Friday, December 14, 2012

የሰንደቅ ሙሉ ዘገባ

 

 
ሰንደቅ ጋዜጣ ረቡዕ ታህሳስ 3 /2005 ዓ.ም
አንድነት ፓርቲ ሹም ሽር ያደርጋል
አቶ ስዬ አብርሃ ማስጠንቀቂያ ሊሰጣቸው ይችላል
 
በዘሪሁን ሙሉጌታ
 

የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት) ብሔራዊ ምክር ቤት በመጪው እሁድ በሚያካሂደው መደበኛ ስብሰባ በአራት ቁልፍ አጀንዳዎች ላይ ውይይት በማድረግ በፓርቲው አጠቃላይ እንቅስቃሴ ላይ ድክመት ባሳዩ አመራሮች ምትክ ሌሎች እንደሚመርጥ ለም/ቤቱ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለፁ።

በተመሳሳይ ለአንድ ዓመት ትምህርት ለመማር ወደ አሜሪካ የሄዱት የፓርቲው የብሔራዊ ም/ቤት አባል የሆኑት አቶ ስዬ አብርሃ ም/ቤቱን ለአንድ ዓመት አስፈቅደው ቢሄዱም በተደጋጋሚ ጊዜያት በም/ቤቱ ስብሰባ ላይ አለመገኘታቸው የም/ቤቱን አባላት አሳስቧል። በፓርቲው ሕገ-ደንብ መሠረት በፓርቲው የብሔራዊ ም/ቤት ስብሰባ ላይ ለሦስት ተከታታይ ስብሰባዎች አለመገኘት ከም/ቤቱ አባልነት የሚያሰርዝ መሆኑ እየታወቀ አቶ ስዬ አብርሃ ያለበቂ ምክንያት በፓርቲው እንቅስቃሴ ውስጥ አለመገኘታቸው በአንዳንድ የም/ቤቱ አባላት ዘንድ ቅሬታ ፈጥሯል።

ፓርቲው ባስቀመጠው የአምስት ዓመት የስትራቴጂ እቅድን ከመተግበር ባለፈ በፓርቲው ሊቀመንበር የተዋቀረው የካቢኔ አባላት ሁሉም በሙሉ ኃይላቸው የፓርቲውን የዕለት ተዕለት ተግባር ማከናወን ባለመቻላቸው ከፍተኛ የስራና የአፈፃፀም ድክመት መታየቱ የም/ቤቱን አባላት በሰፊው ያወያያል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ቀደም ሲል ከፓርቲው በክብር ተሰናብተው የነበሩት ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራሁ እና የቀድሞው የአዲስ አበባ ወጣቶች ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ አባል የነበረው እና “ባለራዕይ የወጣቶች ማኅበር” ሊቀመንበር ወጣት ሐብታሙ አያሌው የፓርቲውን የአባልነት መስፈርቶች ሳያልፍ የፓርቲው ከፍተኛ የስልጣን አካል ወደሆነው የብሔራዊ ም/ቤት አባል ቢሆኑም ወደ አመራርነት ሊመጡ የሚችሉበት ሁኔታ እንደሚፈጠር ከም/ቤቱ አካባቢ የሚወጡ መረጃዎች እየጠቆሙ ነው።

አንድነት ስየን ሊሰርዝ ወይም ሊያስጠነቅቅ ይችላል

 

የተሃድሶው ጅማሬ ይሆን?
 
 
udj
 
በነባር አመራሮች ሲንከባለል የኖረው “የቅንጅት ወራሽ” አንድነት ፓርቲ ኃላፊነቱንና አመራሩን ለተተኪ ሳያስረክብ መቆየቱ በአብዛኛው ትችት ሲያሰጥ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ በተለይም አቶ ስየ አብርሃ ፓርቲውን በተቀላቀሉ ማግስት በከፍተኛ ኃላፊነት መሰየማቸው አልተወደደለትም ነበር፡፡ በአንድነት ፓርቲ ውስጥም እስከመከፋፈል የዘለቀ ልዩነት መፍጠሩ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡
አሁን የረገበ የሚመስለው የፓርቲው የውስጥ ልዩነት፤ በወቅቱ “ዝም አንልም፤ መርህ ይከበር” የሚሉት ኃይሎች የወሰዷቸውን ጽንፈኛ አቋሞች ብዙዎች የሚደግፉት ባይሆኑም ያነሱትን ጥያቄ አግባብነት ግን ይቀበላሉ፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ይሁን በሌላ የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ሊመንበር የነበሩት ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም “እኛ የማማከር አገልግሎት መስጠት አለብን፤ አመራሩን መያዝ ያለበት አዲሱ ትውልድ ነው” በማለት ራሳቸውን በቅሬታ ከፓርቲው ማግለላቸው ይታወሳል፡፡
በአሁኑ ሰዓት አሜሪካ የሚገኙት ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳም ከፓርቲው ጋር ያላቸው ግንኙነት በይፋ በሚታወቅ ደረጃ ላይ አይገኝም፡፡ እርሳቸውን ተከትለው ወደ አሜሪካ የመጡት አቶ ስየም በተየያዩ የአሜሪካ ግዛቶች በፓርቲው ስም ንግግር ሲያደርጉና የራሳቸው እምነት ሲያንጸባርቁ የሚታዩትን ያህል ወ/ት ብርቱካን ከአንድነት ጋር በተቆራኘ ጉዳይ መድረክ ላይ አለመታየታቸው ከፓርቲው ጋር ያላቸውን ግኑኘነት ግልጽ እንዳልሆነ አመላካች ነው፡፡ ወ/ት ብርቱካን ወደ አሜሪካ ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ በአጠቃላይ ከትግሉ ጎራ እንዳልራቁ ቢናገሩም ሲመሩ የነበሩትን ፓርቲ በተመለከተ ዝምታን መምረጣቸው የዳያስፖራውን የፖለቲካ ትግል ይመራሉ ብሎ ተስፋ በጣለባቸው ደጋፊያቸው ዘንድ ይፋ ያልወጣ ግን በብዛት ያነጋገረ ጉዳይ ነው፡፡

ሱዛን ራይስ የቤንጋዚው መዘዝ ሰለባ ሆኑ!

 

ራሳቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚ/ር እጩነት አገለሉ
 
 
susan rice
 
በተባበሩት መንግሥታ የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑትና በፕሬዚዳንት ኦባማ ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት የውጭ ጉዳይ ሚ/ር መስሪያቤትን እንዲመሩ ሊታጩ ይችላሉ የተባሉት ቀዳሚ ተወዳዳሪ ሱዛን ራይስ ራሳቸውን ከእጩነት አግልለዋል፡፡ ጉዳዩ ለፕሬዚዳንቱ የፖለቲካ ክስረት፤ ምርጫውን ሲቃወሙ ለነበሩት የሪፓብሊካን ፓርቲ አመራሮች እና በአሜሪካ ለሚገኙ ኢትዮጵያውን ታላቅ ድል ሆኗል፡፡
በቅርቡ በተጠናቀቀው የአሜሪካ ምርጫ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለሁለተኛ ጊዜ መመረጣቸውን ካረጋገጡ በኋላ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ሱዛን ራይስ ሂላሪ ክሊንተንን እንደሚተኩ በሰፊው መነገር ተጀመረ፡፡ የፕሬዚዳንቱ ቀዳሚ እጩ መሆናቸው ብዙ ቢነገርላቸውም ከተቃዋሚዎቹ የሪፓብሊካንና ሌሎች ጉዳየኞች የተቃውሞ ድምጽ ለመስማት ግን ብዙም ጊዜ አልወሰደም፡፡
ክሪስቶፈር ስቲቨንስ
መስከረም 1፤ 2005ዓም በሊቢያ ቤንጋዚ ከተማ የአሜሪካ ቆንስላ እና አምባሳደር ላይ የደረሰውን ጥቃት አስመልክቶ ሪፓብሊካኑ የመቃወሚያ ክሳቸውን ማሰማት ጀመሩ፡፡ በወቅቱ በደረሰው ጥቃት በሊቢያ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት ክሪስቶፈር ስቲቨንስ እና ሌሎች ሦስት አሜሪካውያን የቆንስላው ሠራተኞች ተገድለው ነበር፡፡
ግድያው ከተፈጸመ ጥቂት ቀናት በኋላ በአሜሪካ በሚገኙት አምስት ዋና ዋና የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በመቅረብ ድርጊቱ የአሸባሪዎች ጥቃት ሳይሆን በካሊፎርኒያ የተሠራ ጸረ-እስላማዊ ቪዲዮ ምክንያት የተጫረ ነው በማለት አምባሳደር ራይስ ለኦባማ አስተዳደር መከላከያ አቀረቡ፡፡ ምርጫ ሊካሄድ ሁለት ወር ሲቀር የተከሰተው ይህ ድርጊት የምርጫ ፉክክር ውስጥ ለነበረው የኦባማ አስተዳደር ከፍተኛ የፖለቲካ ኪሣራ እንደሚያመጣ የተገመተው አስቀድሞ ቢሆንም የአምባሳደሯ መከራከሪያ ሁኔታውን ሊያለዝብ ችሎ ነበር፡፡

Wednesday, December 12, 2012

ይድረስ ለሟች የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ (ጉዳዩ-ስልጣን እንዲያስረክቡ ስለመጠየቅ)

ይድረስ ለሟች የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ (ጉዳዩ-ስልጣን እንዲያስረክቡ ስለመጠየቅ)

Zenawi-Burial

ሲመረን እና ስናመር!!!

ግልጽ ፖስት ይድረስ ለሟች የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ጉዳዩ-ስልጣን እንዲያስረክቡ ስለመጠየቅ

አቶ መለስ – እኔ በፍጹም እርሶን ካረፉበት የመቀስቀስም ሆነ የማስቸገር እቅድ የለኝም ነበር፡፡ ነገር ግን አሁን ሳስበው የቅርብ ወዳጀችዎም እረፍት ስላልሰጦት እኔም ይህንን መልእክት ባስተላልፍ ቅር አይሎትም ብዩ ተነሳሁ፡፡ መቼም ባሉበት ሆነው ከፓርቲዎ እስከ ሚዲያው ድረስ ስምዎ ሲነሳ መዋሉ በስቅታ ሳይገሎት አይቀርም፡፡ አኔና እርሶ ያን ያህል አንተዋወቅም (ሆሆይ በየት በኩል………..)፡፡ እንኳን አሁን ሞተው ቀርቶ ኖረውም ቢሆን እኔን አንዲትዋን ህዝብ የሚሰሙበት ምንም አይነት አመል አልነበሮትም፡፡ እነደው ድንገት ከሞት በኋላ ባለው ህይወት ተቀይረው ከሆነ ለእርሶ ባይሆን ለሰዎችዎ ይጠቅም ይሆናልና እባክዎ ጆሮዎን ያውሱኝ፡፡

እንግዲህ እለእርስዎ የሚወራውን ስመለከተው በቅርቡ “አቶ መለስ ገነት ገብተዋል፡፡ ስማቸወም ለመለስኤል ተብሏል” የሚል የኢቲቪ ዜና ይመጣል ብዩ እየተሳቀቅኩ እገኛለሁ፡፡ በመሆኑም እንዲህ አይነቱ የእርሶንም በህይወትም ሆነ በሞት የሚያስችግር ነገር አሁንም ካሉበት ሆነው አንድ ይሉልኛል ብዩ ይህንን መልእክት ለጠፍኩ፡፡ ለመሆኑ በዜናው በሬዲዮኑ ጋዜጣው እና ሌላው ሁሉ ላይ እርሶ ሲያወሩ እንደሚውሉ አውቀዋል፡፡ እርሶ ያልተናሩበት ቲቪ፣ ያላወሩበት ሬዲዮ፣ የሌሉበት ስብሰባ ከጠፋ ሰነበተ፡፡ በህይወት እያሉ ከመሩት (አንደኛውን እሱ ይሻል ነበር) በላይ ከሞቱ የመሩት እየበለጠ ተቸግረናልና እባክዎ ስልጣኖን ያስረክቡልን፡፡ የተፈጥሮ ግዴታ ከወንበሮ ቢያነሳዎትን ሰልጣኖን ለመረከብ የሚችል ስለጠፋ ከሞት በኋላም አለማረፎ በጣም አሳዝኖኛል፡፡ እርሶን ብቻ ነውና የሚሰሙት “እበካችሁ ራሳችሁን ችላችሁ ምሩ፣ ራሳችሁን ሁኑ፣ ምንም ሆነ ምን የራሳችሁን ታሪክ ለመጻፍ እድሉን ተጠቀሙበት” በሉልን፡፡ እንዴት ነው ነገሩ? ለሰርሶም ስም ቢሆን “በህይወት እያለ 21 አመት ከሞተ በኋላ —–አመት የገዛ መሪ” መባል ለስሞ ጥሩ አይደለም፡፡ (እነዲሁም ቢኖር ስልጣኑን አይለቅም ነበር የሚለው ሃሜት ማጠናከር ይሆንቦታል፡፡)

የኦነግ አባል ሆነዋል” በሚል በተከሰሱት በቀለ ገርባ፣ ኦልባና ለሊሳ፣ ወልቤካ ለሚን ላይ ተፈረደባቸው

የኦነግ አባል ሆነዋል” በሚል በተከሰሱት በቀለ ገርባ፣ ኦልባና ለሊሳ፣ ወልቤካ ለሚን ላይ ተፈረደባቸው

 
Free Bekele Garba and Olbana Lellisa

የመንግስት ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት “ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲን ሽፋን በማድረግ የአሸባሪቡድን የሆነው ኦነግ አባል ሆነዋል” በሚል በተከሰሱት በአቶ በቀለ ገርባ የክስ መዝገብ ውስጥሚገኙ ግለሰቦች ላይ ፍርድ መስጠቱን የዜና ዘጋቢዎች ከአዲስ አበባ አመለከቱ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪው አንደኛ ተከሳሽ አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ኦልባና ለሊሳ ፣ ወልቤካ ለሚ ፣ አደም ቡሳ ፣ ሀዋ ዋቆ ፣ መሀመድ ሙሉ ፣ ደረጀ ከተማ ፣ አዲሱ ሞክሬና ገልገሎ ጉፋ የቀረበባቸው ክስ “የኦሮሚያ ክልልን ከፌዴሬሽኑ ለመገንጠል ፣ የአሸባሪ ቡድን የሆነው ኦነግ አባል በመሆንና ኬኒያ ድረስ በመሄድ ወታደራዊ ስልጠና በመውሰድ” የሚሉ መሆናቸውን ዘጋቢዎች ጠቁመው ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ከመስጠቱ አስቀድሞ ተከሳሾቹ ለፍርድ ቤቱ የተለያዩ የፍርድ ማቅለያዎችን ማቅረባቸውን ዘግበዋል። በዚህም መሠረት በመንግስት አቃቤ ሕጎች “የአሸባሪነት ክስ” በቀረበባቸው ላይ አንድም ጊዜ በነጻ ፈትቶ የማያውቀው በሚል የሚተቸው ፍርድ ቤቱ በተከሳሾቹ ላይ የሰጠው ፍርድ የሚከተለው ነው። 1ኛ. አቶ በቀለ ገርባ – በ8 ዓመት እሥር 2ኛ. ኦልባና ለሊሳ – በ13 ዓመት እስር 3ኛ. ወልቤካ ለሚ – በ7 ዓመት እስር 4ኛ. አደም ቡሳ – በ3 ዓመት እስር፣ 5ኛ. ሀዋ ዋቆ – በ8 ዓመት፣ 6ኛ. መሀመድ ሙሉ- በ 10 ዓመት እስር 7ኛ. ደረጀ ከተማ – በ8 ዓመት እስር፣ 8ኛ. አዲሱ ሞክሬ – በ10 ዓመት እስር 9ኛ ገልገሎ ጉፋ – በ12 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ወስኗል። በተጨማሪም ተከሳሾቹ ከሁለት እስከ አራት ዓመት ለሚደርስ ጊዜም ህዝባዊ መብታቸው ፍርድ ቤቱ መሻሩም ታውቋል። በቀለ ገርባ በተለይ ከአቶ ቡልቻ ደመቅሳ በኋላ የኦፌዴን ፓርቲን ጥሩ ተፎካካሪ ያደርገዋል ተብሎ የሚጠበቅ መምህር ነበር ሲሉ የሚያውቁት ይናገራሉ። መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ተደብቆ ተገኘ በተባለው መትረየስ እና ባዶ ሠንሰለት ምክንያት “የተንኮል ድርጊቶችን ግዙፍ በሆነ ዓይነት ማሰናዳት ወንጀል” በሚል ክስ ጭምር የተከሰሱት 9ኛው ተከሳሽ ገልገሎ ጉፋ ከ1984 እስከ 2002 ዓ.ም የኦነግ አመራር አካል የነበሩ ሲሆን በ2002 ዓ.ም ግን ከሌሎች ከኦነግ አባላት ጋር ሆነው እጃቸውን ለመንግሥት ሲሰጡም የኦነግን ዓላማ ኮንነው ሃገር ቤት የገቡ መሆናቸው ይታወሳል።

 

ከአእምሮ ባርነት ነጻ እንውጣ!

 

(መክብብ ማሞ)

emancipation from mental slavery

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በተደጋጋሚ የተሃድሶን አስፈላጊነት በሚያወጡት ርዕሰአንቀጽ ላይ አስነብበውናል፡፡ ባለፈው ጊዜ “ከፖለቲካ ተሃድሶ በፊት [የእውቀት] ተሃድሶ በአስቸኳይ!!” በሚል ርዕስ የተሃድሶን ጥቅምና አስፈላጊነት አስታውቀውናል፡፡ በቅርቡ ደግሞ “የተሃድሶ ያለህ!!!” በማለት በድጋሚ የሰሚ ያለህ ብለውናል፡፡ እኔም ይህንን በሙሉ ልብ የማምንበትን ሃሳብ በማንሳታቸው ላመሰግናቸው እወዳለሁ፡፡ በዚሁ ርዕስ ዙሪያ “ከአእምሮ ባርነት ነጻ እንውጣ” በሚል ሃሳቤን እንደሚከተለው አቅርቤአለሁ፡፡

ከአእምሮ ባርነት ነጻ እንውጣ

የሰውን ልጅ “ሰው” ከሚያሰኙት መካከል ማንነቱን የሚወስኑት የአካላዊ፣ የአእምሯዊና የመንፈሣዊ ኃይላት ውጤት መሆኑ በዋንኛነት ተጠቃሽ ነው፡፡ እነዚህ ዕድገታቸውን በተመጣጠነ መልኩ ካልተጠበቀ የሰው ልጅ “ሰው” ተብሎ ቢጠራና ራሱንም “ሰው ነኝ” እያለ ቢኖርም ከ“ሰው”ነት ተራ የወጣ ለመሆኑ ራሱ ምስክር ነው፡፡

የእነዚህ ኃይላት ተመጣጥነው አለማደግ ሰውን ለብዙ ዓይነት ችግር ይዳርጉታል፡፡ ተምሮ ለድንቁርና፤ ባለጸጋ ሆኖ ለመንፈሣዊ ድህነት፤ ነጻ ሆኖ ለባርነት፤ … ይዳርጉታል፡፡ ከባርነትም የአእምሮ ባሪያ መሆን ትልቁ ጭቆናና ውርደት ነው፡፡

የአእምሮ ባሪያ የሆነ ነጻነቱን የሚጎናጸፍበት በርካታ መንገዶች ቢኖሩም የዕውቀት ተሃድሶ ማድረግ ቀዳሚው ነው፡፡ የዕውቀት ተሃድሶ ለማድረግ ትምህርት ቤት መግባት አያስፈልግም – እዚያ የሚሰጥ ትምህርት አይደለምና፤ የዲፕሎማና የዲግሪ ክምችት አይሻም – በሥርዓተ ትምህርት ውስጥ የተቀረጸ ኮርስ አይደለምና፤ … የዕውቀት ተሃድሶ ለማድረግ ከሁሉ በላይ ቅንነት እና እውነተኛነት ያስፈልጋል፡፡

አልአሙዲ ያጠሩትን መሬት ተነጠቁ

 

huda mexico bldg

 የሼክ መሐመድ ሁሴን አልአሙዲ ኢንቨስትመንት ላይ ጥያቄ ያላቸው ጥቂት አይደሉም። የራሳቸውን ህንጻ ከመጨረስ ይልቅ በኪራይ አንድ ህንጻ የሚያሰራ ገንዘብ ለዓመታት ሲከፍሉ ማየትና መስማት የተለመደ ነው። የንግድ ሰዎች ይህንን ዝንባሌያቸውን ከነጋዴ የሚጠበቅ እንዳልሆነ ይናገራሉ። በዙሪያቸው ተሰባስበው ያሉትም ቢሆኑ አመቺ ቦታ ሲያገኙ በዚሁና በሌሎች ጉዳዮች ያሟቸዋል።

ናኒ ህንጻ

ጊዮን ሆቴል አጠገብ የተሰራው የናኒ ህንጻ ሲጀመር የተወለደ ህጻን አስራ ሁለት ዓመት ሲሞላው ነው ያለቀው። ከጊዮን ሆቴል ፊትለፊት ለአስራ ሁለት ዓመት ለህንጻው መጋዘን ሆኖ ሲያገለግል የነበረው የአዲስ አበባ ስታዲየም የመኪና ማቆሚያ ተገቢው ክፍያ ሳያገኝ ቢኖርም የሳቸውን ፎቶ በስታዲየም ውስጥ ለመለጠፍ ቀዳሚ ነው። አሁን መለስ መጡና አሳነሷቸው እንጂ ስታዲየሙ የእርሳቸው የሚመስልበት አጋጣሚም ነበር።