ ስርዓት ምን ያህል እንደዘቀጠ፣ ወድቀቱም እንደቀረበ ያሳያል።

ኢሳትን አያችሁ የተባሉ ወታደሮች ታሰሩ፤ ሠራዊቱ ዉስጥ የተፈጠረዉ መከፋፋል አሁንም እንደቀጠለ ነዉ

 

 

ኢሳትን አያችሁ የተባሉ ወታደሮች ታሰሩ፤ ሠራዊቱ ዉስጥ የተፈጠረዉ መከፋፋል አሁንም እንደቀጠለ ነዉ

[ግንቦት 7 ዜና] ሰሜን ኢትዮጵያ ዉስጥ በባድሜ ግንባር ወታደራዊ ክበባቸዉ ዉስጥ ቁጭ ብለዉ በናይልሳት የሚተላለፈዉን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንን ሲከታተሉ የተገኙ በርካታ ወታደሮች ለሁለት ሳምንታት ታስረዉ በከባድ ማስጠንቀቂያ መለቀቃቸዉን ትግራይ ዉስጥ የሚገኙ ወታደራዊ ምንጮቹን በመጥቀስ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት ዘገበ። አንድ ስማቸዉና ማዕረጋቸዉ እንዳይጠቀስ የጠየቁ ከፍተኛ መኮንን በስልክ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት ወታደሮቹ የታሰሩት በክበባቸው ውስጥ ቁጭ ብለዉ የኢሳትን ዝግጅት ሲከታተሉ ሲሆን ከ 14 ቀናት እስርና እንግልት በኋላ የተፈቱት የዲሻቸውን አቅጣጫ ወደ ናይል ሳይት ያዞሩት ሳያዉቁ በስህተት መሆኑን ለበላይ አለቆቻቸው ተናግረዉ ዳግመኛ ኢሳትን እንደማይመለከቱ ቃል ከገቡ በኋላ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

የሱዛን ራይስ ሸፍጥ በቤንጋዚው ጥቃት ላይ!

    

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

Click here for English version

Click here for PDF

በሴፕቴምበር 2 2012 የአሜሪካዋ አምባሳደር በተባበሩት መንግስታት: ሱዛን ራይስ በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የቀብር ስርአት ላይ ስሜታዊ ሆና የሚያቅለሸልሽ ቃላት ያዘለ ንግግር አነብንባ ነበር፡፡ መለስን፤ ‹‹የማይደክምና ራሱን የማይወድ››በአጠቃላይ እሱነቱ ለስራውና ለቤተሰቡ የሆነ ብላዋለች፡፡ ‹‹ጠንካራ፤ በእምነቱ የጸና እና በእርግጥም ለጂሎችና ለደደቦች እሱ እንደሚጠራቸው ትእግስቱ ትንሽ ነበር፡፡ ሱዛን ራይስ ይህን ቅጥ ያጣና ከአንድ አሜሪካን ከሚያህል ሃገር ወኪል ጨርሶ ሊሰማ የማይገባ ያልተገራ ንግግር ስታደርግ ጅልና ደደብ የሚለውን ቃል በድፍረትና በአጥንኦት የለጠፈችው በኢትዮጵያዊያን ነጻ ጋዜጠኞች፤የተቃዋሚ መሪዎች፤ተሟጋቾች፤የፖለቲካ እስረኞች፤የሲቪል ማሕበረ ሰብ መሪዎች፤እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ላይ ነው፡፡ የንግግሯን ቪዲዮ በመመልከት ሴትዮዋ ይህን ንግግር የመለስን ተቃዋሚዎች በመጨረሻ ጡጫ ደረታቸዉን ብላ ለመለስ የአስከሬን መሸኛ አድርጋ ማቅረቧ እንደነበር ያስታውቃል፡፡

Susan Rice, the U.S. Ambassador to the U.N. Addis Ababa speech, Alemayehu G. Mariam‹‹ አንድ አይነት ላባ ያላቸው ወፎች አብረው ይከንፋሉ›› ይባባል፡፡ ራይስ እንደ መለስ ሁሉ ተቃዋሚዎቿንና ሃሳቧን የማይጋሯትን ትሳደባለች ታንቋሽሻለች፡፡ በስቴት ዲፓርትመንት አካባቢ የሚያውቋት በዘለፋ በቁጣና በማስፈራራት አነጋገራዎ ነው፡፡ በዚህም አጉል ደንፊ ተብላ ትታወቃለች፡፡ አለያም በጣም በሚያውቋት ዘንድ ‹‹የቻይና መደብር በሬ›› (አተራማሽ ወይም በጥባጭ ማለት ነው) ይሏታል፡፡ በስብሰባዎች ላይ በቃላት ርችት፤በአፈነበልባል፤በጣት ቀሳሪነት ራይስ ትታወቃለች፡፡ በአንድ ወቅት በአሜሪካን ዲፕሎማቶች ዋና ታዋቂ በነበሩት ሪቻርድ ሆል ብሩክ ላይ የበላዮች ስቴት ዲፓርትመንት አባላት ስብሰባ ላይ በአሜሪካንና በሌላውም ዓለም በሳቸው ደረጃ ካሉ ሰዎች የማይጠበቀውንና ጸያፍ ተብሎ የሚጠራውን ድርጊት በአደባባይ የመሃል ጣታቸውን ቀስረውባቸዋል ይባላል፡፡

የአቡነ ጴጥሮስ መታሰቢያ ሐውልት፣ የሚያለማውስ?

ከድሜጥሮስ ብርቁ -ቶሮንቶ

 የዳግማዊ ምንሊክ አና የአቡነ ጴጥሮስ መታሰቢያ ሃውልቶችን ከስፍራቸው ለማንሳት ዝግጂቱ አንደተጠናቀቀ ስሰማ አሁን በስልጣን  ላይ ያለው የህወሃት ቡድን በትክክልም የ”መለስን ራዕይ”ለማስፈጸም ደፋ ቀና አያለ አንደሆነ ተረዳሁኝ። ከዚህ በፊት በሌላ ፅሁፍ አንደገለጽኩት የ”መለስ ራዕይ” የሚባል ነገር አንደሌለ እና የመለስ አየተባለ ለመሸጥ የሚሞክረው “ራዕይ” በትክክል የህወሃት ለመሆኑ አመላክቻለሁ። ጣሊያን ኢትዮጵያን ሲወር የነበረው የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ “ሃገሪቱን አሰለጥናለሁ” የሚል ነበር። አስቡት የኢትዮጵያ ስልጣኔ ጉዳይ ወዝውዞት ከጣልያን ሃገር ድረስ ጦር ሰብቆ ሲመጣ። አቡነ ጴጥሮስ በግፍ ሃውልታቸው የቆመበት ቦታ ላይ የተገደሉትም ዛሬ ህወሃት በሚጠቀመው ቋንቋ ሲመነዘር “ጸረ-ልማት” ናቸው በሚል ነበር።

Abune Petros was born in 1892 in a farmer family in the city of Fiche

 

ሲጀመር “ልማት” የሚለው ‘ዲስኩር’ ከጥርጣሬ ይልቅ የህዝብን አመኔታ አንዲገዛ ማድረግ ያስፈልጋል። መረጃ በማፈን፣ ውዢንብር አንዲነግስ በማድረግ ደሞ የህዝብን ትኩረት ለጊዜው በማስቀየር ሌላ የፓለቲካ ጥፋት ከበስከጀርባ መስራት ይቻል አንደሁ አንጂ የሕዝብን አምነት መግዛት አይቻልም። በዚሁ ሃውልት ጉዳይ አንኳን የሚወራው ዜና የተደበላለቀ ነው። መጀመሪያ ይፈርሳሉ የሚል መረጃ ተለቀቀ። ህዝቡ ሲጯጯህ ደሞ “የለም አይፈርሱም” የአቡነ ጴጥሮስ ሃውልት ብቻ ነው ለጊዜው በባለሙያዎች “በክብር” ከቦታው የሚነሳው። ተመልሶም በባለሙያዎች በክብር የነበረበት ቦታ “በክብር” ይቀመጣል” የሚል መረጃ ተለቀቀ። የኋለኛውን መረጃ የምድር ባቡር “ባለስልጣን” (መሆኑ ነው) የተናገረው ተባለ። የባለስልጣኑን ቃል አንደወረደ ማመን ከተሞክሮ አንጻር ስህተት ሊሆን ይችላል። ማን ይሆን? ከየት ይሆን ብሎ -ለማወቅ ያህል- መጠየቁ ዘመኑ ከፈጠረው ፖለቲካ አስተሳሰብ ሳይሆን ካለው ነባራዊ የፓለቲካ የሃይል ሚዛን አና አሰላለፍ ነው መታየት ያለበት። በ “ልማት” ስም መታሰቢያ ሀውልቱን በባለሙያ “በክብር ከማስነሳት” ይልቅ ሃውልቱ በማይነካበት ሁኔታ ባለሙያዎች መስራት የተፈለገውን ግንባታ አንዲሰሩ ስለመቻላቸው ወይንም ስላለመቻልቸው ስለመሞከሩ አና ስላለመሞከሩ የምናውቀው ነገር የለም። የራሳችንን ግምት ግን አንወስዳለን -የአቡነ ጴጥሮስ መታሰቢያ “ለህወሃት ምኑ ነው?” የሚል ጥያቄ ግምት ውስጥ በማስገባት። የህወህትን ተፈጥሮ አና ባህሪ ግምት ውስጥ በማስገባት!

Friday, November 23, 2012

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ሊፈርስ ነው


ዳር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:- በአዲስ አበባ የሚገኘው የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልትሊፈርስ ነው:፡ ዛሬ በሸገር ኤፍ ኤምላይ ቀርበው መግለጫ የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሀላፌ እንዳሉት ከባቡር ስራ ጋር በተያያዘ የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ይነሳል::ሆኖም መነሳቱ በጊዜዊነት ነው ሀዲዱ ከተሰራ በሆላ ወደቦታው ይመለሳል ብለዋል:: የኢሳት ምንጮች ከፕሮጀክት መሀንዲሶች አካባቢ የተገኘን መረጃ ጠቅሰው እንደገለጡት የሀዲዱ ዲዛይን ላይ ለሚነሳው የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ላይ ቦታ የለም እናም ሀውልቱ እንደፈረሰ የመቅረቱእድል የሰፋ ነው ሲሉ ገልጠዋል:፡ በተያያዘ መረጃ በዲዛይን ላይ የአጼ ሚኒሊክ ሀውልት ተመሳሳይ እጣ ፈንታ ሊገጥመው እንደሚችል ታውቆል:: መንግስት ጊዚያዊ ነው ቢልም ዲዛይኑ የሚያረጋግጠው ግን ሀውልቶቹ እስከወዲያኛውም ወደቦታቸው እንደማይመለሱ ነው::ከፍተኛ ተቃውሞ የቀረበበትና በሲኖዶስ እንዲፈርስ የተወሰነው የአቡነ ጳውሎስ ሀውልት ቆሞ የታላቁ አርበኛና መስዋእት አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ሊፈርሱ ነው መባሉ በእርግጥ አነጋጋሪ ሆኖል።


Abune Petros was born in 1892 in a farmer family in the city of Fiche

ኢህአዴግና ስርአቱ፤ በዘመመ ጎጆ የነገሰ የእብዶች ተስካር


Bizuayehu Tsegaye

ሰላም እንደምን ከረምን አንባቢያን? ክዚህ ቀደም ‘Bureaucracy; the pillar EPRDF rusting’ በሚል አርእስተ አንድ መጣጥፍ ለአንባቢያን አካፍዬ ነበር። ምናልባትም በሃገርኛ ብታካፍለን ያለኝ አንድ አንባቢ ነበርና አማርኛ መተየቢያ ‘ንድፈ ቁስ‘ ስፈልግ ሳፈላልግ ሰነበትኩ። ተሳክቶም ይህዉ በእንዲህ ዳግም መጣሁ።

አርእስቱ ታዲያ በሀገራችን የማህበራዊ አገልግሎት አሰጣጥ ልምድ ሲደመጥ የኖረን ቅራኔ መነሻ ያደረገ ነበር። የብልሹ አሰራር ልምድ በአሁኑ አስተዳደር አጀማመር ፣ ያለፈበትን ደረጃ ፣ በወቅቱ ያለበትን ሁኔታ ፣ በዚህ የተነሳ ወደፊት ለመተግበር የሚገደዉን አሉታዊ እጣፈንታ እንዲሁም የመፍትሄ ሀሳብ በመጠቆም የተገነዘብኩትን ያህል ለማካፈል ሰፍሮአል።

ለመነሻ ያህልም በአሁኑ ወቅት ቁጥር የሌለዉ ብሶት በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ማሰማት እንግዳ አለመሆኑን ፤ እንዲያዉም በአግልግሎት አሰጣጡ እና በ አገልግሎት ሰጪ አካላት መሃከል ስላለዉ መስተጋብር ትዝብት ለመዳሰስ ሞክሯል። መሳካቱ በምላሻችሁ የሚረጋገጥ ይሆናል። አንባብያንም በጉዳዩ የየግል አመለካት ኖርአችሁ ለማካፈል ትፈቅዱ ይሆናል። ለዚህ ግልጥ የሃሳብ ልዉዉጥ የምክንያትነት ‘ማእረጉ’ን ግን ከእኔ ዘንድ እንድታኖሩት ተጠቁሞ ነበር። አሁንም እንዳለ መሆኑን በማስተላለፍ…እንዲህ ቀርቦአል።

በሐገራችን እንዳብዛኛዉ የወቅቱ ኢትዪጲያዊ ወጣት ሁሉ ያኔ ወያነ/ኢህአዴግም በእስተዳደር ልምዱ ልጅእግር ፤ ይበልጥ ሊገልጠዉ በሚችል ቃል እንጭጭ አሊያም ጥሬ ሳለ ይብዛም ይነስ አገልግሎታቸዉን ለተጠቃሚዉ ማህበረሰብ ለማድረስ ፍሬ ያለዉ የመተዳደሪያ ህገ ደንቦች እንዲሁም በሚወጡት ህግጋት የሚገዙ/ለመገዛት ዝግጁ የሆኑ አካላት ነበሩ። በእድሜ ጠና ያሉም ይህ የቀድሞዉ አስተዳደር ዉርስ የፈጠረዉ ተጥኖ ሊሆን እንደሚችል ሊገምቱ ይችላሉ ማለት ስህተት ላይሆን ይችላል።

Friday, November 16, 2012

"ሰንበት ምሳ"



አቤ ቶኪቻው



 

እኛ ሰፈር ሽሮሜዳ የሰንበት ምሳ የሚባል ነገር አአለ። እሁድ እሁድ ቤተሰቦች ለልጆቻቸው የሚሰጡት ሳንቲም፤ አንዳንዴም ወዳጅ ለወዳጁ በእሁድ ቀን የሚያበረክተው ስጦታ (ብዙ ጊዜ ይህ ስጦታ ወይ ስሙኒ ወይ ደግሞ ሃምሳ ሳንቲም ነው) ብቻ ግን "ሰንበት ምሳ" ነው የሚባለው። ሰሞኑን በሌላ መስኮት ልመጣ አስቤ ተጠፋፍተን ሰነበትን አይደል!? እስቲ ዛሬ በዝች ሰንበት "ሃይ" እንባባል

ይቺ ፅሁፍ አዲስ ታይምስ (ፍትህ) ትላንት ይዛት ትወጣ ዘንድ ልኪያት ነበር። ከርዕሷ በቀር እንዳለች ናት! (ሃ አንዳንድ ቦታ ትንሽ ነካ ነካ ተደርጋለች) እስቲ ለማንኛውም እንቋደሳት፤ ተጀመረች

Thursday, November 15, 2012

በደራ ወረዳ የተፈጸመው ኢሰብዓዊ ድርጊት አነጋጋሪነቱ ቀጥሎአል -የወንጀሉ ተባባሪዎች የሆኑ 3 ፖሊሶች እስካሁን አልተያዙም


ህዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም



ኢሳት ዜና:-በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በደራ ወረዳ በገብሮ ቀበሌ የፍትህና ጸጥታ ሹም የሆነ ግለሰብ ከሶስት ፖሊሶች ጋር በመ ሆን በቀበሌው የሚኖርን አንድን ግለሰብ መሳሪያ ደብቀሀል በሚል ሰበብ ግለሰቡንና ባለቤታቸውን ልብሳቸውን በማስወለቅ እርቃናቸውን እንዲታሰሩ ማድረጉን፣ እንዲሁም ባልየው ብልቱ በገመድ እንዲታሰር ከተደረገ በሁዋላ ህዝብ በተሰበሰበበት አደባባይ እርቃኑዋን የሆነቸው ባለቤቱ አስጸያፊ ድርጊቶችን እንድትፈጽም፣ በሰደፍ በመመታቱዋም የስድስት ወር ልጇን እንድታስወርድ መደረጉን የገበሮን የቀበሌ ሊቀመንበር፣ የወረዳውን አስተዳዳሪና አንድ የምክር ቤት አባልን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።

 ዜናው በኢሳት ይፋ ከሆነ በሁዋላ ኢትዮጵያውያን የተሰማቸውን ስሜት እየገለጹ ነው። አንድ በደቡብ ክልል ተወላጅ የሆኑ ሰው በአካባቢያቸው በደራ ከተፈጸመው የሰብአዊ መብት ጥሰት ያለነሰ ድርጊት በአለታ ወንዶ መፈጸሙን ገልጸዋል
 ሌላው ኢትዮጵያዊ ደግሞ ለዚህ ሁሉ ድርጊት ተጠያቂው ስርአቱ ነው ሲል መንግስትን ከሷል
ከፈረንሳይ አገር ትእግስት የምትባል ሴት በሰጠችው አስተያየት ድርጊቱ ድንጋጤን እንደፈጠረባት ተናግራለች
ሌላ በውጭ አገር የሚኖር ኢትዮጵያዊ በበኩሉ የመንግስቱ ሹም የሰራው ስራ እጅግ እንዳሳዘነው ገልጾ ፣ ህዝቡ እንዲህ አይነት ግፍ ሲፈጸም ዝም ብሎ መመልከቱ ጥያቄ እንደፈጠረበት ተናግሯል
 በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆኑት ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ ፣ ድርጊቱ ሴትነታችን፣ እናትነታችን ከሁሉም በላይ ኢትዮጵያዊነታችን የተዋረደበት ጊዜ ላይ መድረሱን ያሳያል ብለዋል
ወ/ሮ ሰብለ ወርቅ ታደሰ እንዳሉት መንግስት እንዲህ አይነት ሰዎችን በዙሪያው አሰልፎ ስልጣን ለላይ ለመቆየት ማሰቡንና ፣ በስልጣን ላይ እስከቆየ ድረስ እንዲህ አይነት የሰብአዊ መብት ጥሰት ሲፈጸም ችላ እንደሚል የቀደመ ልምዳቸውን በማንሳት ተናግረዋል
 ወ/ሮ ሰብለ በመጨረሻም ህዝቡ እርምጃ መውሰድ ካልቻለ ባርነታችን መቀጠሉ አይቀሬ ነው ብለዋል
ሌላው የሰብአዊ መብቶች ተማጋች የሆኑት አቶ ብዙነጽ ጽጌ በበኩላቸው ድርጊቱ ከባህላችን የወጣ በመሆኑ ሀዘንና ድንጋጤ የተሰማቸው መሆኑን ገልጸው፣ አሁን ባለው ስርአት በህግ መፍትሄ ይመጣል ብለው እንደማያስቡ ገልጸዋል።
አቶ ብዙነህ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አጠቃላይ የስርአት ችግር የሚፈጥረው መሆኑን ተናግረዋል
 ምንም እንኳ አሰቃቂ ድርጊቱን የፈጸመው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ቢውልም እስካሁን ድረስ ለፍርድ እንዳልቀረበ ታውቋል። ከግለሰቡ ጋር በመተባባር ወንጀል የፈጸሙ ሶስት የወረዳው ፖሊሶችም በቁጥጥር ስር አልዋሉም።
የወረዳው ባለስልጣናት በትናንትነው እለት መረጃውን ለኢሳት ያቀበለውን ሰው ለመለየት እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ተሰብስበው እንደነበር ለማወቅ ተችሎአል።

    Wednesday, November 14, 2012

    ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ በጀርመን አገር ዋና ከተማ በርሊን ላይ ተደረገ

    በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአይነቱ ልዩ የሆነ በተለያዩ መፈክሮች እና በኢትዮጵያ ባንዲራ ያሸበረቀ ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ በጀርመን ዋና ከተማ በርሊን አደረጉ። ሰላማዊ ሰልፉን ያዘጋጀው በጀርመን የፖለቲካና የሲቪክ ማህበራት አንድነት ድርጅት (EPCOU) ሲሆን በእለቱም ከተለያዩ የጀርመን አካባቢ የሚኖሩ ቁጥራቸው ከ290 በላይ የሚገመት ኢትዮጵያውያን ተሳትፈዋል::መነሻውን በርሊን ከተማ SPD (ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ) ዋና ቢሮ ፊት ለፊት ያደረገው ሰላማዊ ሰልፍ የኢትዮጵያውን አምባገነን ስርአት ቁንጮ የሆነውን ስብሃት ነጋ በጀርመን ተጋብዞ ንግግር እነዲያደርግ መጋበዙ ኢትዮጵያውያንን እጅግ በጣም ያሳዘነ እና ያስቆጣ ድርጊት መሆኑን በመፈክር አሰምቷል። የሰላማዊ ሰልፍኛው ተወካዮች ከሶሻል ዲሚክራቲክ ፓርቲ ተወካይ ጋር አጠር ያለ ንግግር አድርገው የተዘጋጀውን ፅሁፍ ለተወካዩ ሰተዋል። ሰላማዊ ሰልፈኞቹ SPD (ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ) ዋና ቢሮ ፊት ለፊት ሲያሰሙት ከነበረው መፈክር መካከል ስብሃት ነጋ ስለ ሰብአዊ መብትና ዲሞክራሲ የመናገር የሞራል ብቃት የለውም ! Shame on SPD for inviting Ethiopian dictator Sebehat Nega ! እና ሌሎችም ይገኙበታል።

    Friday, November 9, 2012

    “ኦባማ መጀን” ወይስ “በእውቀት” መደራጀት?


    obama back to w h


    የአሜሪካ ምርጫ ሲጠናቀቅ ተሸናፊው ሚት ሮምኒ ደጋፊዎቻቸው በተሰበሰቡበት አዳራሽ ምስጋና ካቀረቡ በኋላ እንዲህ አሉ፡- “… ሁለታችንም ለምንወዳት አገራችን የምንመኘውን ለማድረግ በተለያየ አቅጣጫ ሞከርን፤ … ሕዝባችን ደግሞ የሚፈልገውን መሪ መረጠ፤ … ስለዚህ ፕሬዚዳንቱን ደውዬ አነጋሬያቸዋለሁ፤ ባገኙትም ድል እንኳን ደስ አለዎ ብያቸዋለሁ፤ … በተለይ ለእርሳቸው፣ ለቀዳማዊ እመቤት እና ለልጆቻቸው ሁሉ መልካሙን እመኛለሁ፤ … አገራችን ከባድ ፈተናዎች ተጋርጠውባታል፤ … ባለቤቴና እኔ ለፕሬዚዳንቱና ቤተሰባቸው ከልብ እንጸልያለን፤ በሥራቸው ስኬት እንዲያገኙና ታላቋን አገራችንን በመምራት የሚያከናውኑት ሁሉ የተሳካ እንዲሁን እመኛለሁ፡፡” ይህንን ካሉ በኋላ ወደተለመደው ህይወታቸው ሄዱ – የፖለቲካ ገዳም ገቡ፡፡ ይህ ንግግር ወደራሳችን እንድንመለከት የሚያደርግ ነው፡፡ የእኛስ ፖለቲከኞች ዕድሜ ልካቸውን የፖለቲካ አክሮባት እየሰሩ አንደ ፓርቲ ሲያቋቁሙ፤ ሌላ ሲያፈርሱ፤ አንዱን ሲጠልፉ ሌላውን በሾኬ ሲሉ … ከመቆየት ይልቅ የሚሞክሩትን ሞክረው አልሆን ሲል በክብር ለተከታዩ ቦታ ለቅቀው ወደ ፖለቲካ ገዳማቸው የሚገቡት መቼ ይሆን?
    የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በድጋሚ መመረጥ ብዙ የተጠበቀ ቢሆንም የአሜሪካ ሚዲያ እንደተለመደው በሕዝቡ ውስጥ በፈጠረው የ“አፍጥጣችሁ እዩኝ” ፍላጎት ምክንያት አንድን ምሽት በስሜት ውጥረት እንዲያልፍ አድርጓል፡፡ “ተስፋ” እና “ለውጥ” የተሰኙ ልብን የሚያማልሉ ቃላትን በመላው ሕዝብ ዘንድ በማስረጽ የዛሬ አራት ዓመት እጅግ ከፍተኛ በሆነ የሕዝብ ድጋፍ የተመረጡት ባራክ ሁሴን ኦባማ እንደገና ለተጨማሪ አራት ዓመታት ተመርጠዋል፡፡ አራት ዓመት መለስ ብለን ስንቃኘው የታሰበው “የለውጥ ተስፋ” ተግባራዊ ሆነ ወይስ ተጨማሪ አራት ዓመታትን “አዲስ ንጉሥ እንጂ ለውጥ መቼ መጣ” በእንግሊዝኛ የሚያስዘፍን ነው?

    እነ አቶ አንዱለም አራጌ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ




    ጥቅምት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

    ኢሳት ዜና:-በሽብርተንነት ወንጀል ተከከሰው ብግፍ እስር ላይ የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ ም/ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አንዱአለም አራጌ፣ ሌላው የአመራር አባል አቶ ናትናኤል መኮንን እንዲሁም የመኢዴፓ የአመራር አባል የሆነው አቶ ክንፈ ሚካኤል ደበበ የይግባኝ አቡቱታቸውን ለማቅርብ ፍርድ ቤት ቢቀርቡም ዳኞቹ ለህዳር 13 ቀን 2005 ዓም ቀጠሮ በመስጠት ችሎቱን አሰናብተዋል።
    የፍርድ ሂደቱን በተመለከተ ችሎቱን የተከታተሉትን አንድነት ፓርቲ ሊቀመንበርና የቀድሞው የኢትዮጵአ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የእስረኞች መንፈስ ጠንካራ እንደነበር ተናግረዋል።
    የኢትዮጵያ መንግስት በግፍ ያሰራቸውን የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈታ በአለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች እና መንግስታት ቢጠየቅም እስካሁንም አሻፈረን እንዳለ ነው።

    Thursday, November 8, 2012

    ኢህአዴግ ስንት ቦታ ሊሰነጠቅ ይችላል?


    (ከተመስገን ደሳለኝ)

    ብርዱ የጥቅምት ነው፤ አጥንት ድረስ ዘልቆ የሚያንቀጠቅጥ ኃይለኛ ቅዝቃዜ፡፡ አዲስ አበባ ገና ከእንቅልፏ በመንቃት ላይ ነች፡፡ ለስራ የቸኮሉ መንገደኞች ትራንስፖርት ፍለጋ ወዲያ ወዲህ ይካለባሉ፡፡ ማክሰኞ ጥቅምት 7 ቀን 2005 ዓ.ም. ከጠዋቱ 12 ሰዓት ከ50 ደቂቃ ላይ ብስራተ ገብርኤል አደባባይ ‹‹መገናኛ ራዲዮ›› በያዙ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ የትራፊክ ፖሊሶቹ ስራ የበዛባቸው ይመስላሉ፡፡ 12 ሰዓት ከ55 ደቂቃ ሲል በሁለት የሞተር ብስክሌት በተፈናጠጡ የትራፊክ ፖሊሶች ፊት አውራሪነት አንዲት ሳይረን የተገጠመላት የፖሊስ ታርጋ የለጠፈች መኪና የ‹‹መንገድ ልቀቁልኝ›› ጩኸቷን እያንባረቀች አቋርጣ በማለፍ ወደ ሳር ቤት አቅጣጫ ከነፈች፡፡ ሶስት ‹‹ቪኤት›› መኪና ሰለሱ፡፡ ሌላ ባለሳይረን መኪናም ከኋላ እየተከተለች ነው፡፡ ሁሉም መኪኖች በከባድ ፍጥነት ነው የሚበሩት፡፡ ሳር ቤት ያለው የፑሽኪን አደባባይም ተመሳሳይ ቁጥር ባላቸው የትራፊክ ፖሊሶች ተጨናንቋል፡፡ ሜክሲኮ አደባባይ፣ አምባሳደር፣ ፍልውሃ፣ ገብርኤል መሳለሚያ… ቤተ-መንግስቱ የአጀቡ መድረሻ ቦታ ነው፡፡
    አጀቡ አዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝን ከመኖሪያ ቤታቸው ወደ ስራ ቦታቸው ለማድረስ ነው፡፡ ይኸው ትዕይንት ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ላይ ይደገማል፡፡ ቅደም ተከተሉ ተገልብጦ፤ ከቤተ-መንግስት… ብስራተ ገብርኤል፤ የአደጋ ማስጠንቀቂያ ድምጽ፡፡

    Wednesday, November 7, 2012

    ዜና ፎቶ፤ ትላንት ቃሊቲ ይሄንን ትመስል ነበር




    በቃሊቲ ማሰሪያ ቤት እነርሱ “ማረሚያ ቤት” ይሉታል። በርካታ ወገኖቻችን እንደሚገኙ ይታወቃል። በቅርቡ ደግሞ የሙስሊም ኢትዮጵያውያን መፍትሄ አፈላላጊዎች ወደ ቃሊቲ ተዛውረዋል። ይህ ፎቶ ህብረተሰቡ ከታሳሪዎቹ ጎን መሆኑን ያሳያል። “አያሳይም” የሚል ካለ በደንብ ደግሞ ይመልከተው!  ፎቶውን ብቻ ሳይሆን የታሰሩበትንም ምክንያት በደንብ ብንመለከት ደግሞ ሁላችንም ከነዚህ ወገኖች ጎን  መቆማችን አይቀሬ ነው!
    በመጨረሻም
    እንመርቃለን…
    እግዜር ያለ አሳሪዎችን “ሃይ…!” ይበልልን ታሳሪዎችን ያበርታልን!

    Tuesday, November 6, 2012

    ማን ጸሎት ያሳርግ


    (ለምለም ጸጋው)



    “በቃሊቲ ማሰሪያ ቤት እነርሱ “ማረሚያ ቤት” ይሉታል። በርካታ ወገኖቻችን እንደሚገኙ
    ይታወቃል። በቅርቡ ደግሞ የሙስሊም ኢትዮጵያውያን መፍትሄ አፈላላጊዎች ወደ ቃሊቲ
    ተዛውረዋል። ይህ ፎቶ ህብረተሰቡ ከታሳሪዎቹ ጎን መሆኑን ያሳያል። “አያሳይም” የሚል ካለ
    በደንብ ደግሞ ይመልከተው!  ፎቶውን ብቻ ሳይሆን የታሰሩበትንም ምክንያት በደንብ
    ብንመለከት ደግሞ ሁላችንም ከነዚህ ወገኖች ጎን መቆማችን አይቀሬ ነው!”November 
    5th, 2012”  (http://www.ethiopianreview.net/index/?p=47899)

    ማን  ጸሎት ያሳርግ 

    ወይ ነውር አይገዛው
    አምልኮት ዓልነካው፤
    የእትዮጵያን ሰው ሁሉ
    በቃሊቲ አጎረው።
    ይድነቃችሁ ብሎ
    በየሱስ ስም ማለ፤የመለስን ወንጌል
    እንደ ክታብ እርጎ
    በአንገቱ ሰቀለ።
    ለሁሉም ለመሆን
    አዲሱ ምንስቴር በቃሊቲ ሳይቀር፤
    አርብ ሰኞ ሳይል
    አለ ዓላህ አክብር።
    ምነው የኔ ወዳጅ
    ጓዴ የጴንጤ አማኝ
    አያቴ ኦርቶዶክስ
    የሚያምኑ በየሱስ
    የዓባቴ ወገኖች
    አሉ ብዙ እስላሞች
    በክርስትና መልክ እስኪ ልጠይቅህ
    በቃሊቲ ቦታ ቁርስ ምሳ ሲቀርብ
    ማን  ጸሎት ያሳርግ
    ብለህ ታውጃለህ
    ዐረ ባላህ በሉ ወይንም በየሱስ
    እስከመቸ ድረስ
    እንዲህ እንታመስ
    አዳምጠኝ ይልቅስ ወሪውን ልንገርህ
    ብቻውን አልቅሷል ዖሮሞው አባትህ
    ለአማራዋ እናትህ
    ተው እንጅ ዓትቀልድ ምነው ምኑ ነካህ
    ከለቅሶው ያልደረስህ
    አሁን ገና ገባኝ አላህን ፈርቶ ነው
    ሰላም በማወጅህ
    ዐረ ባላህ በሉ ወይንም በየሱስ
    እስከመቸ ድረስ
    እንዲህ እንታመስ
    © ለምለም  ጸጋው በስልምና ሃይማኖትም ሆነ መብታቸውን ለማስጠበቅ በመናገራቸው በእስር ቤት
    ለሚማቅቁ ሁሉ (http://www.ethiomedia.com/assert/4785.html) 

    ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አሜሪካውያን በ2012 ምርጫ መሳተፍ ይገባቸዋል

    ከፕሮፌሰር  ዓለማየሁ  ገብረማርያም
    ትርጉም  ከነጻነት ለሃገሬ
    ጉዳዩ የምርጫ  ብቻ አይደለም እኮ
    ባለፈው ሴብቴምበር ስለ ፕሬዜዳንት ባራክ ኦባማ ድጋሚ መመረጥ ድጋፌን ገልጬ ነበር፡፡ ለታዳሚዎቼ  እንዳስነበብኩት በ2008 ምርጫ ተወዳዳሪ ባራክ ኦባማን ደግፌ እንደነበርና
    Ethiopian Americans your vote counts vote on November 6 2012
    ከምርጫው በኋላ ግን በታየው በተለይም ኢትዮጵያንና  አፍሪካን በተመለከተ  ስለተካሄደው አስተዳደራዊ ፖሊሲ ግን በጣሙን ቅሬታ አድሮብኛል፡፡ እንደትጠቀስኩት:-
    ፕሬዜዳንት ኦባማ በአፍሪካ ውስጥ ተግባራዊ አደርጋለሁ ያሉትን መልካም አስተዳደርን፤የሰብአዊ መብትን መከበር፤የዴሚክራሲን ተግባራዊነት በተመለከተ ቃላቸውን ጠብቀዋል?  በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የሰብአዊ መብት ገፈፋና ረገጣ ያሉትን አድርገዋል? በጭራሽ! ኢትዮ አሜሪካውያንስ ፕሬዜዳንቱ በአክራ (ጋና) የገቡትን ቃል ስላልጠበቁና የሰነዘሩትን የተስፋ ቃል ባለማክበራቸው ቅር ተሰኝተዋል? አስተዳደራቸውስ በኢትዮጵያ በጉልበት ስልጣን ለያዘው ፈላጭ ቆራጩ ዲክታተራዊ ገዢ ድጋፍ ማድረጋቸውስ ኢትዮ አሜሪካውያንን አሳዝኗል? አዎን በሚገባ እንጂ!
    ፕሬዜዳንት ኦባማ ‹‹በአፍሪካ ጠንካራ የሆነ የዴሞክራቲክ ስርአት፤ት የሕግ የበላይ ነት የሚከበርበት፤ለፖለቲካዊ እንቅስቃሴ አድሎ የሌለበትና ሁሉም በእኩል የሚስተናገዱበት መድረክና ሰብአዊ መብትም በእውነተኛ መልኩ የሚተበርበት ኢኒስትቲዩሽን መፍጠር አስፈላጊ ነው›› ማለታቸውን እናስታውሳለን፡፡ ከዚህ ባሻገርም ‹‹አፍሪካ ጡንተኞች አየስፈልጓትም፤ በጉልበት ስልጣን ላይ በመንጠላጠል ማስተዳደርን ወደ መግዛት መለወጥ ባህሪያቸው የሆኑ ሰዎችም አያስፈልጓትም፤ የሚያስፈልጓት ጠንካራ የሆኑ ተቋሞች ነው፡፡›› ልማት ምንግዜም በመልካም አስተዳደር ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ማንም ሃገር መሪ ነን ብለው ስልጣን የተቀመጡት የሕዝቡን ካዝና የሚበዘብዙት ከሆነ ሕዝቡ በምንም መልኩ ሃብት ሊያፈራ ንብረት ሊኖረው አይችልም::  ታዲያ ፕሬዜዳንት ኦባማ እነዚህን አጓጊና የኢትዮጵያ የሌለችም አፍሪካዊያን ናፍቆት የሆኑትን ቃላት ሲናገሯቸው አምነውባቸው ከልባቸው ነው ወይስ ለማለት ብቻ ነው የተነፈሱት?

    Friday, November 2, 2012

    November “Ethiopian Election Massacre” Commemoration Month



    On May 15, 2005, over 26 million Ethiopians voted peacefully to elect their leaders. As the results started to come in, showing a landslide victory for the opposition party, Meles Zenawi went on TV and declared a state of emergency. He also ordered re-votes in several districts where members of his party went down in defeat, banned political rallies, and unleashed his killers against peaceful citizens who protested his attempt to steal the election.

    When the Addis Ababa Police showed restraint, Meles ordered all of them to be disarmed, and gave the Federal Police and his personal army, the Agazi, a shoot-to-kill order.
    The Agazi and Federal Police snipers from roof tops and military trucks gunned down young, hundreds of unarmed protesters with 50 caliber rifles. Over 50,000 students and other individuals were rounded up and sent to concentration camps in remote parts of the country. All senior members of the opposition CUD were arrested. All the private press were shut down. The 2005 election massacre was one of the darkest moments in the history of Ethiopia.

    ከጠ/ሚኒስቴር መለስ ምኑን እንውረስ?



    ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ መሞታቸው ሁሉም ሰው ያሳዘነ ጉዳይ ነው፡፡ ለምን ከተባለ ሁሉም ሰው ከመሞት የሚያመልጥ ባይኖርም
    የአሟሟታቸው ሁኔታ ግን ለየት ባለ ሁኔታ ስለተፈፀመ በጣም ያሳዝናል፡፡ መጀመሪያ በሪፖርተር ጋዜጣ አንድ የመንግሥት ቃለ-አቀባይ መነሻ በሌለው ሁኔታ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ የጤና ችግር የለባቸውም የሚል መግለጫ ሰጠ፡፡ ሰዉየው ይህ ያሉበት ምክንያት ምንድነው? ስለጤናቸው ምን ተብሎ እና ነው ይህን መግለጫ የሰጡ ማለት ጀመረ፡፡ በስተጀርባ አንድ ነገር እንዳለ ጥርጣሬ ውስጥ ገባ፡፡ ቆየት ብለው ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ታመው ህክምና እንደገቡና ህመሙም የሚያሰጋ እንዳልሆነ መግለጫ ተሰጠ፡፡ ቆየት ብለውም በተለይ አቶ በረከት ስምዖን በዕረፍት ላይ መሆናቸው በቅርብ ግዜ ሥራቸው እንደሚጀምሩ መግለጫ ሰጡ፡፡

    ይህ ሁላ ሲሆን ግን አንድ ደ/ር እንኳ ስለየጤንነታቸው ጉዳይ መግለጫ የሰጠ አልነበረም፡፡ ይህ ህዝቡ በበለጠ ጥርጣሬ ውስጥ
    ከተተው፡፡ የታመመ ሰው ስለህመሙ የሚያቅና ሁኔታውን ማብራራት የሚችል ሃኪም ነው ስለ ጠቅላይ ሚኒስቴር የጤንነት ጉዳይ
    የሚነገረን ያለ በመንግሥት ሥልጣን ባሉ ሰዎች ነው ይህንን ነገር እንዴት ነው በማለት ራሱ በራሱ መወያየት ጀመረ፡፡ የሃኪም
    መግለጫ ሳይሰማ ዜና ዕረፍታቸው ተሰማ፡፡ መሞታቸው በጣም አሳዝኖናል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ባህሪያት ለተነሱለት ዓላማ በፅናት የሚተገብሩ ሰው ነበሩ፡፡ የሆነ ሐሳብ አቅርበው ተቀባይነት ካላገኘ ሞተው ይገኛሉ፡፡ በሐሳባቸውና
    በአመለካከታቸው የሚነሱ ልዩነቶች ፍፁም አያስተናግዱም፡፡ ለማስተናገድ ቢሞኩሩም የትም አይደርስም ብለው የገመቱት እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ በዓቅም የሚቀናቀናቸው ሰው አይወዱም፡፡ ብዙ አብነቶች ማቅረብ ይቻላል፡፡ አቶ አርከበ ዕቁባይ አቶ መለስ እንደሚጠሩዋቸው “ጅብ”  ናቸው፡፡ ጅብነታቸው በሥራ ነው፡፡ የትግራይ ም/ፕሬሲዳንት በነበሩበት ጊዜ አንዳንድ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ሲሞኩሩ አዲስ አበባ ወስደው የአዲስ አበባ ከንቲባ ሁነው እንዲሾሙ አደረጉ፡፡ በዚ ጊዜ በተለይ በነጋዴው የአገልግሎት አሰጣጥ ለውጥ ሲያስመዘግቡ ቀለም ከመቀባት የማያልፍ ሥራ ነው የሠራኸው ብለው መዓት ወረዱባቸው፡፡ ከዛ በኋላ የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስቴር ድኤታ ሁነው እንዲሠሩ ተደረገ፡፡ ከዛ በማንሳት ደግሞ አማካሪ ብለው ሰው በማያያቸው (አቅማቸው ህዝቡ በማያየው ዋሻ) እንዲገቡ አደረጉ፡፡ይህ ሁሉ መነሻው ስጋት ነው፡፡ አቶ አርከባ በግልፅ መቃወም አልደፈሩም እንጂ ውስጣቸው ከኛ በላይ የአቶ መለስ በላያቸው ላይ ያደረጉት ዘመቻ ያውቁታል፡፡ በዚህ ቅሬታ ነበር በህወሐት ማእከላዊ ኮሚቴ ለፖሊት ቢሮ ምርጫ አልፈልግም ብለው ራሳቸው ያገለሉት፡፡

    አቶ መለስ በተለይ “ከተሃድሶ” በኋላ እሳቸው እንደአስተማሪ የቀረው ማእከላዊ ኮሚቴ የህወሐት/ኢህአዴግ እንደተማሪ ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ የሚማርበት ሁኔታ ነው የነበረ፡፡ የዚህ ጉዳት በጣም ብዙ ነው፡፡ አቶ መለስ ብቁ ሰው ማፍራት አልቻሉም፡፡ በተለይ በትግራይ፡፡ ወጣቱ ትውልድ ሥልጣን ላይ እንዲወጣ አይፈለግም ለምን አይታመንማ፡፡ ነባሩ ታጋይ ደግሞ እሳቸውን በዓቅም የሚወዳደር አጥላልተው ሞራሉ እንዲነካ ያደርጉታል፡፡ እነ አባይ ፀሃዬ፣ሥዩም መስፍንና አርከበ ዕቁባይ የዚህ አብነቶች ናቸው፡፡
    አቶ መለስ ስልጣን ሙሉ በሙሉ ሳይቆጣጠሩ ጊዜ ያሳዩት የነበረ በህሪ ብዙም አይስተዋልም ነበር፡፡ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች
    ለነበሩ ሰዎች የሚያሳዩትን ስህተቶች ማረም፣ ለህዝብ ተብሎ ሐቅም ቢሆን ህዝቡ ካልተቀበለው ድርጅቱ ተቀብሎ ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅብናል ሲሉ ይስተዋሉ ነበር፡፡ ስልጣን ሙሉ በሙሉ በተቆጣጠሩበት ጊዜ ጀምሮ ግን አንድ ቀንም ህዝቡን ያነሳው ጥያቄ ወይም አንፈልገውም ያለውን ነገር ተቀብለው አያውቁም፡፡ ለምሳሌ፡ የሊዝ አዋጅ መጥቀስ ይቻላል፡፡ ህዝብ ሲቃወም የተቃዋሚ ድርጅቶች ሐሳብ ነው ተብሎ ይፈረጃል፡፡ ያነሳ ሰውም እንዲሁ፡፡ ለስልጣን ብለው ዲሞክራሲ ያፍናሉ፡፡ እስከአሁን የተካሄዱ ምርጫዎች ህያው አብነቶች ናቸው፡፡ የተካሄዱ ምርጫዎች ሁሉም በማጭበርበር እንጂ ህዝቡ በነጻነት ያካሄደው ምርጫ አይደለም፡፡ ህዝቡ የፈለገው ፖለቲካዊ ፓርቲ መርጧል ማለት ፍፁም አይቻልም፡፡እርግጥ ነው በ1997 ዓ.ም ዲሞክራሲ ባልገመቱት ሁኔታ ህዝቡ ተነሳስቶ እነሱን ገፍትሮ የመሰለውን የፖለቲካ ፓርቲ መምረጥ በቅቶ ነበር፡፡ በተለይ የአዲስ አበባ ህዝብ በድፍን ቅንጅትን መርጦ ነበር፡፡ ቅንጅት መከራን ተቀብሎ ህዝብን ለማገልገል ስላልተነሳ የህዝብን ድምጽ መንገድ ላይ ጥሎት ሄደ፡፡ የዚሁ ጠባሳ አሁን የምናየው ያለን ዓይነት ምርጫ እንድናስተናግድ ተገደናል፡፡ ይህም ሆኖ ቅንጅት ሥልጣን ይይዛል ከሚል ፍራቻ ምርጫው ከተካሄደ በነገታው አዲስ አበባ ለኦሮምያ ክልል ተሰጥታለች ብሎ በፓርላማ እንዲታወጅ አገረጉ አቶ መለስ፡፡ ይህ የልጆች ጨዋታ ግን ደግሞ ይቅር የማይባል የታሪክ ስህተት ለምን ተደረገ ብለን ካልን የቅንጅትን ዓቅም ለማዳከም ተብሎ ነበር፡፡ ለዚህ ነው አቶ መለስ ለሥልጣን ብለው የማያደርጉት ነገር የለም ያልነው፡፡ በፍትሕ  በኩል  ስንሄድ፤  ዳኛችና ዓቃቢያነ-ህግ በሙያቸው ባላቸው ብቃት ሳይሆን በፖለቲካ ተአማኒነታቸው ብቻ ነው ዳኛችና ዓቃቢያነ ህግ ሊሾሙ የቻሉት፡፡ ይህ በህዝብ ላይ ከፍተኛ የፍትሕ ዕጦት ፈጥሮ ህዝቡ ዕሪ እያለ ይገኛል፡፡ ሁሉም ነገር አሁን በጉቦ ነው የሚፈፀመው፡፡ ከቀበሌ እስከ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፍትሕ አካላት፡፡ መሬት በካድሬዎች ስለሚስተዳደር እንደፈለጉት እያደረጉት ይገኛል፡፡ በሌሎች የመንግሥት ሥራዎችም ኃላፊነት የሚሰጣቸው በፖለቲካ አባልነታቸው ነው ብቃት፣ትምህርት፣ስራ ልምድ አይሰራም፡፡ 

    ይህ ማንን እየጎዳ ይገኛል ? ህዝብ ነዋ፡፡ ታድያ ህዝብ የሚጎዳ ከሆነ ለምን ተመረጠ ? ለስልጣን ተብሎ፡፡ ስልጣንን ከህዝብ ማስቀደም ማለት ነው? በትክክል፡፡ ሙስናን በሚመለከት፡- ጠ/ሚኒስቴር መለስ ሙስና መዋጋት አይፈልጉም፡፡ ለምን ? በሥልጣን ላይ ያሉ ሰዎች በፈፀሙት ህግ ፊት በማቅረብ ፍርድ እንዲገኙ አይፈልጉም፡፡ ምክንያት፡- 1ኛ. የቀኝ እጃቸው የሆኑ በሙስና የተዘፈቁ በመሆናቸው አሳልፈው መስጠት አይደፍሩም፡፡

    2ኛ. ለቅርብ ወዳጆቻቸው ካላጋለጡ ሌለሎች ማጋለጥ ድፍረት አያገኙም፡፡ በዚህ ምክንያት ከድሃው ህዝብ ብዙ ሚሊዮን የአገሪቱ
    ሃብት ጥቂት ባለሥልጣናት እያግበሰበሰት ይገኛል፡፡ አድልዎ ወገናዊነት በሰፊው ይስተዋላል፡፡ ከዩኒቨርስቲ ተመርቆ የሚወጣው ወጣት በመንግሥትም ይሁን በፖለቲካ ድርጅቶቻቸው ስም የተቋቋሙ የኢኮኖሚ ካምፓኒዎቻቸው ለመቅጠር አንችልም ራስህ ተደራጅተው ሥራ ፍጠር ይሉታል፡፡ ወጣቱም ሌላ አማራጭ ስለሌለው በድንጋይ ጠረባ፣በኮብል ስቶን ሥራ፣በብሎኬት፣በልስን እና በሌሎች የሥራ ዘርፎች ሳይወድ በግድ ያልፍልኝ ይሆናል በሚል ተስፋ ሲንቀሳቀስ ይገኛል፡፡ የባለሥልጣኖች ልጆች ግን በነዚህ የወጣቶች የኢኮኖሚ ድርጅቶች ብለው በሚጠሩዋቸው ድርጅቶች አንድም የለም፡፡ የሚበዙ ውጭ አገር ተምረው በዛው የቀሩ ናቸው ሌሎች ደግሞ ትእምት በሚባል የህወሐት ካምኒ ተቀጥረውና ሃላፊ በመሆን ወፈር ያለ ደመወዝ እየተከፈላቸው የተንደላቀቀ ኑሮ ይኖራሉ፡፡