Thursday, July 25, 2013

ዜና መጽሐፍ፤ ፕሮፌሰር መስፍን የግጥም መጽሐፍ እነሆ አሉን!


እንጉርጉሮዜና መጽሐፍ፤  ፕሮፌሰር መስፍን የግጥም መጽሐፍ እነሆ አሉን!
በመጀመሪያም፤
እኒህ ሰውዬን የሚያክል ብርቱ መቼም ኢትዮጵያችን ያላት አይመስለኝም፡፡ ሁሉም ነገር ይቅርና ጎረምሶቹን ፖለቲከኞች እና ምሁሮች በሚያስከነዳ ትጋት፤ በየወቅቱ ሀሳባቸውን ሳይታክቱ በመፃፍ ያጋሩናል፡፡ በየአመቱም የመፅሀፍ በረከታቸውን ያድሉናል፡፡ በእውኑ እንደርሳቸው ያለ ማን አለ… ብለን በማድነቅ ዜናችንን እንጀምራለን!
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም “ዛሬም እንጉርጉሮ” በሚል ርዕስ አዲስ የግጥም መፅሀፍ ማሳተማቸውን ከወደ ፊኒፊኔ የደረሰን ወሬ ያስረዳል፡፡ ፕሮፍ እንዲህ ይሉናል፤
“እንጉርጉሮ በመሰረቱ የግል ነው ለአንባቢ የተዘጋጀ አይደለም ማለት ነው፡፡ አንድ ሰው ከገዛ ራሱ ስሜት ጋር የሚያደርገው ትግል ነው፤ ራሱ፤ ራቁቱን እውነቱን የሚያይበት መስተዋት ነው፤ ቢሆንም የሰው ሁሉ መሰረታዊ ስሜት አንድ አይነት በመሆኑ ተመሳሳይ አጋጣሚ ተመሳሳይ ስሜት ሊፈጥር ይችላል፤ ከዚያ በቀር አንድ ሰው የጠቅላላ ህብረተሰቡ ደስታ እና ምቾት፤ ስቃይ እና ጭንቀ፤ ተስፋ እና ምኞት ተካፋይ መሆኑ በጥልቅ ከተሰማው በእምነት የግል በሆነ መንገድ ያንን ጥልቅ የሆነ ስሜት እንደ ህብረተሰቡ ሆኖ ሊያስተጋባ ይችላል፡፡ የእኔ ሙከራ ተሳክቶ እንደሆነ እና አንዳልሆነ መፍረዱ የአንባቢዎች ፈንታ ነው፡፡”
ታድያ የፈራጅነት ሚና ሰጥተውን ያበረከቱልንን ይቺን የግጥም መጽሐፍ ገዝተን፤ ግጥም አድርገን ብንጠጣት እና ብንፈርዳቸው ምን ይለናል፡፡ ምንም!
በመጨረሻም፤
በውጪ ሀገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዛሬም እንጉርጉሮ እንዴት እንደምናገኛት ጠይቄ እነግራችኋለሁ፡፡

No comments:

Post a Comment