Friday, February 8, 2013

ልዩነት አያስፈራም

የሚያስፈራውና የሚያሳፍረው በዚህ ላይ የተመሰረተው ድንቁርናና ማደንቆሪያ ነው

difference

ባለፉት 21 ዓመታት በልዩነት ላይ የተመሰረተው፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የተነዛው የዘረኝነት መርዝ ቀላል አይደለም። መላ ኢትዮጵያን ቀስ በቀስ እየወረረው መጥቶ ማሰብ ይችላል ተብሎ የሚጠበቅበትን፣ ጥቂት ያልሆነ “ምሁር” የሚባለውን ሁሉ ሳይቀር በነጻ ጭንቅላት እንዳያስብ እያደረገው ነው። ሰለሆነም ነው፣ ማሰብ የሚገባው እንደዚህ ካሰባ፣ የፖለቲካና የስለላ ማዕከሎች ጥናቶች፣ አልፈው ተርፈው ረዥም ታሪክ ያላትን ኢትዮጵያ ሃገራችንን ከእንግዲህ በሃያ ዓመታት ውስጥ ከሚወድቁት መንግስታት ተርታ ውስጥ ያስገቧት። ይህ መቼም፣ ሆነም አልሆነም፣ እራሱ መገመቱ እንኳን፣ እያንዳንዱን የዛሬውን የኢትየጵያ ሃገር ወዳድ ሊያሳስበው ብቻ ሳይሆን፣ ራሱን አስይዞ የሃሳብ ያለህ አሰኝቶ ሊያስጮኽው ይገባል። ደግሞም የመንግሥትንና የአባሪዋቹን ታሪካዊ አካሄድና ዛሬ የሚወስዱትን ኢትዮጵያን የማፈራረስ እርምጃዎች ላስተዋለ አይሆንም ብሎ መከራከር አይቻልም። ስለሆነም የችግሩን ስረ መሰረታዊ መንስኤ መረዳት ብቻ ሳይሆን፤ ሀገር ወዳድ ነኝ የሚል ሁሉ ከዳር እስከዳር አንድ ሆኖ መነሳትም አለበት።

የወንዝ ውሃ እያሳሳቀ ነው የሚወስደው !

ይህ እንዳይሆን፣ በዘረኝነት የተበከለውን የሰው ደካማን አስተሳሰብ፣ በመሰረታዊ ትክክለኛ ሃሳብ ለማደስም ጭምር፣ በዚህ በኩል በተጨባጭ ልምዶች የተደገፉ ለምሳሌነት የሚያግዙ እርማጃውችን ደግሞ ደጋግሞ ማስተጋባት ያስፈልጋል፣ ይጠቅማል። – ኢትዮጵያ ለዘላለም እንድትኖርና ህዝባችን በፍትህ፣ በሰላምና በአንድነት እንዲበለጽግ ለምናደርገው ትግል !

በዚህ አኳያ፣ እኔ የማደንቀው፣ የወንድሜ የኦባንግ ሜቶ ልምድና ሃሳቦች እንደምሳሌዎች የሚቀርቡ ናቸው እላለሁ። ስለሆነም ነው፣ እዚህ እንደገና (ሰንበት ያለም ቢሆን) ላንባቢ ለማሳሰብ የምወደው። (አባሪውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)

ኢትዮጵያ ሃገራችንን፣ በሃያ ዓመታት ውስጥ ይደርሳል ከተባለው አደጋ ለማዳንና ፣ መልሶ ለማቋቋም ዘሬውኑ መነሳት አለብን!

ሕሊና ብርሃኑ

 

 

No comments:

Post a Comment