Monday, February 25, 2013

ቀይ-ሽብር ሲጀምር

Red Terror

ቀይ-ሽብር ሲጀምር

ከደርግ ዲሞክራሲ

ከወያኔ እኩልነት……ከሰማይ ዳቦ ስንጠብቅ

ሰብዕናችን ተፍቆ

ማንነታችን ተንቆ…..ከዕምነታችን ስንርቅ

ውርደታችንን ተመልክተን፤

በቃ ማለት ካቃተን

ታስሮ መታረድ አይቀርም እንደ በግ ተጎትተን

—————–

ዘመናት አስቆጥራ

ብዙ ትውልድ ተሻግራ

መቃብር ዛፍ ሲያበቅል፤ የብሶቱ ቀን ሲርቅ

የደም አሻራ ሲጠፋ፤ የወላጅ እምባ ሲደርቅ

ያኔ ይመስለኝ ነበር ታሪክ እራሷን የምትደግም

ሕብረተ-ሰቡ ሲዘናጋ፤ ሰው ከሐዘኑ ሲያገግም

ለካ ተሳስቻለሁ!

መፃፍ፤ መናገር ሲከለከል:

ማሰር፤ ማሳደድ ሲጀመሩ

የሐሰት ዶኩሜንታሪ በቴሊቪዥን ሲሠሩ

በጋዜጣ ሲያስፈራሩ፤ በሬዲዮ ሲፎክሩ

የሰው በር እየሰበሩ

ቤት-ንብረት ሲበረብሩ

እንዲህ እያለ ነበር

ቀይ-ሽብርም ሲጀምር

Feb. 20, 2013

Yekanadaw Kebede

(Picture: washermansdog-ajnabi.blogspot.com)

 

No comments:

Post a Comment