Wednesday, April 30, 2014

ለወይዘሮሪት ኢህአዴግዬ ሰው ማሰር ሻሽ ሸብ ከማድረግ እኩል ቀላል አይደለምን…


9+ለወይዘሮሪት ኢህአዴግዬ ሰው ማሰር ሻሽ ሸብ ከማድረግ እኩል ቀላል አይደለምን…
ወዳጄ….
በሩቁ የምታውቀው ወዳጅህ ሲታሰር፤ አሳሪዎቹ የሚደረድሩልህ ምክንያት ትንሽ እውነት ሊኖረው ይችላል ብለህ ልታስብ ተችላለህ ከዛ አሳሪዎች መቼም ማሰር አይታክታቸውም አይደል፤ ቀረብ የሚልህ ወዳጅህን ደግሞ ያስራሉ፤ ማሰር ብቻም አይደል ያለ የሌላቸውን ምክንያቶች በቴሌቪዥን በራዲዮ አከታትለው ይነግሩሃል ይሄኔ ግራ ትጋባለህ …መንግስትን ያህል ነገር እንዲህ አይን አውጥቶ ሊዋሽ ይችላል….. ወይስ ወዳጄን በቀጡ አላውቀውም ነበር ብለህ ይምታታብሃል…
የኔ ጌታ አሳሪ ጠዋት ቀበቶውን ካሰረ ሰዓት አንስቶ ሙሉውን ቀን፤ “ደግሞ ማንን ልሰር….” ሲል ነው የሚወለው። እና እያለ፣ እያለ ከራስህ በላይ አውቀዋለው የምትለውን ወዳጅህን ወይም እራስህን ጥርቅም አድርጎ ያስራል። ይሄኔ የፈለግ ምክንያት ቢደረደርልህ አሳሪውን ልታምን እንደማትችል የታወቀ ነው ሀቁ ያለው ራስህ ጋ ነዋ!
እናም ወዳጄ…
በተለይ እንደ ኢህአዴግ ያለ የማሰር ሱስ ያለበት አሳሪ በሩቁ የምታውቃቸውንም በቅርብ የምታውቃቸውንም አስሮ ምክንያት ሲደረድር ወዳጆችህን አተጠራጠር እውነቴን ነው የምልህ መንግስታችን ሰዎችን ሲያስር ጥጃ የማሰር ያክል አይጨንቀውም። ለዚህ ደግሞ አጥጋቢ ምክንያት ሲፈልግ አየገኝም፤ በቃ የአይንህ ቀለም ካላማረው ያስርሃል።
የ ዞን ዘጠኝ ጦማሪዎችን የማውቃቸው ማንም ሰው የታሰረ እነደሆነ መዝገብ አገላብጠው መታሰሩ ከህግ አንጻር፣ ከህገ መንግስት አንጻር፣ ከሞራል አንጻር፤ እያሉ የህሊና ፍርድ ሲሰጡ ነው። ሙስሊም ሳይሉ ክርስቲያን ሳይሉ ኦሮሞ ሳይሉ ጋምቤላ ሳይሉ ያለ ለዩነት ጆሯቸው የደረስ አይናቸው ያየውን ኢፍትሃዊነት ሲያወግዙ ነው። ደግሞ ሲያውግዙ ብቻ አይምሰልህ መንግስት የሚሰራቸው መልካም ነገሮችም እውቅና ሊሰጠው ይገባል፤ ጽንፈኛ መሆን ተገቢ አይደልም ሲሉም ይውቅሱሃል። ዛሬ መንግስት እነዚህን ወጣቶችን ሰባስቦ አስሯቸዋል። (ለወይዘሮሪት ኢህአዴግዬ ሰው ማሰር ሻሽ ሸብ ከማድረግ እኩል ቀላል ነው (በሌላ ቅንፍ ኢህአዴግዬን ወይዘሮሪት ያልኩታ ታግባ አታግባ በቀጡ ሰላላወቅሁ ነው፤ ግራ ስታገባን ግን በድንብ አውቃታለሁ… ሃሃ))

እኔ በአስሩም ጣቴ እፈርማለሁ፤ ዘጠኙም ጋዜጠኞች እና አስተያየት ሰጪዎች የታሰሩት እንደ ሰው በማሰባቸው እና በሀገራችን ጉዳይ ያገባናል በማለታቸው ብቻ ነው!
እንደዚህ የምልህ መንግስት ከሀገሬ አሯሩጦ ስላስወጣኝ ቂም ይዤ አለመሆኑን ድንጋይ ነክሼ እምልልሃለሁ!

No comments:

Post a Comment