Monday, February 18, 2013

የኦርቶዶክሱ “ክሩሴድ”/ “Crusade” የሚባል መርዝስ መች ይሆን የሚረጨው?

(ሕሊና ብርሃኑ)

abunePetros

በታላቁ ኢትዮጵያዊያችን አንደበት፣ ኢትዮጵያ ዛሬም ያለችበትን ከፍተኛ የሕልውና አደጋን ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ ያገናዝብ!

እንደ ግራዝያኑ፣ ማለትም ያቃጣል!

የዛሬው የኢትየጵያ መንግሥት ርሕራሄ የሌለውን በትሩን ያነሳው የተቃዋሚ የፖለቲካ ተቀናቃኞቹ ብቻ ላይ ሳይሆን፣ ሃይማኖት ኃይል ፖለቲካ፣ ለሰብዓዊ መብታቸው የቆሙ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ላይ ነው። ከኢትዮጵያ ታሪክ ጋር የቆየ ዕምነታቸውን ይዘው፣ ለሃይማኖት መብታቸው የሚሟገቱ ሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ሆኑ፣ ከኢትዮጵያ ታሪክ ጋር የተያያዘው የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ምዕመናኖችም ጭምር ነው። ትላንት /05.02.13/ ጀሃዳዊ ሃረካት በሚል ስም ሃገር፣ ህግና ወገን የሚያሰድብ፣ የሚያሳፍር፣ ለዘመናት ተቻችለው የኖሩትን ትላልቅ ሃይማኖቶችን ለማጋጨት የቅስቀሳ መርዙን በረጨ ማግስት፣ ዛሬ /13.02.13/ ደግሞ ከያን ሰሞን ሳይታሰሩ የተረፉ፣ለእምነት መብታቸው ወደ ፈጣሪያቸው የሚጮሁ የክርስትያን ባህታዊዎችን ከዋልድባ ገዳማቸው ተሰደው ከሚኖሩበት አካባቢ እየለቀመ ወደ እስር ቤት እየወረወረ ነው። ኧረ ለመሆኑ መቼ ይሆን እኛስ ክርስትያኖች ለሰብዓዊ መብቶቻችን፣ እንደሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ከኢትዮጵያ ታሪክ ጋር በቆዩት ዕምነቶቻችን እጅ ለእጅ ተያይዘን፣ ሚሊዮን ሆነን ለኢትዮጵያና ለሰብዓዊ መብታችን የምንነሳው፣ ላንድ አፍታ ቆም የምንለው?

ኧረ እስከመቼስ?

ዋይ በይ የጴጥሮስ ነፍስ!

ምንስ ከዚህ ይባስ …

ዋይ በይ የጴጥሮስ ነፍስ!
ምንስ ከዚህ ይባስ …

እስከ ዛሬስ ድረስ፣

ለሥጋዬ ብዬ አጎንብሼ ቻልኩት

ለካስ ነፍሴን ኖሯል የሚያፈላልጓት፣

ዋይ በይ የፔትሮስ ነፍስ እዚያው ባለሽበት
የኔንም እንዳንቺው ዛሬውኑ ጥሪያት፤
ይህን ሁሉ ምዓት ባይኔ ከማይበት፣
እንዲህ ባደባባይ ነፍሴን ሲያዋርዷት።

የለሽ መቀመጪያ፣ ማረፊያ እንደሆን ቤት
ቆም፣ በይ ላንዳፍታ፣
እስቲ ከዚያ በፊት
ሃውልትሽን በዚያው “ሰልጥነው” ሳይጥሉት፣
ሰቆቃሽን ላድምጥ በጸጋው አንደበት።
—–
ህዳር 17 2005 ዓ ም

No comments:

Post a Comment