Saturday, September 28, 2013

ሀገር ማለት


(ሠዓሊ አምሣሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

faces-of-ethiopia


በዚህ ርእሰ ጉዳይ ላይ አስቀድሞ ደራሲ በዓሉ ግርማ በኋላም ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ ግጥሞቻቸውን ጽፈው ነበር፡፡ ሌላም የጻፈ ይኖራል፡፡ ነገር ግን እነኝህ የሥነ-ጽሑፍ ሰዎች ግጥሞቻቸውን ሲጽፉ የተቆነጸለ ወይም የተሳሳተ ትርጉም ሊያሰጥ በማያስችል ሁኔታ ግጥሞቻቸውን ባለመጻፋቸው እንደምገምተው እነሱም ሊሉ ባልፈለጉት መንገድ ተተርጉሞ የቅጥረኞች መጠቀሚያ እስከመሆን ድረስ በቃና ሕዝብን ለማደናገሪያ አገለገለ፡፡ ከሕዝቡ ጥቂት የማይባል ወገንም በመወናበድ ይሄንን የተሳሳተ ትርጉም ይዞ ማንጸባረቅ ያዘ፡፡  ይህም መሆኑ ሀገር በሕዝብ ልብ ውስጥ የነበራት ቦታና ትርጉም ከመዛባቱም ባሻገር በወደፊት የሀገር ህልውና ላይ ከባድ አደጋ የጋረጠ  ሆኖ ቁጭ አለ፡፡ እናም እንደዜጋ አሳሰበኝና ይሄንን የተሳሳተ ትርጉም ለማረም የሀገርን ትርጉም ሳይቆነጸል ሳይጎነጠል ለማስፈር ተገደድኩና ይህችን ግጥም ጻፍኩ፡፡  ግጥሙ እንዳልኩት የሀገርን ምንነትና ሙሉ ትርጉም ለማስቀመጥ ሲባልና ሁሉም ሰው ሊገባው ሊረዳው በሚችል አገላለጽ ሲገለጽ ትንሽ ሊረዝም ችሏል፡፡ ለዚህ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ በግጥሙ ላይ የተገለጹትን ተግሳጾችንና ስድቦችን ሁሉንም በግጥሙ ላይ ከተወከለው ገጸ ባሕርይ ተውሻለሁ ለራሱ ለባለቤቱ መመለስ ይኖሩባቸዋልና፡፡

የልማት መጀመሪያው ሰብዓዊ መብትን ማክበር ነው!


ሞረሽ ወገኔ (ብሪታኒያ) የተሰጠ መግለጫ

Moresh


የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ::

Friday, September 27, 2013

ስበር ዜና – አንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ታሰሩ!

September 27, 2013


የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ዛሬም ታግተው ወደ አራዳ ፓሊስ ጣቢያ ተወስደዋል፡፡ አብረዋቸው የታሰዩት አመራሮችና አባላት እንደሚከተለው 
እንዘረዝራለን !
Millions of voices for freedom - UDJ
በፖለስ የታሰሩ አመራሮችና አባላት በከፊል
ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ – የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር
የተከበሩ ግርማ ሰይፉ – የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር
አቶ ስዩም መንገሻ – የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ
አቶ ዳንኤል ተፈራ – የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
አቶ አስራት ጣሴ – ዋና ጸሃፊ
አቶ ተክሌ በቀለ – የፋይናንስ ጉዳይ ኃላፊ
አቶ ሽመልስ ሃብቴ – የማህበራዊ ጉዳይ ኃላፊ
አቶ ሃብታሙ አያሌው – የህዝብ ግንኙነት ም/ኃላፊ
አቶ ብሩ በርመጂ – የብሔራዊ ምክር ቤት አባል
አቶ አበበ አካሉ – የብሔራዊ ምክር ቤት አባል
አቶ እንግዳ ወ/ፃዲቅ – የብሔራዊ ምክር ቤት አባል
አቶ አለባቸው ነጋሽ – አባል
አቶ መካንንት ብርሃኑ – አባል
አቶ እንዳልካቸው ባዩ – አባል
አቶ ብስራት ተሰማ – አባል
አቶ ወንደሰን ክንፉ – አባል
አቶ ኃይሉ ግዛው – አባል
አቶ ደረጀ ጣሰው – አባል
አቶ ገዛህኝ – አባል
አቶ ባዩ ተስፋዬ – አባል
አቶ ወርቁ – አባል

Thursday, September 26, 2013

ሰማያዊ ፓርቲ ሕገ-መንግስት አረቀቀ

‘‘የአሁኑ ሕገ-መንግስት የኢህአዴግ ፕሮግራም ቅጂ ነው’’ ኢንጂነር ይልቃል

semayawi 12


በቅርቡ የተመሰረተው የሰማያዊ ፓርቲ ‘‘የዜጎች የቃል ኪዳን ሰነድ ለዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ’’ በሚል መርህ ወደፊት የፖለቲካ ሥልጣን ሲይዝ የሚመራበትን አዲስ ህገመንግስት ማርቀቁን አስታወቀ። ረቂቅ ሰነዱ ላይ ምሁራንና ባለሙያዎች ውይይት ካደረጉ በኋላ ለሕዝብ እንደሚቀርብ ፓርቲው አስታውቋል።
የፓርቲው ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት በአዲሱ ረቂቅ ሕገ-መንግስት ላይ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ውይይት እንደሚደረግ አስታውቀዋል። በውይይቱ ላይ ከዚህ በፊት የነበሩ ሦስት ህገ-መንግስቶች ድክመትና ጥንካሬ ምንድን ነው? አዲስ በሚረቀቀው ህገ-መንግስት ምሰሶዎች ምን ይሆናሉ፣ ስልጣንና ሕዝብን እንዴት ማገናኘት ይቻላል በሚሉ ወሳኝ ንድፈ ኀሳቦች ላይ የጠለቀ ውይይት እንደሚደረግ አስታውቀዋል።
‘‘የአሁኑ ሕገ-መንግስት የኢህአዴግ ፕሮግራም ቅጂ ነው’’ ያሉት ኢንጂነር ይልቃል እያረቀቁ ያሉት ሕገመንግሥት የሰነድ ዝግጅቱም ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁንና ምሁራን በሚያደርጉት ውይይት ከዳበረ በኋላ ለሕዝቡ ውይይት ቀርቦ ለባለሙያዎች ተመርቶ ዝርዝር ህጎች እንዲፃፉ ይደረጋል ብለዋል።
ፓርቲው ሰላማዊ ሰልፍ የሚያካሂደው ሕዝቡን ለማነቃቃትና ለማስተማር አባላትንም ለመመልመል ቢሆንም በተጓዳኝ ፓርቲውን ለማጠናከርና ምን አይነት ስርዓት እንገነባለን የሚለውንም ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም ኢንጂነር ይልቃል ገልፀዋል።
ሰማያዊ ፓርቲ ሕገ-መንግስት ባለበት ሀገር ሌላ ሕገ-መንግስት ከማውጣት የሚያግደው ነገር እንደሌለ የጠቀሱት ኢንጂነር ይልቃል፤ ፓርቲው እያካሄደ ያለው ትግል በሕገ-መንግስት የማይመራን አገዛዝ በዲሞክራሲያዊ ስርዓት የመተካት ስለሆነ አዲስ ህገ-መንግስት ማስፈለጉ የግድ ነው ብለዋል።
የፓርቲው ዋና አላማ በሀገሪቱ ሕጋዊ ስርዓትን መትከል በመሆኑ አሁኑ ባለው ሕግ-መንግስት በሚደረግ ምርጫ አብላጫ ወንበር ማግኘቱን ሲያረጋግጥ አዲሱን ሕገ-መንግስት ተግባራዊ ያደርጋል ብለዋል። በዚህ ሀገር ምርጫ ከተካሄደም ሰማያዊ ፓርቲ 99.6 በመቶ አብላጫ ወንበር ለማግኘት የሚያግደው ነገር እንደሌለም እርግጠኞች ነን ሲሉ አያይዘው ገልፀዋል።

“ወሲባዊ ጂሃድ (ጂሃድ አል-ኒቃ)” በሶሪያ!


ሳዑዲ ሞት የፈረደችባቸውን ወደ ሶሪያ አዝምታለች

tunisian girls


የቱኒዚያ ሴቶችና ልጃገረዶች በሶሪያ የአሳድን መንግሥት እየተፋለሙ ከሚገኙት እስላማዊ አማጺያን ጋር “ወሲባዊ ጂሃድ” በመፈጸም በጦርነቱ ላይ ተሳትፏቸውን እየገለጹ መሆናቸው ተነገረ፡፡ በሌላ በኩል በዚሁ ጦርነት ላይ በሳውዲ አረቢያ የሞት ፍርድ የተበየነባቸው ወንጀለኞች እንዲሳተፉ እየተላኩ መሆናቸው ተረጋገጠ፡፡
በያዝነው የመስከረም ወር መጀመሪያ አካባቢ የቱኒዚያው የአገር ውስጥ ሚኒስትር ሎትፊ ቢን ጄዱ በአገሪቱ ፓርላማ ፊት ቀርበው እንደተናገሩት በጦርነቱ ከፍተኛ መስዋዕትነት እየከፈሉ ለሚገኙት ተዋጊዎች ማደፋፈሪያ እንዲሆንና በትግሉ የነርሱንም ድርሻ ለመወጣት የቱኒዚያ ሴቶችና ልጃገረዶች ራሳቸውን በ“ወሲባዊ ጂሃድ” በመስጠት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትር ሎትፊ ቢን ጄዱ (ፎቶ: አልጃዚራ)
ሚኒስትር ሎትፊ ቢን ጄዱ (ፎቶ: አልጃዚራ)
በአረቡ ዓለም በሚገኙ የዜና ማሰራጫዎች በሰፊው የተዘገበው ይህ ዜና እንደሚያስረዳው ሚኒስትሩ ጉዳዩ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ጠቁመዋል፡፡ “እነዚህ ሴቶች” አሉ ሚኒስትር ቢን ጄዱ “እነዚህ ሴቶች (ሶሪያ በሚቆዩበት ጊዜ) ከ20፣ 30፣ 100” አማጺያን ጋር በመተኛት የወሲብ “አገልግሎት” ይፈጽማሉ፡፡  “ወሲባዊ ግንኙነቱንም የሚያደርጉት በ“ጂሃድ አል-ኒቃ” (ማለትም ወሲባዊ ቅዱስ ጦርነት) ስም ሲሆን ወደ ቱኒዚያ የሚመለሱትም እርጉዝ ሆነው ነው” በማለት ሚኒስትሩ ለተከበሩት የፓርላማው አባላት በግልጽ አብራርተዋል፡፡
ከጂሃዲስቶቹ ልጅ አርግዘው የሚመጡት ሴቶች ቁጥር ምን ያህል እንደሆነ ሚኒስትሩ አልጠቆሙም፡፡ ሆኖም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሴቶች በጉዳዩ ላይ እንደሚሳተፉ ከዚህም በተጨማሪ ከ3ሺህ በላይ ቱኒዚያውያን የአማጺያኑን ኃይል ለመደገፍ እንደዘመቱ ይነገራል፡፡ ይህ የቱኒዚያውያኑ ቁጥር በአሳድ ላይ ጂሃድ በማወጅ የሶሪያን አማጺዎች ከተቀላቀሉት የሌላ አገር ዜጎች ከፍተኛውን ቁጥር የያዘ ነው፡፡
ሚኒስትሩ እንደሚሉት ከሆነ እርሳቸው ሥልጣን ከያዙ ካለፈው ዓመት መጋቢት ወር ጀምሮ “ስድስት ሺህ ያህል ወጣቶች በሶሪያ የእርስበርስ ጦርነት እንዳይሳተፉ ለመከልከል” መቻሉን ለፓርላማው አስረድተዋል፡፡ አል አረቢያ ሚኒስትሩን ጠቅሶ እንደዘገበው የቱኒዚያን ድንበር በማቋረጥ ወደ ሶሪያ ለመዝመት የሚፈልጉ ወጣቶችን ለመከላከል በቱኒዚያ የድንበር ቁጥጥር መጠናከሩን ገልጾዋል፡፡ በተጨማሪም በዚህ ድንበር በማሻገር ተግባር ላይ የተሰማሩ 86 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አል አረቢያ ጨምሮ ዘግቧል፡፡

ደጃች ውቤ ሠፈር ሊፈርስ ነው


ቅርስም ሆነ ሌላ ነገር ከባቡር ተርሚናሉ ጋር የሚገናኝ ከሆነ (ይፈርሳል)-የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር

wubie bereha


“በቅርስነት ሊጠበቅ ሲገባው በድንገት ሊፈርስ ነው መባላችን አሳዝኖናል” የአካባቢው ነዋሪዎች

ከአዲስ አበባ ከተማ ምሥረታ ጋር ተያይዞ በቀደምትነት ከተመሠረቱ አካባቢዎች ቀዳሚነቱ የሚነገርለትና በተለምዶ “ውቤ በረሃ” በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ደጃች ውቤ ሠፈር፣ በከፊል የሚፈርስ መሆኑ ለነዋሪዎች ተነገራቸው፡፡
በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ አምስት ንዑስ ቀበሌ 05 ከጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት ወደ አፍንጮ በር በሚወስደው መንገድ በቀኝ በኩል በ11.6 ሔክታር ቦታ ላይ ያሉ ነዋሪዎች እንደሚነሱና ከ100 ዓመታት በላይ ያስቆጠረው ሠፈር እንደሚፈርስ ለነዋሪዎቹ የተነገራቸው፣ መስከረም 11 ቀን 2006 ዓ.ም. በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ለግማሽ ቀን በተደረገ ውይይት ነው፡፡
ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በስተቀኝ በኩል በሚያስወጣው አስፓልት እስከ አደባባዩ ድረስ የተገነቡ የመኖሪያ ቤቶች፣ የንግድ ቤቶችና የተለያዩ ቢሮዎች፣ ሆቴሎችና ምግብ ቤቶችን ጨምሮ እስከ አፍንጮ በር ድልድይ መዳረሻ ድረስ እንዲፈርሱ ምክንያት የሆነው፣ የባቡር ተርሚናልና ኃይል መስጫ ጣቢያ ሊገነባበት በመሆኑ እንደሆነ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት በተደረገው የግማሽ ቀን ስብሰባ እንደተነገራቸው ነዋሪዎቹ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
ነዋሪዎቹ እንደገለጹት፣ በጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አደባባይ ፊት ለፊት ከሚገኙት ንግድ ቤቶች ጀምሮ ከሦስት ሔክታር በማይበልጥ ቦታ ላይ ያሉ ነዋሪዎች እንደሚነሱ ቀድመው ተነግሯቸዋል፡፡ መስከረም 11 ቀን አስቸኳይና ድንገተኛ ስብሰባ እንዳለና ማንም ቢቀር ኃላፊነቱ የራሱ እንደሆነ በማስጠንቀቅ ነዋሪዎች እንዲገኙ ከተደረገ በኋላ፣ በሰሙት ጉዳይ እጅግ በጣም መደንገጣቸውንና ማዘናቸውን አስረድተዋል፡፡
የባቡር ተርሚናልና ኃይል መስጫ ጣቢያ ግንባታ በሚል በዳር ያሉት እንደሚነሱ በቅድሚያ ከተነገራቸው በኋላ በድንገት “የሚያስፈልገው ስምንት ሔክታር ነው፡፡ የሚቀረው 3.6 ሔክታር ተቆርጦ መቀጠል ስለሌለበት ለመልሶ ማልማት መፍረስ አለበት፡፡ ይኼ ደግሞ ተወስኖ አብቅቷል” መባላቸው ተገቢ አለመሆኑንና ኅብረተሰቡን መናቅ እንደሆነ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

Wednesday, September 25, 2013

ከለውጡ በኋላስ? (ጋዜጠኛ ተመሰገን ደሳለኝ )


September 24, 2013

ኢህአዴግ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ (በውስጥም በውጪም ተግዳሮቶች) መገፋቱን በሚያመላክቱ የፖለቲካ አጀንዳዎች ላይ የሚያጠነጥን አንድ ፅሁፍ (‹የአብዮቱ የምፅዓት ቀን ምልክቶች›› በሚል ርዕስ) አቅርቤ እንደነበር ይታወሳል፤ ይዘቱም በመጪዎቹ ወራት ወይም ዓመት ስርዓቱ ‹ምርጫ› አሊያም ‹ህዝባዊ› እምቢተኝነት ከሚያመጣው ‹ማዕበል› (እንደበረከት ስምዖን አገላለፅ ‹ናዳን በሚገታ ሩጫ›) የማምለጥ ዕድሉ የጠበበ መሆኑን የሚያመላክት ነው፤ ይሁንና አንድ አብዮት ታላቅ (ውጤታማ) ሊባል የሚችለው አምባገነን ስርዓትን በመቀየሩ ብቻ ስላልሆነ (ሥር-ነቀል ለውጥ የሚፈጥር አብዮት ዋጋ የሚኖረው የዲሞክራሲ ተቋማትን መሰረት መጣል ሲችል ነውና) በቀጣይ መፃኢ ዕድሉ ላይ መነጋገሩ አስፈላጊ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡
Journalist Temasegan Dasaleg
በዚህ ፅሁፍህ ተጠየቅም ‹ከስርዓቱ ለውጥ በኋላ፣ ማን ነው አማራጩ?› የሚለው ጥያቄ ትኩረት ይደረግበት ዘንድ አመላክታለሁ፡፡
ምክንያቱም በጠለፉ መንገድ ከቀሩ አብዮቶች ታሪክ ተምረን፣ ‹መጥነን ካልደቆስን› የሚከፈለውን ዋጋ በብላሽ የሚያስቀር አሳዛኝ ሁናቴ ሊፈጠር ይችላልና (ቭላድሚር ኤሊች ሌኒን ‹‹አብዮት፣ ለአብዮት ብቻ ሲባል መካሄድ የለበትም›› እንዲል፣ ከኢህአዴግ መገላገሉ መልካም ቢሆንም፣ የአገላጋዩን ማቀፊያ ከወዲሁ መምረጡ ወይም የምንጠይቀውን ማወቁ ብልህነት ነው)

አማራጩ ተወልዷልን?
ከኢህአዴግ በኋላ የሚተካው አማራጭ ተዘጋጅቷል? …ይህንን ቀዳዳ አስቀድሞ መድፈኑን አስቸኳይ ያደረገው፣ ለውጡ የሚመጣበት መንገድ ‹ከህዝባዊ እምቢተኝነት› ይሆናል የሚለው ቅደመ-ግምት ነው፡፡ ከታዓማኒና በዕኩል አሳታፊ ምርጫ የሚነሳ ሽግግር (‹ሕዝብ የሚፈልገውን ያውቃልና ውሳኔው መከበር አለበት› ከሚለው የዲሞክራሲ ፅንሰ-ሃሳብ በመነሳት) አሳሳቢነቱ ከአደባባይ ተቃውሞ የሚመነጨውን ያህል አይደለም፤ ስለዚህም ከስጋት ነፃ መሆን የሚቻለው በሰላማዊ መንገድ ለመታገል መሰረታቸውን ሀገር ቤት አድርገው በህግ የተመዘገቡ የፖለቲካ ድርጅቶች የቤት ስራቸውን ሰርተው ዝግጁ ሆነው ሲጠብቁ ብቻ ነው፡፡ ይህ ግን የድርጅቶቹን ቁጥር ከሰማኒያ በላይ ከማሻቀብ ያለፈ አስተዋፅኦ የሌላቸውን አሰስ-ገሰስ ‹ፓርቲ›ዎች በሙሉ እንደሚመለከት ተደርጎ መወሰድ የለበትም፡፡
ነፍስ ይማርና በ‹‹ልዕልና ጋዜጣ›› እልፍ አእላፍ ችግሮቹን ማረም ከቻለ መድረክ ተስፋ ሊጣልበት ይችላል ብዬ እንደማስብ መፃፌን አስታውሳለሁ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የመድረክ አሰላለፍ ሊቀየር በማጋደሉ (ከአንድነት ጋ አብሮ መቀጠሉ ማጠራጠሩ) እና ሰማያዊ ፓርቲ አዎንታዊ እንቅስቃሴ ከማድረጉ አኳያ ተፎካካሪ ሊሆን የሚችልበት ዕድል በመፍጠሩ፣ በአጀንዳው ላይ ማካትቱን ተገቢ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ ይሁንና ሌሎች ፓርቲዎችን እዚህ ጋ ያላነሳሁበት፣ ከላይ ከጠቀስኩት በተጨማሪ ሶስት ምክንያቶች አሉኝ፤ ቅቡልነትን ማጣት፣ እንቅስቃሴ አልባ መሆን እና በገዥው ፓርቲ ስፖንሰርነት መተንፈስ የሚሉ፡፡

Tuesday, September 24, 2013

ሙስሊም ወንድማማች ዕገዳ ተጣለበት


ውሳኔው የሙርሲን “ቅርንጫፍ” ድርጅቶችንም ይጨምራል

m b


የካይሮው አስቸኳይ ጉዳዮች ፍርድቤት የሙስሊም ወንድማማችን እና ከእርሱ ጋር ግንኙነት ያላቸውን መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በሙሉ ከማንኛውም እንቅስቃሴ አገደ፡፡ የመካከለኛው ምስራቅ የዜና አገልግሎትን ጠቅሶ አልጃዚራ እንደገለጸው ዕገዳው መሐመድ ሙርሲ ይመሩት የነበረውን እና ከሙስሊም ወንድማማች ጋር የጠበቀ ግንኙነት ያለውን የእስላማዊው እንቅስቃሴ የፖለቲካ ክንፍ የነጻነትና ፍትሕ ፓርቲንም ሊጨምር ይችላል፡፡
በሕዝብ ድምጽ ሥልጣን የተረከቡትን መሐመድ ሙርሲ በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ የሙስሊም ወንድማማች ደጋፊዎችና ከፍተኛ አመራሮች አሁንም እየታሰሩና እየተገደሉ ይገኛል፡፡
ከፖሊስና፣ ከደኅንነትና ከመፈንቅለ መንግሥቱ ደጋፊዎች ጋር የሚደረገው ውዝግብ ደም አፋሳሽ ከመሆን አልፎ በወንድማማቾቹ እንቅስቃሴ ላይ “የአሸባሪነት” ታርጋ አስለጥፎበታል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ባለፈው ወር በተከሰተው ግጭት የሙስሊም ወንድማማች ደጋፊዎች ከ600 በላይ ክርስቲያኖችን መግደላቸውና ቤ/ክናትን ማቃጠላቸው እንደሚገባው አልተዘገበም በማለት አንዳንድ የሚዲያ ተቋማት ወቀሳ ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡
የሰኞው ዕለት ዕገዳ በአሁኑ ጊዜ በወንድማማች ኅብረቱ ላይ የሚካሄደውን የተፋፋመ ወከባ በሕጋዊ መልኩ ያጠናክረዋል የሚል ግምት እየተሰጠበት ቢሆንም የግብጽ አገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ግን ሁኔታው እንደዚያ እንዳልሆነ ለአልጃዚራ ዘጋቢ ተናግሯል፡፡ “በአሁኑ ጊዜ እየተካሄዱ ያሉት የተቃውሞ ሰልፎች ሰላማዊ እስከሆኑ ድረስ መቀጠል ይችላሉ፤” ሆኖም የሙርሲን መነሳት በመቃወም አስመስለው የሽብር ተግባር ለመፈጸም የሚፈልጉ ሁሉ የትም ሊያመልጡ እንደማይችሉ አስጠንቅቋል፡፡
85ዓመታትን ያስቆጠረው እስላማዊው እንቅስቃሴ በ1946 በሕግ ታግዶ የነበረ ሲሆን በቅርቡ ሕጋዊነቱን አግኝቶ ወደ ግብጽ ፖለቲካ ውስጥ ከገባ በኋላ የበርካታዎችን ድጋፍ አግኝቷል፡፡ የዚህም ውጤት በዴሞክራሲያዊ መንገድ በግብጽ በቅርቡ በተካሄደው ምርጫ የፓርላማውን አብላጫ ወንበርና የፕሬዚዳንትነቱን መንበር መቆጣጠር ችሏል፡፡

Monday, September 23, 2013

አወይ ሶሪያ….የኢትዮጵያ ጠላት!

September 23, 2013

(በሰሎሞን ተሰማ ጂ.) http://semnaworeq.blogspot.com   Email:solomontessemag@gmail.com
የሶሪያ ጉዳይ ከዕለት ወደ ዕለት እየከፋ መጥቷል፡፡ በስልጣን ላይ ያለው ጎሳ “የአላዊት ጎሳ” ይባላል፡፡ አላዊቶችና በደዊኖች በሽፍትነትና በባህር ላይ ውንብድና ስማቸው የገነኑ ናቸው፡፡ በደዊኖች፣ ሶሪያን ለዘመናት ያህል ሲፈልጧትና ሲቆርጧት ኖረዋል፡፡ እንደነሱ ዘረኛ፣ እንደበደዊኖች ጠባብ፣ አክራሪና ቁመኛ ታይቶም-ተሰምቶም አይታወቅም፡፡ አላዊቶችም ቢሆኑ “አልሸሹም ዞር አሉ” ናቸው፡፡ እነዚህ ወገኖች፣ የሶሪያን ሀገረ-መንግሥት (State apparatus) ከተቆጣጠሩበት ዘመን ጀምሮ ለኢትዮጵያ በጎ ተመኝተውላት አያውቁም፡፡ ይባስ ብሎ ደግሞ፣ ከ1950ዎቹ መጀመሪያ ወዲህ እጅግ በከፋ መልኩ የኢትዮጵያን ጥቅምና ሉዓላዊነት በሚፈታተን መልኩ በግትርነት ቆመው ነበር፡፡ በጣም በተጋነነና በመረረ ኹናቴ መንቀሳቀስ የጀመሩት ግን ከ1953ዓ/ም ወዲህ ነው፡፡ በዚህ ዓመትም በጂዳ-ሳዑዲት ዓረቢያ የተቋቋመውን “የኤርትራ ነፃ-አውጪ ድርጅት” (ወይም በተለምዶ አጠራሩ ጀ.ብ.ሐ) እየተባለ የሚታወቀው፣ በአሳውርታ የሚኖሩት የቤንአሚር ጎሳ ተወላጆች ቡድን ለመደገፍ በደዊኖች ተሯሯጡ፡፡ ከእነርሱም ቀጥሎ ወደስልጣን የመጡት አላዊቶች ተመሳሳይ ተግባር ፈፀሙ፡፡ ያለምክንያት አልነበረም፤ በአሳውርታ የሚወለዱት ቤንአሚሮች “የበደዊንና የአላዊት ደም አላቸው” ከሚል ጎሰኛ ቀመር ተነስተው ነው፡፡ 
Syria officially the Syrian Arab Republic
ስለሆነም፣ በ1955ዓ/ም በይፋ ለጀ.ብ.ሐ አገናኝ ቢሮ በደማስቆ ከተማ ተከፈተለት፡፡ ከዚያም ጊዜ ጀምሮ፣ በርካታ ፀረ-ኢትዮጵያ እንቅስቃሴዎችን መደገፍ ጀመሩ፡፡ በ1960 እና 1961ዓ.ም ብቻ እንኳን፣ “ነፃነትን-መደገፍ” በሚል ስም፣ እ.አ.አ እስከ 1970 ድረስ በበደዊን ጎሳዎች የሚመራው የሶሪያ መንግሥት በርካታ የአጋሚዶ/የውንብድና ተልዕኮዎችን ከአፍ-እስከ-ገደፉ ደግፏል፡፡ (ይሄንን በተመለከተ፣ በ1933ዓ/ም በደቀሽሐይ-ሐማሴን የተወለደውና በጀብሐ ውስጥ የ5ተኛው ወታደራዊ ክፍል/ምድብ ዋና መሪ የነበረው፣ ወልዳይ ካህሳይ ብዙ-ብዙ ነገር ያወሳናል፡፡ ወደኋላ ላይ እንመለስበታለን፡፡) በዚህ የመቀራረብና የመተሳሰብ ዘመን በሆነው በ21ኛው ክፍለ ዘመን፣ በደዊኖችና አላዊቶች ከአንድ መንግሥት የሚጠበቀውን ዓለም አቀፍ ኃላፊነት ዘንግተው፣ ዓለም አቀፍ ውንብድና ውስጥ ሙጭጭ አሉ፡፡ በዘመናዊ አስተዳደር፣ ሃይማኖትና ጎሳ እምብዛም ቦታ እንደሌላቸው ያልተገነዘቡት በደዊኖችና አላዊቶች፣ በዘር፣ በጎሳና በሃይማኖት ጥላ ስር የተሰባሰቡትን ወንበዴዎች ሁሉ በወታደራዊ ስልጠናና በትጥቅ ሲረዱ ኖረዋል፡፡ በዚህም አቋማቸው የተነሳ በመካከለኛው ምስራቅ ውስጥ የተነሱትን ማናቸውንም ግጭቶች ቤንዚን በማርከፍከፍ ሲጋግሙት ኖረዋል፡፡ ወይም በሀገራችን አባባል ጭድ ሲነሰንሱበት ኖረዋል፡፡ ሊባኖስ ቀንደኛዋ ተጎጂ ናት፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ሐሪሪ ሳይቀሩ የተገደሉት በሶሪያ ጎሰኞች መሰሪ ደባ ነው፡፡ (በአሜሪካዊያኑና በበርካታ የዓረቡ ዓለም ሰዎች የተጠላውና የተወገዘው-“ጫማ ሳይቀር የተወረወረበት”-ትንሹ ጆርጅ ቡሽ እንኳ፣ “የዳቢሎስ ዛቢያ (Evil Axes)” ብሎ እስኪጠራት ድረስ፣ የበደዊኖቹና የአላዊቶቹ ሶሪያ፣ እጅግ አገደኛ ምሳር ናት፡፡)

Sunday, September 22, 2013

የዛሬው የሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ ፎቶና የሚያሰሟቸው መፈክሮች በጥቂቱ !!

September 22, 2013


በአሁኑ ሰዓት ሰማያዊ ፓርቲ ከሶሰት ወር በፊት የጠራውን ሰልፍ እያካሄደ ይገኛል:: ሰልፉ በደማቅ ሁኔታ ተጀምሮ ነበር የሰልፉ መድረሻ መሰቀል አደባባይ ቢሆንም ሕዝቡ አራት ኪሎ አካባቢ ሲደርስ የአዲስ አበባ ፓሊሶች ሰልፈኛውን ወደ መሰቀል አደባባይ እንዳይሄድ ሲያግዱ የፌድራል ፓሊስ ደግሞ በርቀት እየተመለከተ ነው::ሰልፈኞቹ ወደ ስማያዊ ፓርቲ ቢሮ እንዲመለስ ተደርጓል ሕዝቡ ግን ድምጹን ከማሰማት ወደኋላ አላለም
ርዮት ትፈታ !! ውብሽት ይፈታ !! እሰክንድር ይፈታ !! አንዷለም ይፈታ !!! አቡበከር ይፈታ !!! ፍትህን መጠየቅ አሽባሪነት አይደለም !! ነፃነት እንፈልጋለን !! እኛ አሽባሪ አይደልንም !! ፍትሕ እንፈልጋለን !!! የሙሰሊም ኮሚቴ ይፈቱ !!! ዜጎችን ማፈናቀል አግባብ አይደለም !!! አንለያይም !!! አንለያይም !! ፍትህን ያሉ ቃልቲ ገቡ!! አሽባሪ አይደለንም !! ፍትህ ናፈቀኝ !! ድምፃችን ይሰማ!! ፍትሕ እያሉ ቃልቲ ገቡ !! ውሽት ሰለቸን !! ፍትህ ናፈቀን !

Friday, September 20, 2013

አሳዛኙ የወገናችን ኅልፈት!


"ህይወት እንደዋዛ"

the pic


ዲፕሎማቱ እጅ ላይ ያረፈችው ኢትዮጵያዊት ወጣት ሬሳ ትላንት ከሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ ወዳልታወቀ ስፍራ ተወሰደ ።
ቀን መስከረም 8: 2006 ለ5ኛ ግዜ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግዜያዊ መጠለያ ኮኔትነር ውስጥ፡ የአንዲት ኢትዮጵያዊት አስዛኝ፡ ህልፈተ ህይወት የአካባቢውን ማህበረሰብ እምባ ሲያራጭ፡ ደረት ሲያዳቃ መዋሉን የአይን ምስክሮች ገለጹ። ወጣቷ በቤት ሰራተኝነት ኮንትራት የመጣች የክርስትና እምነት ተከታይ መሆኗን የሚናገሩት እነዚህ የአይን እማኞች የወጣቷ ሬሳ እስካሁን በውል ወዳልታወቀ ስፍራ መወሰዱን አረጋግጠዋል።
የእህቶቻችን ሞት ከሚፈበረክበት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር የስደተኞች ጊዜ ያዊ መጠለያ ኮንቴነር፡ ያለምንም ህክምና እና በቂ መሰረታዊ ፍጆታ በለሌለበት ሁኔታ እንደ ወንጀለኛ የኮንቴነር የብረት በር ተከርችሞባቸው ከሚገኙ እህቶቻችን መሃከል አንድ ወር ባልሞላ ግዜ ውስጥ በተከታታይ የሁለት ኢትዮጵያውያን ህልፈተ ህይወት መሰማቱ የአካባቢውን ማህበረሰብ አስደንግጦል።
በተለይ ትላንት ማለዳ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 3 አካባቢ አስከሬንዋ ጊዜያዊ መጠለያ ኮንቴነር ውስጥ ሞታ የተገኘችው ኢትዮጵያዊት ወጣት ህመሙ አገርሽቶባት ስታቃስት «ጣዕረሞት ስታሰማ»፡ እንደ ነበር የሚናገሩ ወገኖች ዲፕሎማቱ ትብብር እንዲያደርጉላት ስልክ ቢደወልላቸውም በወቅቱ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የወጣቷ ህይወት በሚያሳዝን ሁኔታ ማለፉን ይገልጻሉ።
ሟች እዚህ ደረጃ ላይ ከመድረሷ በፊት ዲፕሎማቱ በኤምባሲው ሃላፊነት ወደ ሆስፒታል ወስደው ማስመርመር እና ህይወቷን ከሞት መታደግ ሲችሉ ባሳዩት ግዴለሽነት እና ወገናዊ ርህራሄ የጎደለው አሰራር የወጣቷ ህይወት እዚህ በረሃ ላይ ቀርቷል ብለዋል። ወጣቷን ወደዚህ ግዜያዊ መጠለያ ግቢ ዲፕሎማቱ ከአሰሪዎችዋ ተረክበው ሲያመጧት “ሃኪም ቤት ውሰዱኝ ህይወቴን አጣሁ!! አድኑኝ ኧረ የወገን ያለህ!! ኧረ ያህገር ያለህ!! አናቴ ድረሺልኝ!!” እያለች ትማጸናቸው እንደነበረ በአካባቢው የነበሩ የአይን ምስክሮች አክለው ገልጸዋል። የወጣቷ የሰውነት አቋም እና አጠቃላይ ሁኔታ ያዩ አንዳንድ ታዛቢዎች በውስጥዋ የቆየ በሽታ እንደሌለባት እና ወጣቷ አንጀቴ ተቃጠለ ውሃ ውሃ ስትል እንደነበር እና ሃኪም ቤት ውሰዱኝ እያለች ልብ በሚነካ ሁኔታ ስትማፀን የታዘቡ ወገኖች ምናልባትም ከምግብ ጋር የተቀልላቀለ መርዝ ነክ ነገር በልታ ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬያቸውን ያጎላሉ።

Wednesday, September 18, 2013

የቤተመንግስት ደህንነት ሃላፊ ተነሱ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

የነአዜብ ቡድን እየተመታ ነው!!

የቤተ-መንግስት የደህንነት ጥበቃ ዋና ሃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት የሕወሐት አባል አቶ ጌታቸው ተፈሪ ከስልጣናቸው መነሳታቸውን ምንጮች አስታወቁ። አቶ ጌታቸው ቀደም ሲል በክልል 14 ፖሊስ ኮሚሽን የደሕንነት ልዩ ተወርዋሪ ሃይል ሃላፊ ተደርገው ሲያገለግሉ መቆየታቸውን የጠቆሙት ምንጮች፣ ከዚያም ወደ ቤተ መንግስት ተዛውረው መመደባቸውንና በተጨማሪ የአገር ውስጥ ደህንነት ምክትል ሃላፊ በመሆን ከአቶ ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤል ጋር ሲሰሩ መቆየታቸውን አስረድተዋል። የአቶ መለስና ወ/ሮ አዜብ የቅርብ ሰው የሆኑት አቶ ጌታቸው ተፈሪ በነበራቸው ታማኝነት የቤተመንግስት የደህንነት ሃላፊ ተደርገው በአቶ መለስ ተመርጠው እንደተሾሙ ያስታወሱት ምንጮች፣ በማያያዝም እስከ 1994ዓ.ም የቤተመንግስት የደህንነት ጥበቃ በሃላፊነት ሲመሩ የቆዩት አቶ ዘርኡ መለስ በወቅቱ ከአቶ መለስ ጋር በፈጠሩት የፖለቲካ ልይነት ምክንያት ካዛንቺስ አካባቢ በሚገኘው የቀድሞ “ኮከብ ሬስቶራንት” የአሁኑ “ሚልክ ሃውስ” መኖሪያ ሕንፃ አንደኛ ፎቅ ቤታቸው ውስጥ አንገታቸው በስለት ታርዶና በድናቸው ተበላሽቶ መገኘቱን አመልክተዋል። ይህን አሰቃቂ ግድያ ያከናወነው አሁን በእስር ቤት የሚገኘው የቀድሞ አገር ውስጥ ደህንነት ሃላፊና የአቶ መለስ ቀኝ እጅ ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤል መሆኑን ምንጮቹ አጋልጠዋል።
የነ አዜብ ቡድን እየተመታ ነው!
የነ አዜብ ቡድን እየተመታ ነው!

Tuesday, September 17, 2013

የኤርትራ ጉዳይ በሶስት ትውልዶች ውስጥ


map of eritrea


የኤርትራው ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቅ እንደቀልድ እና እንደ እልህ የጀመሩት ”ኤርትራ ኢትዮጵያዊ አይደለችም” ብሎም ”የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው” አጀንዳን የሻብያ አጀንዳ እንዲሆን ካስደረጉ በኃላ ከእሳቸው በፊት የነበረው ትውልድ ባይቀበላቸውም የእሳቸውን ትውልድ ”የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው” የሚለውን ገለፃ ለመንገር አላንገራገሩም። አቶ ኢሳያስ በአንድ ጎናቸው ተንቤን ትግራይ ቢወለዱም ያነሷት ጉዳይ ግን ኢትዮጵያን ለማዳከም ለዘመናት ከሚያልሙ አንዳንድ የአረብ ሀገራትም ሆነ ጎረቤት ሱዳንን የሚያማልል ብሎም ዳጎስ ያለ ድጎማ የሚያስገኝ የወቅቱ አዋጪ ”የገበያ ማስታወቅያ” መሆኑን የተረዱት ይመስላሉ።
ቀዳማዊ አፄ ሃይለስላሴ ዩንቨርስቲ በነፃ ትምህርት ዕድል ይማሩ የነበሩት አቶ ኢሳያስ አፈወርቅ ”የኤርትራ ነፃነት ግንባር” (ELF) ከመቀላቀላቸው በፊት በቻይና የፖለቲካ እና የወታደራዊ ስልጠና ለመውሰድ ተጉዘው እንደነበር ተወስቷል። አቶ ኢሳያስ እና ድርጅታቸው ከሰላሳ አመት ውግያ በኃላ ”ሁሉ ነገር ተፈፀመ!” ብለው ተናግረው ሳይጨርሱ ሌላ ጦርነት ”በባድሜ መሬት ሰበብ” እውነታው ግን የምጣኔ ሀብት የበላይነት ለመያዝ ከሕወሓትጋር በነበረ ግፍያ አዲስ ጦርነት ውስጥ ገብተው አስር ሺዎች ሲረግፉ አብረው ከአቶ መለስ ጋር ተዋናይ ሆነው ታዩ። ያ ”የቅኝ ግዛት ጥያቄ” ያሉት ጉዳይ አስመራን ከያዙ በኃላም ጥያቄው ተወሳሰበባቸው።
አቶ ኢሳያስ እና ድርጅታቸው ሻብያ ስልጣን ከያዘ ሃያ ሁለት ዓመታትን አስቆጠረ። በእነኝህ ሃያ ሁለት ዓመታት ውስጥ የኤርትራ ተወላጆችሲነገራቸው የነበረው ”የአፍሪካ ታይዋን ትሆናለች” ትንታኔ ሐሰት መሆኑን ተረዱት። ይልቁን ከአስመራ ዩንቨርስቲ ጀምሮ እስከ ቀድሞ በውሱን አቅም ይሰሩ የነበሩ ድርጅቶችን የገበያ ተወዳዳሪነት አቅም ተዳከመ። በአስር ሺዎች በሱዳን፣በኢትዮጵያ፣በየመን አድርገው ተሰደዱ።ኤርትራ ከዲፕሎማሲ እስከ አካባቢ ሃገራት ድረስ እንድትገለል አደረጉ። የአቶ ኢሳያስ ”የዓለም እይታ ፍልስፍና” የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ሆነ። እሳቸው አሜሪካንን የሚያዩበት እይታ የግል አስተያየት መሆኑ ቀረና የመንግስት ቃል አቀባይ የሚናገረው ”መዝሙረ-ኤርትራ” ሆኖት አረፈው። አምባገነንነት አስደናቂው እና አዝናኝ ገፅታው ይሄው ነው።መሪው ሲያስነጥሰው ሁሉም ለመሳል ጉሮሮውን ይጠራርጋል።
”የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው” የሚለው የአቶ ኢሳያስ ትውልድ ጥያቄ ዛሬም ፈተና ላይ ነው።
አቶ ኢሳያስ እና ትውልዳቸው የወቅቱ ገበያን ስሌት ያደረገው ”የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው” አሁን በተነሳው ትውልድ የሚሞገትበት ጊዜ እሩቅ የሚመሰለው ካለ በሃሳቡ የመቀጠል መብቱን አከብራለሁ። ለእኔ ግን ይህ ጥያቄ በእራሱ የሚሞገትበት ጊዜ እንደሚመጣ አስባለሁ። የማኅበራዊ ትምህርት ሳይንስ ለምሳሌ የፖለቲካ ሳይንስ እንደ ኬሚስትሪ እና ባዮሎጂ በቤተ-ሙከራ (ላብራቶሪ) ጥናት ውጤቱን ከወዲሁ ለመወሰን አይቻልም። የሚቻለው ነገር ካለፉት፣አሁን ካለው እና መጪውን ከመተለም አንፃር በምክንያታዊ አቀራረብ ከወዲሁ ሁኔታዎችን መመልከት ነው። ከእዚህ አንፃር የኤርትራ ፖለቲካዊ ጥያቄዎች ሶስተኛው ትውልድ ላይ የወደቀ የእዚህ የሶስተኛው ትውልድ ጥያቄም በእርሱ ታሪካዊ ሂደት የሚፈነዳበት ሁኔታ ይኖራል። የሶስቱ በኤርትራ ጉዳይ የተሳተፉ ትውልዶች ጥያቄዎች እንደዘመናቱ ”የፖለቲካ ገበያ አዋጭነት” እንደ አቶ ኢሳያስ ያሉ ተዋናዮች ተጫውተውበታል። ጥያቄው የሶስተኛውንም ትውልድ ጥያቄ አሁንም ”የፖለቲካ ገበያውን” ተመልክተው ጥያቄውን በመሞረድ የአቶ ኢሳያስ ቡድን ሊመራው ይችላል ወይ? የሚለው ጥያቄ ፈታኝ ነው። መልሱ አይመስልም ነው።

Monday, September 16, 2013

ሰንደቅዓላማችን (ትእምርተ-ኪዳናችን) ከየት መጣ ማንስ አጠፋው?

(ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

flag ethio


ሰንድቅ ዓላማ ማለት በዘንግ ወይም በመስቀያ ያለ ሰንደቅ ማለት ነው፡፡ መስቀያው ዓላማ ሲባል የሀገር ዓርማ የሆነው ባለቀለሙ መለያ ምልክት ደግሞ ሰንደቅ ይባላል፡፡ የሚለው አንዱ ሲሆን ሌላኛው ትርጉሙ ደግሞ ሰንደቅ ዓላማ የሚባለው ባለቀለሙ የመለያ ምልክት ብቻ እንጅ መስቀያውን አይጨምርም ሰንደቅ ዓላማ መባሉም ሰንደቁ የራሱ የሆነ ዓላማ እንዳለው ለማመልከት ነው የሚሉም አሉ፡፡ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የመንግሥት ሰንደቅ ከመሆኑ በፊት ከኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ንዋዬ ቅድሳት አንዱና እንዲያውም የመጀመሪያው የሆነ የቤተክርስቲያን ሰንደቅ ነበር፡፡ በቤተክርስቲያን እነዚያ ሦስት ቀለማት አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ወይም ቀይ ቢጫ አረንጓዴው ቀለማት በንዋዬ ቅድሳቶቿ ሁሉ ላይ ይገኛል፡፡
ከትንታዊ የብራና መጻሕፍት አንሥቶ እስከ ጉልላቷና መንበረ ታቦቷ ድረስ ከጥንት ጀመሮ የእነዚህ ቀለማት ማኅተም በተለያዩ መልኩ አሠራሩና ጥበባዊ ስልቱ እንዲያርፍበት ይደረጋል፡፡ የዚህ ምክንያቱ ደግሞ በመጽሐፍ ቅድስ በዘፍ 9÷8-17 ላይ እንደተገለጸው እግዚአብሔር በኖሕ በኩል ለሰው ልጆች ሁሉ ዓለምን ዳግመኛ በጥፋት ውኃ ላያጠፋት ቃል ሲገባለት ለገባው ቃል ምልክትና ምስክር ትሆን ዘንድ ቀስቴን በደመና ላይ እዘረጋለሁ ብሎ የምሕረት ቃል ኪዳን ምልክት ትሁን እንዳለው እናያለን፡፡
አንዳንድ ሰዎች ታዲያ ሰንደቁ ቀስተ ደመና ከሆነ ለምን ሦስት ቀለማት ብቻ ሆነ? በቀስተ ደመና ውስጥ ያሉት ቀለማት ሰባት ናቸውና የሚሉ አሉ፡፡ እርግጥ ነው አትኩረን ላየነው በቀስተ ደመና ውስጥ ያሉ ቀለማት ሰባት ናቸው፡፡ ነገር ግን አራቱ ቀለማት የሚፈጠሩት በውሕደትና በውርርስ እንጅ እንደ ሦስቱ ቀለማት ማለትም እንደ ቀዩ ቢጫውና አረንጓዴው በራሳቸው ህልው ሆነው አይደለም ቀዩ ከቢጫው ቢጫው ከአረንጓዴው ጋር ባለው መገናኛ መገናኛቸው ላይ በንክኪው ውሕደት ሲፈጥሩ የሚፈጠሩና ከቀስተ ደመናው ላይና ታች ከሰማዩና ከመሬቱ ቀለማት ጋር ባለው መወራረስ የሚፈጠሩ ናቸው፡፡ በመሆኑም ቀዩ ከቢጫው ቢጫው ከአረንጓዴው ጋር ሲገናኙ ሲነካኩ የሚፈጠሩት 2 ቀለማትና በቀለማት ባሕርይ ምክንያት ከላይ ከሰማዩ ከታች ከመሬቱ ቀለማት ጋር በሚፈጠሩት መወራረስ የሚፈጠሩት ሌላ 2 ቀለማት ናቸው፡፡ በድምሩ 4ቱ ቀለማት ከአረንጓዴው ከቢጫውና  ከቀዩ ውጭ ያሉት በራሳቸው ህልው የሆኑ ሳይሆኑ በእነዚህ በሦስቱ ቀለማት ተጽዕኖ የሚፈጠሩ በመሆናቸው ቤተክርሲቲያን ሦስቱን ዋነኛ የቀስተ ደመናውን ቀለማት ብቻ ልትወስድ ችላለች፡፡
በመሆኑም የቀስተ ደመናው ቀለማት በጉልህ የሚታዩት ቀይ ቢጫ አረንጓዴ ሦስቱ ቀለማት ናቸው እንጅ ሰባት ቀለማት አይደሉም ማለት ነው፡፡ በተጨማሪም  ሦስቱ  ቀለማት ሦስት መሆናቸው በቤተክርስቲያን ካላቸው የሚስጢር ትርጉም አንዱን ብቻ ስጠቅስ የምሥጢረ ሥላሴ ምሳሌ መሆኑ ወይም መሆናቸው ነው ትላለች ቤተክርስቲያን፡፡ ማለትም ሥላሴ (እግዚአብሔር) አንድም ሦስትም ናቸው ወይም ነው የሚለውን ምስጢረ ሥላሴን ለማጠየቅ ነው፡፡ ቀስተ ደመና ከቃል ኪዳን ምልክትነቱም በላይ የልዑል እግዚአብሔር የክብሩ መገለጫም ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስና ነቢዩ ሕዝቅኤል በየራእዮቻቸው ልዑል እግዚአብሔር በክብርና በሚያስፈራ ግርማ በዙፋኑ ላይ ሆኖ ዙሪያውን በሚያምርና ኅብር ባለው የቀስተ ዳመና ጸዳል ተከቦ ተመልክተውታል፡፡ ራዕ ዮሐ 4÷2-3 ትን ሕዝ 1÷26-28

“የበሰበሱት” ህወሃት እና ሻዕቢያ


አንዱ ሌላውን የማጥፋት እሽቅድድም!

tplf-vs-eplf


አምባገነነኖች ከሚታወቁበት አንዱና ዋንኛ መለያቸው መካከል ሁለተኛ ሰው አለማዘጋጀታቸው ነው። አቶ መለስ በድንገት ሲስፈነጠሩ በውል የታየው አስከሬን ደብቆ ድብብቆሽም የዚሁ ውጤት ነው። ኢሳያስ ከስልጣን ቢወገዱ ማን ይተካቸዋል? የሚለው ችግርም ጎልቶ የሚታየው ከዚሁ የአምባገነኖች በሽታ አንጻር ነው።
ግጭትና ችግር ከመፈጠሩ በፊት የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ደወል የሚያንጫርረው ዓለምአቀፉ የግጭት ቡድን (International Crisis Group) ፍርሃቻም ከዚሁ የመነጨ ይመስላል። በኤርትራ ህዝቡ በቃኝ ወደ ማለቱ ደረጃ መቃረቡን የሚጠቁመው የዘንድሮው ዓመት ሪፖርት ኤርትራ በቅርቡ መንግስት አልባ የመሆን እድሏ ሰፊ እንደሆነ ያወሳል። በቅርቡ “የሚከሽፉ መንግስታት” በሚል ስማቸው ከተዘረዘሩት ውስጥ አገሮች መካከል ኢትዮጵያም ተመልክታለች።
እኩል ወደ ስልጣን የመጡት ሻዕቢያና ወያኔ ደረጃቸው ቢለያይም ሊድኑ በማይችሉበት ደረጃ መበስበሳቸው በገሃድ የሚታይ እውነት እንደሆነ አብዛኞች ይስማማሉ። ከበሰበሱበት ባህርና ችግር ለመውጣት አግባብ ያለውን መንገድ ከመከተል ውጪ አንዱ ሌላውን ቀድሞ ለማጥፋት እሽቅድድም መርጠዋል። የዚሁ የእሽቅድድማቸው መድረሻ መሰረት ደግሞ አንዱ ለሌላው ተቃዋሚ ምርኩዝና አጋር የመሆንና አንዱ በሌላው መንኮታኮት የግል ትርፍን አስጠብቆ ለመዝናናት እንጂ ህዝብን ማዕከል ያደረገ አይደለም።
ኤርትራ “በነጻ” ምድሯ ላይ “አቅፋና ደግፋ” የያዘቻቸው የኢህአዴግ ተቃዋሚዎች የሚታይ ውጤት ባለማስመዝገባቸው ተግባር ለሚናፍቁ ወገኖች ጉዳዩ “ከበሰበሰ ባህር” አይነት ሆኖባቸው ዓመታት ተቆጥረዋል። ሰሞኑንን ከኢሳት ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት የግንቦት7 ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ይፋ ያደረጉት መረጃ አዲስ የውይይት አጀንዳ ዘርግቷል።
በኤርትራ መንግስት በኩል የሚደረገው ድጋፍ “ባለ አራትና አምስት ኮከብ ሆቴል ውስጥ ተቀምጦ የመታገል ያህል ነው” በማለትandargachew ያሞካሹት አቶ አንዳርጋቸው “ታይቶ የማይታወቅ፣ ከሚገባው በላይ የበዛ” ሲሉ የገለጹት የኤርትራ ድጋፍ አስቀድሞም ቢሆን ውጤት ማስመዝገብ ያልቻለው ኤርትራ በከተሙ ተቃዋሚዎች ችግር እንጂ በኤርትራ መንግስት እንዳልሆነ በቅርብ ሆነው ማየትና መረዳታቸውን በመግለጽ ምስክርነት ሰጥተዋል።
ይህ መረጃ ከተሰራጨ በኋላ ከኢህአዴግ ወገን ሁለት አንኳር ጉዳዮች ተሰምተዋል። በኤርትራ ላይ መከላከልን መሰረት ያደረገው ፖሊሲ “ተመጣጣኝ ርምጃ መውሰድ” በሚል በመቀየሩ ኢህአዴግ ባልተጠበቀ ወቅትና ጊዜ አስቀድሞ ጥቃት ለመሰንዘር እንደሚችል፣ በሌላ በኩል ደግሞ ለኤርትራ ያዘጋጀላትን አዲስ የአስተዳደር ቅርጽ ተግባራዊ የሚያደርጉ ድርጅቶችን ወደ ግንባር መግፋት የሚሉት የመጀመሪያዎቹ ሲሆኑ ሁለተኛው ግን ከወትሮው ለየት ያለ ሆኖ ተገኝቷል።
አዲስ ራዕይ የሚባለው የኢህአዴግ ልሳን ይፋ እንዳደረገው ወደ ጎረቤት አገራትም ሆነ ሌሎች አካባቢዎች የሚሰደዱ ዜጎች በተቃዋሚ ወገን ለውትድርና እየተመለመሉ እንደሆነና ይህ ሁኔታ በዝምታ ከታየ ስርዓቱ ችግር ሊገጥመው እንደሚችል አመላክቷል። ከዚህም ጋር ተያያዥነት ባለው መልኩ ሌሎች ወገኖች ግብጽ እጇን የዘረጋችላቸው ክፍሎች ስለመኖራቸው መረጃዎች እንዳሉ ለማሳበቅ ሲሞክሩ ሰንብተዋል። ከዚህ አንጻር ቀደም ሲል ከነበሩት የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች በተለየ መልኩ ኢህአዴግ ስጋት ውስጥ ስለመሆኑ ይሰማል።

Friday, September 13, 2013

ስጋቴን ልግለፅላችሁ


(ክፍል አንድ - ከአንዱ ዓለም ተፈራ፤ የእስከመቼ አዘጋጅ)

fear of the


ሀገራችን በአሁኑ ሰዓት በከፍተኛ አደጋ ላይ ነች። ይኼን ሁላችንም እናውቀዋለን። የትግሬዎች ነፃ አውጪ መንግሥት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ያደረሰውና በማድረስ ላይ ያለው ልክ የለሽ በደል፤ ተጽፎም ሆነ ተነግሮ አላበቃም። ገና ብዙ ይጻፋል። ገና ብዙ ይተረካል። ለነገሩ መቼ ይኼ ጉደኛ የወንበዴዎች ድርጅት በደሉን አበቃና! የመጨረሻው ለመቃረቡ ግን፤ የመውደቂያ ደወሉን ራሱ አስምቶናል። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት መውደቁ አይቀሬ ነው፤ ቀን ከመቁጠር ባሻገር። ይኼ ሲከሰት ግን ምን ይከተላል የሚለው ጥያቄ እንደተንጠለጠለ ነው።
ያልተመለሱ ብዙ ጥያቄዎች ዙሪያችንን አጥረውናል። ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ዘር፣ ጎሳ፣ ሀገር፣ ድርጅት፣ ፓርቲ፣ ኅብረተሰብ፣ ኢትዮጵያዊነት፣ የነፃ አውጪ ድርጅት፣ ግንባሮች፣ ጥምረቶች፣ ትብብሮች፣ ደጋፊዎች፣ ተደጋፊዎች፣ . . . እነዚህ ሁሉ ፅንሰ ሃሳቦች በመካከላችን ተመሣሣይ ደወል አያሰሙም። አንዳንዶቹ ላንዳችን ከሚያሰሙት በተቃራኒ ትርጉም ለሌላው ይሠጣሉ። በዚህ በያዝነው ሂደት የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ሲወድቅ የሚተካው ምንድን ነው? የሚለው አሳስቦኛል። የዚህ ጽሑፍ ዘገባ ይኼን በደንብ እንመርምር ነው። ሊከሰቱ የሚችሉ ገፅታዎችን በማመልከት፤ በኔ እምነት ማድረግ አለብን የምለውን አስቀምጣለሁ።
ከፊታችን ከተጋረጠው አደጋ መሰስ አድርጎ የሚያወጣን የተደበቀ ማዳኛ ሚስጥር የለንም። ሁሉን በደንብ ከመርምረን ደግሞ፤ ነገ የሚከሰተውን መተንበዩ ከባድ አይሆንም። አሁን ያለንበትን የፖለቲካ ሀቅ ስመረምረው፤ ነጋችን ተስፋ ሠጪ አይደለም። ለድፍረቴና ረዘም ላለው አስተያዬቴ፤ ብዙ ተጨንቄበታለሁ። በዚህ ስጋት ብቻዬን እንዳልሆንኩ ይገባኛል። አማራጭ ግን አላገኘሁም። እንዳለ ማቅረቡን ግዴታዬ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። የትግል አዟሪት ከመካከላችን ጠፍቶ፣ ሀገራችን ሰላም ወርዶ፣ በትክክለኛ መንገድ ረሀብንና በሺታን አስወግደን፣ ሀገራችን ወደ ብልፅግና ጎዳና እንድታቀና፤ መሠረታዊ የሆነውን የአስተዳደር ጥያቄ ለአንዴና ለሁሌም መመለስ ይኖርብናል። ከውስጡ በስብሶ፣ አለያም በሰላማዊ አመፅ ሆነ በታጠቁ አማፅያን፤ ይኼ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት በሚንኮታኮትበት ጊዜ፤ በቦታው ማን ይተካል?
አንድ ሀገር አንድ ብሔር ከሚለው እስከ አንድ ሀገር ብዙ ብሔሮች ባዮች ድረስ ባንድ ጎራ አለን። የብሔሮች ስብስብ ሀገር ከሚሉት አንስቶ አንድ ሀገር የአንድ ኢትዮጵያዊ ሕዝብ እስከሚሉት ባንድ ጎራ አለን። ታሪካችን ባዮችና የኛ ታሪክ አይደለም ባዮች ባንድ ላይ ባንድ ጎራ አለን። እንዴት ባንድ እንሠለፍ? እውነት አንድ ነገር፣ አንድ ግብ፣ አንድ ውጤት ነው የምንፈልገው? አሁን ባለንበት ሁኔታ የታጋዩ ክፍል ማዕከል ካለማበጀቱ አልፎ፤ አንድ ራዕይና አንድ ተልዕኮ የለንም።
አንዳንዶች፤ “ብቻ የትግሬዎች ነፃ አውጪ መንግሥት ይውደቅ እንጂ፤ ምንም ችግር የለም” ይላሉ። ሌሎች ደግሞ፤ “የለም! ምን ይከተላል የሚለውን ከወዲሁ ካልተዘጋጀንበት፤ በኋላ አደጋ ላይ እንወድቃለን።” ይላሉ። ከትግሬዎች ነፃ አውጪ መንግሥት ውድቀት በኋላ የሚመጣው ያስጨነቃቸውና የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ውድቀት ብቻ ያሳሰባቸው ባንድ ጎራ አሉ። እንዴት ባንድ ይሠለፉ? እውነት አንድ ግብ አላቸው? ባለንበት ሁኔታ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ሲፈረካከት፤ ሀገራችን የበለጠ አደጋ ላይ ትወድቃለች። መፈረካከሳቸው ተወዳጅና አይቀሬ ቢሆንም፤ ተተኪው በጣም የሚያሰጋ ነው።
የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት መውደቁ አንድና ሁለት የለውም። ምን ይከተላል በሚለው ላይ ሳተኩር፤ በኔ ግምት አምስት ሊከሰቱ የሚችሉ ገፅታዎች አሉ። ዋናው ማጠንጠኛ ማዕከሉ፤ ሀገር አቀፍ ሆኖ፤ በሀገሪቱ ሁሉ መረቡን የዘረጋ፣ የሕዝቡ ወገን የሆነ አንድ ጠንካራ አካል በቦታው አለመገኘቱ ነው። በርግጥ በአሁኑ ሰዓት የአንድነት ፓርቲና የሰማያዊ ፓርቲ ጠንካራ ሆነው ይገኛሉ። አንድነት ከፈጠሩና ከተባበሩ፤ ወደ ሕዝባዊ ወገንነት አንድ ዕርምጃ ቀረብ ያለ ጉዞ ይሆናል። በሂደት ደግሞ ሊራራቁ ይችላሉ። አንድነት ፓርቲ በብዙ ቦታዎች መረቡን የዘረጋ ይመስላል። ሰማያዊ ፓርቲ ገና ከአዲስ አበባ እግሩን ያልነቀለ ይመስላል። አንድነት ብቻውን ለመገስገስ የሚሯሯጥ ይመስላል። መራራቃቸው ትልቅ ጉዳት አለው። በሌላ በኩል ደግሞ፤ አንድ ፓርቲ ብቻውን የሚገፋው ማንኛውም መንገድ፤ የብቻው ጉዞ ነው።

በአዲስ አመትም ያላባራው ስቆቃ


ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ እና ልናገረው የከበደኝ ሮሮ!

reeyot2


በግልም ቢሆን አዲሱን አመት በሰላም እና በደስታ መቀበሌ እውነት ነው! መስከረም ጠብቶ ብዙ ቀናት ሳንቆጥር ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚደርሰኝ የስደተኛ ወገን መከራ ግን ከአዲሱ አመት ዋዜማ ጀምሮ እስከ መባቻው አላባራም … አያንዳንዱን የወገን ስደት ሰቆቃ መከራ ጨክኘ ከመናገር ለመቆጥብ ያደረግኩት ትግል ላንዲት ቀን ቢሳካም ህሊናየ ግን እረፍት አላገኘም! በተለይ በአዲሱ አመት ዋዜማ “ብሪማን” ተብሎ በሚጠራው የጅዳው ትልቅ ማረሚያ ቤት የደረሰኝ መረጃ ያማል …
ያሳለፍነው ሮመዳን ወር እንደገባ ጅዳ ውስጥ የትዳር ጓደኛውን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሎ በአሳር በመከራ ከተያዘ በኋላ ዘብጥያ የወረደው አዕምሮውን የሳተ ኢትዮጵያዊ ከጤነኛ ታሳሪ ሃበሾች ጋር ነብሰ ገዳይ ከተራ ወንጀለኛ ጋር ደባልቀው በማሰራቸው ደም እንዲፈስ ምክንያት ሆኗል በማለት ታሳሪዎች እያነቡ ገልጸውልኛል። ይህ ነፍሰ ገዳይ ከአንድ ፍርዱን ጨርሶ በተወካይ ጉትጎታ እጦት ከእምስት ወራት በላይ  እስር ይንገላታ የነበረን በእስር ቤቱ ተደብቆ ሲጋራ የሚሸጥን ወጣት ኢትዮጵያዊን ታሳሪ “አንዲት ሲጋራ ለምን አልሰጠህኝም” በሚል ቂም በብረት ዘንግ አይኑን አፍስሶ የመደብደቡ ወንጀል ሊናገሩት የሚከብድ አሰቃቂ እንደነበር “ተደብዳቢው ከሞት አይተርፍም” ያሉኝ እማኝ ታሳሪዎች በሃዘን ገልጸውልኛል … በአዲሱ አመት ዋዜማ!

በአዲስ አመት መባቻ  ዛሬ ምሽት … ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ እና ፍትህ!

ሀገር ቤት የጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ የርሃብ አድማ መምታት ዜና ከአሜሪካ ራዲዮ የግማሽ ሌሊት የሳተላይት ስርጭት እያዳመጥኩ በወጣቷ ጋዜጠኛ የእስር እንግልት ዙሪያ እንደ ዜጋ የሚሰማኝን ለማለት በሃሳብ ላይ ነኝ፣ ከኮምፒውተሬ ጋር ተፋጥጨ በሃሳብ ከርዕዮት አለሙ አልፊ ከእስክንድር ከውብሸት እና ከአንዷለም የእስር ፈተና ርቄ ፍትህን ፍለጋ ሄጃለሁ … “አሸባሪዎች!” አልኩ ለራሴ ውስጤ እየተቆጣ! ግን ዝም አልኩ … ጭጭ  … ዝም! ምን ይባላል!

Thursday, September 12, 2013

” እኔ ባልፍም እንኩዋን ሺህ ርዕዮቶች ስላሉ በርቱ አትደናገጡ “

September 12, 2013

Sources:-  Daniel Haregawi Timeline(FB)
ke  Sekedar alemu
Reeyot-Alemu
* የርዕዮት ደህንነት አደጋ ላይ መሆኑን እንድታዉቁት ስል ነዉ ይህንን በብዙ ሀዘን ዉስጥ ሆኜ የጻፍኩላችሁ
ትላንትና እንደሁል ጊዜዉ ስንቅ ይዤላት ወደ ቃሊቲ ሔድኩ በር ላይ ያለዉ ፖሊስ “የርዕዮት እህት ነሽ አይደል እሱዋን መጠየቅ አትችይም በአስተዳደር በኩል ሔደሽ ጠይቂ” አለኝ፡፡ እንዳዘዘኝ በአስተዳደር በር በኩል ሔድኩ ወደ ዉስጥ በስንት ትግል ከስለሺ (የርዕዮት እጮኛ) ጋር ገባን፡፡
ከብዙ ጥበቃ በሁዋላ በብዙ ፖሊሶች ታጅባ መጣች ፊትዋ ተለዋዉጦ ስለነበር ምን እንደሆነች ስጠይቃት ከእናት፡ አባት እና ንስሃ አባት ዉጪ ማንም ሊጠይቃት እንደማይችል እና የእነሱን ስም እንድትሰጥ እንደተጠየቀች እና አሚናዘር የሚትባል የሴቶች ክፍል ሀላፊ አልጋዋ ድረስ በመምጣት እንደሰደበቻትና እንደዛተችባት እየነገረችኝ እያለ አሚናዘር የተባለችዉ ሃላፊ ወደኛ በመምጣት ርዕዮትን በማመናጨቅና በመስደብ ከኛ ልትወስዳት ስትሞክር ለምን እንደሆነ ስጠይቃት “ከዛሬ ወዲህ ዐይኑዋን አታዩትም ማንም እኔን ሊያዝ አይችልም የእናንተ ጋዜጣና ሚዲያ ምን እንደሚያመጣ እናያለን ” በማለት ርዕዮትን በማዋከብ እና በመጎተት እየሰደቡ ወሰዱዋት፡፡ ምድር ላይያሉ ሰቅጣጭ እና ለህሊና የሚከብዱ ስድቦችን አወረዱብን በዚህ መሀል ርዕዮት ድምጹዋን ከፍ አርጋ “የማልጨርሰዉን ነገር አልጀምርም እኔን ለማንበርከክ እና ለማሸማቀቅ ክሆነ መቼም አላረገዉም ትገይኝም ከሆነ ነይ ተኩሺ ” ስትል ጎትተዉ ወሰዱዋት፡፡ እኛንም ከጊቢዉ አዋክበዉ አስወጡን፡፡

ኮሎኔል ሃይማኖት ይፈቱ…! ርዮት አለሙም ትፈታ!


733CornellHaymanotTesfayaኮሎኔል ሃይማኖት ይፈቱ…! ርዮት አለሙም ትፈታ!
ኮሎኔል ሃይማኖት የአቶ ገብረዋህድ ባለቤት ናቸው፡፡ ከጫካ ታግለው መጥተው ሹመት በሹመት ሆነው “ሲሾም ያልበላ ሲሻር ምን ሊበላ ነው” ብለው ሲበሉ፣ ሲበሉ፣ ሲበሉ…”የተበሉ” ሴትዮ ናቸው፡፡
አቶ ገብረውሃድ ማለት ደግሞ፤ “ስልጣናቸውን በመጠቀም ያከማቹት መሬት ቢሰበሰብ ኤርትራን የሚያክል ሀገር ይወጣዋል እና ትልቁ ስጋት ሰውዬው መሬቱን ለምን ወሰዱ… ሳይሆን ይሄንን መሬት ይዤ የራሴን እድል በራሴ ወስኛለሁ እና የመገንጠል መብቴ ይከበርልኝ እንዳይሉ ነው…” በሚል ሀገሬው ሲያማቸው የነበሩ ግለሰብ ናቸው፡፡
እንግዲህ እኒህ ቱባ ባለስልጣን ቱባ ቱባ ዝርፊያ አድርገዋል ተብለው ሲታሰሩ ባለቤታቸው ኮሌኔል ሃይማኖት ደግሞ የራሳቸውንም የባለቤታቸውም ዝርፊያ ውጤት የሆነውን ንብረት “ለማንኛውም መደበቅ ነው የሚሻለው…” ብለው ሲያሸሹ ተገኝተው ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡
ከላይ ያየነው ከመንግስት ሚዲያዎች እንደሰማነው እና በራሳችን ቋንቋ ተርጉምን እንደፃፍነው ነው፡፡
ይሄን ያክል ከተንደረደርን፤
ኮሎኔል ሃይማኖት አዲሱን አመት በእስር ቤታቸው ድል ያለ ድግስ ደግሰው ቤተሰቦቻቸው እዛው ቃሊቲ ድረስ ሄደውላቸው ያማራቸውን ለብሰው ያሰኛቸውን በልተው ደስ ያላቸውን ጠጥተው ስቀው ተጫውተው ነው ያሳለፉት፡፡
ከሁለት ቀን በፊት ከጋዜጠኛ ርዮት አለሙ ጋር ክፍል የተጋሩት ኮሎኔል ከጋዜጠኛይቱ ጋር ከተገናኙበት ቀን አንስቶ “ቀልባቸው አልወደዳትም” ይዝቱባታል፡፡ ይሰድቧታል፡፡ ያንጓጥጧታል፡፡ ለዚህ ደግሞ የስጋ ዘመዳቸው ሆነቸው የቃሊቲ ሴት ዋርዲያዎች ሃላፊ አሚናዘር “እሰይ አበጀሽ የኛ ልጅ” ብላላቸዋለች፡፡
“ሙስና ይብቃ” ብላ ስትፅፍ ተገኝታ በቁጥጥር ስር የዋለችው ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ፤ ከእናት እና ከአባቷ ውጪ ሌላ ሰው ማናገር አትችይም ተብላ ስትከለከል፤ ሙስና ይስፋ ብለው በሙስና የተዘረፈ ንብረቶችን ሲያሸሹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ኮሎኔል ያለ የሌለ ሃይላቸውን ተጠቅመው ሊያበሳጯት እየተጉ ነው፡፡ ለዚህም አበል እንዲሆን በዓልን እስር ቤቱ መኖሪያ ቤታቸው እስኪመስል ድረስ አሸብርቀውበት ውለዋል፡፡
በተቃራኒው ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ በዓሉን በርሃብ አድማ አሳልፋለች፡፡ እንደ ኮለኔሏ እና እንደ ዋርዲያዎቹ ዛቻ ከሆነ ርዮት አለሙን በተለያየ ዘዴ ምግብ መመረዝን ጨምሮ ጥቃት ሊያደርሱባት እንደሚችሉ…  ዝተውባታል፡፡
ኮሎኖል ሃይማኖትን ያሰራቸው አካል በጥፋታቸው እስር አስሯቸው ይሁን በስልጣናቸው ስራ እያሰራቸው ይሁን ግራ ተጋብተን እንገኛለን! ማሰሩ ከሆነ  ግን፤ ይሄ እስር ሙስናን የሚዋጋ ሳይሆን ጭራሽ በሙስና የሚያስወጋ ነውና እና ዛሬውኑ ይፈቱልን! ጋዜጠኛ ርዮት አለሙም ትፈታልን! ሌላው ይቅር …ቢያንስ እስር ቤት ውስጥ ድጋሚ መታሰሯ ይቁም!

Wednesday, September 11, 2013

የ፩ኛ ዓመት መልዕክት – የሚዲያ ተሃድሶ ግድ ነው!!


(ርዕሰ አንቀጽ - የ"ጋዜጠኛነት" ውንብድና ይቁም!!)

media


ዛሬ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ከተቋቋመ አንድ ዓመቱ ነው። ባሳለፍነው አንድ ዓመት ውስጥ የደገፉን፣ ያበረታቱን፣ አስተያየት በመስጠት ያረቁንና በመድረካችን የተሳተፉ ያሉትን ያህል የምንሰራውን ስራ ለመቆጣጠር፣ የተመሰረትንበትን ግልጽ መስመር ለማስቀየር የሞከሩና ጨዋነት በጎደለው መልኩ የተዛለፉም አጋጥመውናል። ለሁላችም እንኳን ለአንደኛው ዓመት አደረሰን!!
“ወፌ ቆመች በሉን” በማለት ከዓመት በፊት የሚዲያውን ሰፈር በአሃዱ ብለን ከተቀላቀልንበት ጊዜ አንስቶ የሰራነውን ስራ በጥሞና ለመመልከት ሞክረናል። ሌሎች ሚዲያዎችንና ብሎጎችንም ዳሰናል። የራሳችን ደካማ ጎን ስንፈትሽ እግረ መንገዳችንን ዙሪያችንን ስንቃኝ የሚዲያ ተሃድሶ (ሪፎርም) አስፈላጊ እንደሆነ ተረድተናል። አምነናል። “መቼ” ለሚለው ጥያቄ ምላሹ ዛሬ፣ አሁን፣ አሁኑኑ የሚል ነው።

ድክመታችን

ስንጀምር በዘረጋናቸው ዓምዶች መሰረት ጊዜ በመጠበቅ መረጃ በወቅቱ አላስተላለፍንም። የሳምንቱ አጫጭር ዜናዎችና ድንቃ ድንቅ ወሬዎችን የምናቃምስበት የጎልጉል ቅምሻ ዓምድ በጀመርንበት አቅም መቀጠል አልቻልንም። የግጥም ጨዋታን በተከታታይ አላቀረብንም። ጦማሮች ሲላኩ ፈጥነን ያለ መለጠፍ ችግር አለብን። እነዚህ ከድክመቶቻችን መካከል በቅድሚያ የሚጠቀሱ ናቸው። ምንም እንኳን ስራችንን የምንሰራው በበጎ ፈቃደኞች በትርፍ ጊዜ ቢሆንም በግምገማችን በድክመት አስቀምጠነዋል። አንባቢዎችንንም ይቅርታ እንጠይቃለን።

ያጋጠሙ አንኳር ችግሮች

የተሳሳተ መረጃ በመላክ ታማኝነታችንን ለማሳጣት በተደጋጋሚ ሙከራ ተደርጓል። “እነማን ናቸው፣ ከየት መጡ፣” በሚል አጀንዳ ይዘው የተወያዩ አሉ። ማንነታችንና፣ ምንነታችንን እንድናብራራ በደብዳቤ የተጠየቅንበትም ጊዜ ጥቂት አይደለም። የኤዲቶሪያል ፖሊሲያችን ከሚፈቅደው ውጪ በዘለፋ የተሞሉ ጽሁፎች በመላክ እንዲስተናገድላቸው የወተወቱን በርካታ ናቸው። በቀጥታ በአድራሻችን የማይላክልንን ጽሁፍ ስለማናስተናግድ /ወደፊትም አናስተናግድም/ ወደ አንድ መንገድ ሊያጠጋጉን የሞከሩ አንቱና አንተ የሚባሉ አጋጥመውናል። ከሁሉም በላይ በተደጋጋሚ የጋዜጠኛነት ውንብድና ተፈጽሞብናል። ይህ መረን የወጣ ችግር ማቆሚያ ሊበጅለት እንደሚገባ አጥብቀን እናምናለን። ለሙያውና ለስነምግባሩ የሚገዙ በዚህ ሃሳባችን ድጋፍ እንደሚሰጡን እናምናለን።

በ2005 እንዲህ ብለን ነበር!


ከማበስበሻው ባህር የሚወጣ የለም- ይሰፋል እንጂ

difo


በአዲሱ ዓመት የተመሰረትንበትን አንደኛ ዓመታችንን ምክንያት በማድረግ በተለያዩ ወቅቶች ለንባብ ካበቃናቸው ርዕሰ ጉዳዮች መካከል መርጠን ለትውስታ አቅርበናል። ካቀረብናቸውም ሆነ በድረገጹ ላይ ያሉትን ጽሁፎች በመምረጥና በማሰራጨት ልደታችንን ታከብሩልን ዘንድ ግብዣችን ነው።
በሌላ በኩል የዝግጅት ክፍላችን ኤዲሪቶሪያል ቦርድ አንባቢዎች በነጻነት አስተያየት እንዲሰጡ፣ አስተያየታቸውም ያለ አንዳች ገደብ እንዲታተም ወስኗል። በመሆኑም ጎልጉልን አስመልክቶም ሆነ በርዕሰ አንቀጽ ላይ ባስቀመጥነው ሃሳብ ላይ በመንተራስ አስተያየት ለምትልኩ “ከስድብና ከዘለፋ” ውጪ በደስታ የሚስተናገድ እንደሆነ አስቀድመን እንገልጻለን። የዓመቱ ምርጥ በማለት “መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ” እና “ጥቁሩ ሰው ይናገራል” የሚሉትን ቃለ ምልለስሶች በስጦታ አቅርበናል። መልካም አዲስ ዓመት፣ ለኛም መልካም አንደኛ ዓመት!!
አዲሱ ዓመት ፍትህ የሰፈነበት እርቅ የሚከናወንበት ይሆን ዘንድ እንመኛለን።
የትግራይ ህዝብ ስማ
“ሰሞኑን በውዴታም ይሁን በግዴታ በመቀሌ እጅግ ከፍተኛ የሚባል ቁጥር ያላቸው የትግራይ ተወላጆች ሲጨፍሩ፣ ሲዘሉ፣ ከበሮ እየመቱ የባህላቸውን ዘፈንና ውዝዋዜ ሲያወርዱ አይተናል። ምክንያቱ በግልጽ ባይነገርም ሲደበቅ የነበረው የህወሃት ሃብትና ንብረት ውጤት የሆኑ፣ በልዩ የመንግስት ድጋፍ የተከናወኑ ግዙፍ ተቋሞች በጎዳና ለህዝብ ሲቀርቡም ተስተውሏል። ልማቱ መልካም ነው። ደስ ይለናል። ምንም ተቃውሞ የለንም። ግን መልዕክት አለን። ለማን?ምሬትን፣ ጭቆናና መንገፍገፍ ሲበዛ በፍቃደኛነት በቦንብ ላይ እንደሚያስሮጥ ለሚያውቀው የትግራይ ህዝብ!! የትግራይ ህዝብ ስማ!!
… “የ100 ዓመት የቤት ስራ ሰጥተናቸዋል” በሚል በየድረገጹ የሚለጠፉ ተራ ድንፋታና ትዕቢት የሚፈጠሩትን ሓውዜኖች ከማብዛት ውጪ ትርፍ የላቸውምና ወደ ደጉ መንገድ መመለስና ሰብዓዊነትን በማስቀደም፤ ተደጋግፎ መኖርን ማጎልበት ይሻላል ለማለት እንወዳለን። ተሳስበውና ተረዳድተው የሚገነቡት የትም ሆነ የት የአገር ነውና ሁሉም ይኮራበታል፤ ይጠብቀዋል። ተጠቃሚ ይሆንበታል። የሚያምርብንም ይህ ነው። ህወሃት አልሰማም ብሏል። የትግራይ ህዝብ ግን ስማ!! ይህ ሁሉ የሚደረገው በስምህ ነው!! …

Tuesday, September 10, 2013

የ2005 ዋና ዋና ፖለቲካዊ ክንዉኖች


hailemariam


የመለስ ዜናዊ አስተሳሰብና ምግባር ሕዝብን በተለይም ፖለቲከኞችን በተራራቀ ተቃራኒ ጫፍ እንዳቆሙ መሞታቸዉ የኢትዮጵያን ፖለቲካ በበጎ ወይም በመጥፎ፥ ወይም በሁለቱም መሐል-ክፉኛ መንካቱ እንደማይቀር ያኔ ተብሎ ነበር። አሁንም አልቀረም።
የቀድሞዉ ጠቅላይ ሚንስትር ተሸኙ።
ሁለት ሺሕ አራትም ተሰናበተ። እና አዲስ ዓመት። ሁለት ሺሕ አምስት። ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ርዕሠ-ሊቃና ጳጳሳት እና፥ በአቶ መለስ ዜናዊ ሞት ማግስት የባተዉ ሁለት ሺሕ አምስት ካዲስ መሪ፥ ካዲስ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሹመት ጋር አዲስ ተስፋ አጭሮም ነበር። ዓመቱ ዛሬ-አርጅቶ ሊሰናበት ሁለት ቀን ቀረዉ። የዓመቱን የኢትዮጵያ አበይት ፖለቲካዊ ክንዉኖች እየጠቃቀስን፥ ተስፋዉ መጠዉለግ-መፅደቁን፥ ላፍታ እንቃኛለን። አብራችሁኝ ቆዩ።
መለስ በተቀበሩ በሳምቱ ሁለት ሺሕ አምስት እንደ አዲስ ዓመት ሲብት ሁለት የስዊድን ጋዜጠኞችን ጨምሮ በሺሕ የሚቆጠሩ እስረኞች በምሕረት መፈታታቸዉን የኢትዮጵያ መንግሥት ማወጁ፥ የአዲሱ ዓመት አዳዲስ መሪዎች አሮጌዉን ከፋፋይ መርሕ ከአሮጌዉ ዓመት ጋር ለማሰናበት ፍንጭ ማሳየታቸዉ መስሎ ነበር።
ከእስረኞቹ የመፈታት ዜና በተጨማሪ የኢትዮጵያ መንግሥት ከኦጋዴን ብሔራዊ ነፃዉጪ ግንባር (ኦብነግ) ጋር ለመደራደር መወሰኑን አስታዉቆም ነበር።ኦብነግ የመለስ ዜናዊ መንግሥት ለረጅም ጊዜ ባሽባሪነት የወነጀለዉ፥ ከሁለት ሺሕ ሁለት ጀምሮ ደግሞ ከአልቃኢዳ፥ ከአልሸባብ፥ እና ከሁለት ሐገር በቀል ድርጅቶች ጋር በሕግ-በአሸባሪነት የፈረጀዉ ቡድን ነዉ።semayawi rally
በዚሕም ሰበብ በመለስ ሞት ማግሥት አዳዲሶቹ መሪዎች ከኦብነግ ጋር ለመደራደር መስማማታቸዉን ሲያስታዉቁ፥ ለኢትዮጵያ ፖለቲካ አዲስ ተስፋ ማጫሩ አልቀረም። በአዲሱ ዓመት ዋዜማ ናይሮቢ ኬንያ ዉስጥ በኢትዮጵያ መከላከያ ሚንስትር ሲራጅ ፈርጌሳና በኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አዉጪ ግንባር የዉጪ ግንኙነት ሐላፊ በአብዱረሕማን መሕዲ መካካል የተደረገዉ ድርድር እንዲደረግ የወሰኑት አቶ መለስ ዜናዊ ከመሞታቸዉ በፊት መሆኑ ሲነገር ግን ተስፋዉ የአዲሱ ዓመት ፀጋ፥ የአዲሶቹ መሪዎችም ብልሕነት እንዳልሆነ ግልፅ ሆነ። እስረኞቹ የተለቀቁትም በመለስ ዉሳኔ እንደነበር ተነግሯል።
የሁለቱ ወገኖች ተደራዳሪዎች በድርድሩ ሥነ-ሥርዓታዊ ጉዳዮች ተስማምተዉ፥ ለመስክረም ማብቂያ ለሁለተኛ ዙር ድርድር ለመገናኘት ተቀጣጥረዉ ነበር። መንግሥት አማፂዉ ቡድን ሕገ-መንግሥቱን ካልተቀበለ አልደራደርም በማለቱ፥ አማፂዉ ቡድን ቅድመ ሁኔታዉን ባለመቀበሉ ቀጠሮዉ-በቀጠሮ ቀረ። ተስፋዉም ቢያንስ ለዚሕ ዓመት ተጨናጎለ።