Wednesday, February 27, 2013

ሞት በምልጃ፤ የበረሃ ጣዕር!

ማስለቀቂያ ካልተከፈለ – ኩላሊት ለገበያ

tigist gebre

“አቧራ ይጨሳል። ከዚያ ያፈኑትን ይዘው ይሰወራሉ” አስደንጋጩ ታሪክ ውስጥ ያለው ስዕላዊ ገለጻ ነው። አንድ ወቅት አዲስ አበባ የህጻናት ሌቦች ተበራክተው ነበር። በወቅቱ በርዳታ ስም ተመዝግበው የፈጣሪ ስም እየጠሩ ህጻናትን በመነገድ የከበሩ ወረበሎች በደንብ የተደራጁና የሚቀናቀናቸውን የማስወገድ አቅም ስለነበራቸው “አቧራው ጨሰ” የሚል ስያሜ የኮድ ስም ተሰጥቷቸው ነበር። አሁንም አሉ። “ህጻን እናሳድጋለን” እያሉ በዘረጉት ሰንሰለት የህጻናትን ደም የሚጠጡ “አንቱ” የተባሉ ሰዎች!! የውጪ አገር ዜጎች ጭምር …

በሱዳን ሰዎችን በማፈን ሲና በረሃ የሚሰውሯቸው ራሻይዳዎች የተደራጁ ናቸው። ከአረብ ምድር የፈለሱ ናቸው የሚባልላቸው እነዚህ ጎሣዎች በሱዳንና በኤርትራ የሚገኙ ሲሆን በተለይ በኤርትራ ያሉቱ ከዘጠኙ ጎሣዎች መካከል የሚቆጠሩ ናቸው፡፡ አኗኗራቸው የዘላን በመሆኑ ከኤርትራ መንግሥት ቁጥጥር ውጪ እንደሆኑ ይነገርላቸዋል፡፡ እነዚህ ጎሣዎች እጅግ አሰቃቂ የሆነ የአፈናና የጭከና ድርጊት ሲፈጽሙ በወጉ ታጥቀውና ዘመናዊ ተሽከርካሪ በመያዝ ነው። የሚታፈነውን ሰው ከተቆጣጠሩ በኋላ አዋራ ይነሳል። የሚከንፉበት ተሽከርካሪ አሸዋውን ተርትሮት ሲወረወር የሚነሳው ጭስ ሲበተን እነሱ የሉም። ቀሪው ተግባር “ሚስትህን፣ ወንድምህን፣ እህትሽን፣ ዘመድሽን ለሚያርዱ የሰውነት ክፍል ሌቦች አሳልፈን ሳንሰጥ ዶላር ክፈል ወይም ክፈይ” የሚለው ድርድር ነው። ይህ ድራማ መሰል ንግድ ሲከናወን ተገደው ይሁን የንግዱ ተባባሪ በመሆን በውል በማይታወቅ ሁኔታ የድርድሩ አስተርጓሚ ሆነው የሚሰሩት ኤርትራዊያን እንደሆኑ ተሰምቷል። ኢትዮጵያዊያኖችም አሉበት ይባላል። ማንም ይስራው ማን ድርጊቱ አሰቃቂ መሆኑ ብዙዎችን አስለቅሷል። አስጨንቋል።

በደላሎች እስራኤል ለመግባት ጉዞ ከጀመሩት ወገኖች መካከል ስንቶቹ በሲና በረሃ ሟምተው እንደቀሩ መረጃ የለም። ከሱዳን ምድር ወጥተው ግብጽ በመሻገር ሲና በረሃ እንደ ከብት ተበልተው የሚጣሉት ወገኖች ስቃይ ለሰሚው ግራ ነው። ወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው አሰቃቂ መከራ ከቀን ቀን እየተባባሰ ነው። አሰቃቂ ዜናዎች መስማት ለየእለቱ የሚያስፈልገን መሰረታዊ ጉዳይ እስኪመስል ተለመዷል። ይህ አሳሳቢ ጉዳይ “እስከመቼ በዚህ ይቀጥላል” የሚለው የሁሉም ወገን “ዳር ቋሚዎች” ጥያቄ ነው።

“ለጆሮ የሚሰለች ነው፣ እርዳታ መስጠት ታከተን፣ የሚል መልስ የሚሰጡ አጋጥመውኛል። ድርጊቱ ተደጋግሞ ለጆሮ የሚያሰለች ደረጃ እስኪደርስ እነዚህ ወገኖች የት ነበሩ? ቢያንስ ሌሎች ላይ ተመሳሳይ ችግር እንዳይደርስ ምን ሰሩ? በውጪ አገር ያለን ወገኖች የሚረዳውንና የማይረዳውን መለየት የተሳነን ይመስለኛል” በማለት በሚኔሶታ የሚኖሩት ወ/ሮ ሰብለ አስተያየታቸውንና ተማጽኗቸውን ያሰማሉ።

Monday, February 25, 2013

ህወሃት ሊወድቅ ነው

(ለነጻነታችን እንጨክን ፡ እንቆሽሽ!)

TPLF-Logo

ገዢው ፓርቲ ለጥገናዊ ለውጥ ምንም አይነት ቦታ የማይሰጥ መሆኑን በተደጋጋሚ ግልጽ አድርጓል። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትርም ይህንኑ ጉዳይ አስምረውበታል። ከዚህ የተነሳ ከገዢው ፓርቲ ጋር የነበረው የምርጫ ትግል በአጠቃለይ መክኗል። ዛሬ አገራችን ሙሉ በሙሉ ወደ ነጻነት ትግል ምዕራፍ ገብታለች።

ፓለቲካ አይነት ፡ አይነት አለው። የምርጫ ፓለቲካ እና የነጻነት ፓለቲካ አንድ አይደሉም። የምርጫ ፓለቲካ ንጹህ ነው ፡ ጭምት ነው። የነጻነት ፓለቲካ ግን ይጨክናል ፡ ይቆሽሻል።

የአገራችን ዘመናዊ የፓለቲካ ታሪክ ሲቃኝ በተደጋጋሚ የሚታየው ፡ ባለፉት 40 ዓመታት አብይ ለውጥ አራማጆች ከየዋህነታቸው እና ከንጹህ የፓለቲካ ስልታቸው የተነሳ ለአገራቸው የነበራቸው ራዕይ ተጨናግፏል ፡ መክኗል ፤ ኢትዮጵያ ያፈራቻቸው ብዙ ታላላቅ ሊሂቃኖቻችንም በከንቱ ጠፍተዋል።

ካለፉት ያልተሳኩ የነጻነት ሙከራዎች ተምረን ፡ አሁን ያለውን ትልቅ የነጻነት ዕድል በተሳካ መልኩ ለመጠቀም ከፈለግን ፡ ለነጻነታችን መጨከን እና መቆሸሽ አማራጭ የሌለው መንገድ ሆኗል።

ሙከራ 1፦ መንግስቱ እና ገርማሜ ነዋይ

አፄ ኃይለስላሴ ላይ ተደርጎ የነበረው የ1953 ዓ.ም የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ አራማጆች ፡ ወንድማማቾቹ መንግስቱ ነዋይ እና ገርማሜ ነዋይ ፡ ውጥናቸው ለምን እንደ መከነ ሲመረመር ዋናው ምክንያቱ ንጹህና ጭምት የፓለቲካ ስልት ነው።

የንጉሳዊው ስርዓት በኢትዮጵያ ጭሰኛ ላይ ያደርግ የነበረውን ጭቆና ችላ ማለት ያልቻሉት ወንድማማቾች ፡ ንጉሱን ከስልጣን አስወግደው ፍትሃዊ የመንግስት እና የምጣኔ ሃብት ስርዓት ለመቅረጽ መመኘታቸው ድንቅ ነበር።

ሆኖም ግን እቅዳቸው ያልበሰለ ፡ ያልጨከነና ለመቆሸሽ ያልደፈረ ነበር። ከዚያም የተነሳ መፈንቅለ መንግስቱ ከሸፈ። መግደል የነበረባቸውን በጊዜው አለመግደላቸው ፡ ማሳተፍ የነበረባቸውን ባለማሳተፋቸው ፡ መቅደም የነበረባቸውን ባለመቅደማቸው የተነሳ የነበራቸው ራዕይ ተኮላሽቷል። የመፈንቅለ መንግስቱ ጠንሳሾች የዋህነታቸውና ፡ ንጹህነታቸው አስበልቷቸዋል።

ቀይ-ሽብር ሲጀምር

Red Terror

ቀይ-ሽብር ሲጀምር

ከደርግ ዲሞክራሲ

ከወያኔ እኩልነት……ከሰማይ ዳቦ ስንጠብቅ

ሰብዕናችን ተፍቆ

ማንነታችን ተንቆ…..ከዕምነታችን ስንርቅ

ውርደታችንን ተመልክተን፤

በቃ ማለት ካቃተን

ታስሮ መታረድ አይቀርም እንደ በግ ተጎትተን

Tuesday, February 19, 2013

“ጭንጋፍ (ምቱር) ፓትርያርክ”

(በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ)

Abuna's Residence (Patriarch of Ethiopian Church), Addis Ababa, Ethiopia

የካቲት ፳፩ ስለሚወለደው ፓትርያርክ ስናስብ ከአቡነ ጳውሎስ የተለየ ሆኖ እናገኘዋለን። አቡነ ጳውሎስን ይህ መንግስት ከሜዳ አግኝቶ በማደጎ አሳደጋቸው እንጅ ጸንሶ የወለዳቸው አይመስሉም። ይህን ለማለት ያስገደደኝ፤ እርቁ እንዲጀመር በፈቀዱት በአቡነ ጳውሎስ ላይ አቶ ስብሀት ነጋ “እርቁ እንዲጀመር በመስማማታቸው ተሳስተዋል” ብለው በወረወሩባቸው ትችት እራሱ የወያኔ መንግስት አቡነ ጳውሎስን የጉዲፈቻ ልጅ አድርጓቸዋል። የኢ.ህ.ዴ.ግ. ልጅ መስለው የተገኙት በቦታው ከተሰየሙ በኋላ ነውና ማደጎ ነበሩ ማለት ነው። ይህ ዛሬ ሊወለድ ነው ተብሎ የተነገረን ፓትርያርክ ከአቡነ ጳውሎስ ለየት ያለ ኢ.ህ.ዴ.ግ.ን በጫካ በነበረበት ጊዜ በአካሉ በሥጋውና በነፍሱ አስመሎ ይወልደው ዘነድ የጸነሰ ነው። (ሙሉው ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል)

Monday, February 18, 2013

የኦርቶዶክሱ “ክሩሴድ”/ “Crusade” የሚባል መርዝስ መች ይሆን የሚረጨው?

(ሕሊና ብርሃኑ)

abunePetros

በታላቁ ኢትዮጵያዊያችን አንደበት፣ ኢትዮጵያ ዛሬም ያለችበትን ከፍተኛ የሕልውና አደጋን ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ ያገናዝብ!

እንደ ግራዝያኑ፣ ማለትም ያቃጣል!

የዛሬው የኢትየጵያ መንግሥት ርሕራሄ የሌለውን በትሩን ያነሳው የተቃዋሚ የፖለቲካ ተቀናቃኞቹ ብቻ ላይ ሳይሆን፣ ሃይማኖት ኃይል ፖለቲካ፣ ለሰብዓዊ መብታቸው የቆሙ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ላይ ነው። ከኢትዮጵያ ታሪክ ጋር የቆየ ዕምነታቸውን ይዘው፣ ለሃይማኖት መብታቸው የሚሟገቱ ሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ሆኑ፣ ከኢትዮጵያ ታሪክ ጋር የተያያዘው የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ምዕመናኖችም ጭምር ነው። ትላንት /05.02.13/ ጀሃዳዊ ሃረካት በሚል ስም ሃገር፣ ህግና ወገን የሚያሰድብ፣ የሚያሳፍር፣ ለዘመናት ተቻችለው የኖሩትን ትላልቅ ሃይማኖቶችን ለማጋጨት የቅስቀሳ መርዙን በረጨ ማግስት፣ ዛሬ /13.02.13/ ደግሞ ከያን ሰሞን ሳይታሰሩ የተረፉ፣ለእምነት መብታቸው ወደ ፈጣሪያቸው የሚጮሁ የክርስትያን ባህታዊዎችን ከዋልድባ ገዳማቸው ተሰደው ከሚኖሩበት አካባቢ እየለቀመ ወደ እስር ቤት እየወረወረ ነው። ኧረ ለመሆኑ መቼ ይሆን እኛስ ክርስትያኖች ለሰብዓዊ መብቶቻችን፣ እንደሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ከኢትዮጵያ ታሪክ ጋር በቆዩት ዕምነቶቻችን እጅ ለእጅ ተያይዘን፣ ሚሊዮን ሆነን ለኢትዮጵያና ለሰብዓዊ መብታችን የምንነሳው፣ ላንድ አፍታ ቆም የምንለው?

Saturday, February 16, 2013

ኢህአዴግ ሌላ፤ ኢትዮጵያችን ሌላ!!

(ርዕሰ አንቀጽ)

smne banner1

ሚዲያ ከስሜታዊነት፣ ከስጋና ደም ድምር፣ ከችኩል ውሳኔና ግብታዊነት ነጻ ለመሆን ሌት ተቀን መስራት እንዳለበት ባለሙያዎች አበክረው የሚናገሩት ዓቢይ ጉዳይ ነው። ሚዲያ ስንል ደግሞ ሁሉንም ነው – የኅትመት፣ የምስል፣ የድምጽ፣ የድረገጽ፣ የዲጂታል፣ የማኅበራዊ ድረገጽ፣ … ። ሁሉም ሚዲያዎች አሻግሮ በማየት ህዝብንና አገርን የመጠበቅ ኃላፊነት አለባቸው። ጋዜጠኞች ወይም እንደ ጋዜጠኛ የሚሠሩ ሁሉ ከየትኛውም ሙያተኛ በላይ ሃላፊነት ሊሰማቸውም ግድ ነው። ለዚህም ነው በጋዜጠኝነት ሙያ “አመጣጥን፣ አሁንም አመጣጥን፣ አሁንም አመጣጥን … “ባላንስ” አድርግ” የሚባለው!!

ከኢህአዴግ ዓይነ ያወጣ ውሸትና ዝግነት የተነሳ ሁሉንም መረጃዎች የማመጣጠኑ ሙያዊ ሃላፊነት ለመወጣት ፈተና ቢያጋጥምም በከፍተኛ ደረጃ ጥንቃቄ ልንወስድባቸው የሚገባን ጉዳዮች አሉ። ከነዚህ ጉዳዮች መካከል አንዱና ዋናው የሃይማኖት ጉዳይ ነው። እውነት ለመናገር አሁን ባለው የሃይማኖት ውዝግብ ህዝብ ግራ ተጋብቷል። መሰላቸቱንም እየገለጸ ነው። ሲመረው “አረ መግዱ” ሊል ይችላል። ይህንን የሚለው ደግሞ የማይደግፈው ብቻ ሳይሆን እየተደገፈና እየተሞካሸ ያለው ሊሆን ይችላል፡፡ ሁሉም ወገን!!

እንደሚታወቀው አገራችንን ሊጠብሳት እያዘጋጃት ያለው የ”ጎሳ ፖለቲካ” ደራሲውና ቀማሚ በሞት ቢለዩም የሚያበርደው አስተዋይ መሪ አልተገኘም፡፡ በማስተዋል ማርከሻውን ለሚቀምሙም በቂ ጆሮ አልተሰጣቸውም – ጩኸቱ እጅግ ያደነቁራልና። ከውጪም ከውስጥም የሚረጨው የጎሳና የ”ደም” መርዝ ሳያንስ አሁን ደግሞ በሃይማኖት ተንተርሶ የተጀመረው አለመግባባት አስደንጋጭ ይዘት እንዳለው አያጠያይቅም። ተወደደም ተጠላም ያስፈራል። ኢህአዴግ ባቀናበረው “የድርሰት” ፊልም መነሻ ሳይሆን በበርካታ መረጃዎች የተደገፈ ማሳያ ማቅረብ ይቻላል።

ሁሉም ችግሮች በሰለጠነ መንገድ መፈታት የሚችሉ ቢሆንም ኢህአዴግ በሚከተለው “የደንቆሮና ድንቁርና የወለደው (አስፈሪ) የፍርሃት ፖለቲካ” ሳቢያ ነገሮች እየተካረሩ አገርና ህዝብ ላይ ሲያነጣጥሩ ማየት ተለምዷል። በሌላ አነጋገር በኢህአዴግ ግትርነትና “ያለ እኔ” በሚል በሚከተለውና ራሱም ባመነበት “የበሰበሰ አስተሳሰብ” የተነሱ ችግሮች ተጠራቅመው መጨረሻቸውን ህዝብና አገር ላይ አድርገዋል። በተለያዩ ቦታዎች የደረሰውን አሰቃቂ መከራ፣ ግድያና መፈናቀል አንዘነጋውም። ኢህአዴግ አልሰማ ብሎ ኤርትራን ከኢትዮጵያ በላይ አፍቅሮ የማይረሳ የታሪክ ዋጋ አሳጥቶናል። ተቆጥሮ የማያልቅ የኢኮኖሚ ኪሳራ አድርሶብናል። በወንድሞቻችንና በጭቁን ህዝብ ደምና አጥንት ፈርዷል። ብዙ፣ ብዙ፣ እጅግ ብዙ፣ … ኢህአዴግ ክፋቱና አረመኔነቱ ተዘርዝሮ አያልቅም። በበርካታ ምክንያቶች ኢህአዴግን እንቃወማለን፤ አጥብቀን እናወግዛለን፤ ለሥርዓቱ መለወጥ እና ለፍትሕ እንታገላለን። በኢትዮጵያችን ግን አንጫወትም። በኢህአዴግ መወገድና ማስወገድ ሰበብ ግን በጭፍን በኢትዮጵያችን ላይ አንቀልድም። ኢህአዴግ ሌላ፤ ኢትዮጵያችን ሌላ!!

“ኢህአዴግ አንገቱን ታንቋል”

ዓለም ባንክ ርምጃ ለመውሰድ ጫፍ ደርሷል

inspection panel and world bank

/ዜና ጎልጉል/ ኢህአዴግ ላይ ቀደም ሲል ሲቀርቡበት ከነበሩት ሪፖርቶች በተለየ ጥቅሞቹ ላይ ያነጣጠሩ አስደንጋጭ መረጃዎች እንደወጡበት ተሰማ። መረጃው የኢህአዴግን አንገት የማነቅ ያህል እንደሚቆጠርና ለተግባራዊነቱ የተንቀሳቀሱትን አካላት “የአስተዋይነት” ትግል ውጤት እንደሆነ ተጠቁሟል።

ኢህአዴግ በህዝብ ስም በብድርና በርዳታ የሚያገኘውን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለፖለቲካ ስራ እንደሚያውለውና ለአፈና ተቋማቱ ማጠናከሪያ እንደሚጠቀምበት የተከሰሰበት ሪፖርት መጠናቀቁን የገለጹት የጎልጉል ታማኝ ምንጮች ናቸው። ምንጮቹ እንዳሉት ሪፖርቱ የቀረበለት የዓለም ባንክ በቅርቡ መረጃውን ተቀብሎ ርምጃ ይወስዳል ተብሎ ይጠበቃል። ኢህአዴግ ርምጃው ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ለማክሸፍ የተለመደውን ሩጫ መጀመሩ ተሰምቷል።

በኢህአዴግ ላይ የቀረበው ሪፖርት የመፍትሄ ሃሳብም ያካተተ እንደሆነ የተናገሩት የጎልጉል ምንጮች፣ የዓለም ባንክ የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ሪፖርቱን ሙሉ በሙሉ እንደሚቀበለውና ይፋ እንደሚያደርገው አስረድተዋል። የምርመራ ዘገባውን ስላጠናውና ስላቀረበው የኢንስፔክሽን ተቋምና የስራ ተሞክሮ በቂ ግንዛቤ ያላቸው እነዚህ ክፍሎች እንደሚሉት የዓለም ባንክ ቦርድ ይህ ተቋም ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ያቀረባቸውን ሪፖርቶች ላለመቀበል አንገራግሮ እንደማያውቅ ያስረዳሉ።

በሚመሩት ህዝብ ላይ ግፍ የሚፈጽሙ መንግስታትና በልማት ስም የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚያካሂዱ አገራት የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በስፍራው በመገኘትና መረጃዎችን ከመሠረታቸው ዘልቆ በመመርመር አጥንቶ ተጠያቂ የሚያደርገው ኢንክሉሲቭ ዴቨሎፕመንት ኢንተርናሽናል Inclusive Development International (IDI) የሚባለው ተቋም ከኢትዮጵያውያኑ ሰለባዎች ውክልና በመውሰድ ስራውን ለማከናወን እንቅስቃሴ መጀመሩን ጎልጉል ምንጮቹን በመጥቀስ መዘገቡ ይታወሳል። ተቋሙም በውክልናው መሰረት ለኢንስፔክሽን ፓናል በዝርዝር የሰለባዎቹን በደል በማተት አሳውቆ ነበር።

ኢህአዴግ በርዳታና በብድር የሚያገኘውን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለፖለቲካ ስራ፣ ለአፈና፣ ለወታደራዊ አቅም ግንባታ፣ ለተለያዩ የአፈና ተቋም ሰራተኞቹ ደሞዝና ህዝብን በመርገጥ ስርዓቱን ለሚንከባከቡ የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችን በመክፈል ገንዘቡን ለመጠቀም ከታለመለት ዓላማ ውጪ እንደሚያውለው በበርካታ መረጃዎች ያረጋገጠው የኢንስፔክሽን ቡድን ለዚሁ ስራው ኬንያ፣ ደቡብ ሱዳንና ኢትዮጵያ በቅርቡ አቅንቶ ነበር።

ምርመራው ያስደነገጠው ኢህአዴግ በተለያየ መልኩ ሰለባዎች በደላቸውን እንዳይናገሩ፣ በጥቅም የተደለሉ ሰዎችን በየቦታዎቹ በማዘጋጀትና በማስፈራራት አፈና ማካሄዱን የጎልጉል የመረጃ ምንጮች በወቅቱ ቢያስታውቁም ጎልጉል መረጃውን ለስራው መሳካት ሲባል ይፋ ከማድረግ ተቆጥቧል።

ከቀናት በፊት ሪፖርቱን አጠናቆ ለዓለም ባንክ ቦርድ ያቀረበው የኢንስፔክሽን ቡድን (ፓናል) በማያወላዳ መንገድ ተጽኖ ፈጣሪ ተቋም መሆኑንን ያስረዱት ለስራውና ለተቋሙ ቅርበት ያላቸው ክፍሎች፣ ሪፖርቱን ከቦርዱ አባላት አንዱ እንኳ አልቀበልም ቢሉ ምን ሊከሰት እንደሚችልም አብራርተዋል።

“አንድ ወይም ከአንድ በላይ የቦርድ አባላት የፓናሉን ሪፖርት ውይይት እንዲደረግበት እስካልጠየቁ ድረስ ፓናሉ ባቀረበው መሠረት እንዳለ ይጸድቃል። ከጸደቀም በኋላ ሪፖርቱ በዓለም ባንክ ስም ይፋ ይሆናል። ሪፖርቱ ታምኖበት ይፋ ከሆነ በሪፖርቱ የቀረቡት የመፍትሄ ጭብጦች ተግባራዊ ከማድረግ ውጪ ሌላ አማራጭ የለም። እስካሁን ባለው አሰራር የፓናሉ ሪፖርት ተቃውሞ አጋጥሞት አያውቅም” ሲሉ መልስ ሰጥተዋል።

“ይህ ታላቅ ውጤት የተገኘው በእቅድና አስተውሎ በመራመድ ነው። ወደፊትም በቀጣይ የሚከናወኑ ተግባራቶች አሉ። የአገዛዙን ትምክህትና ማን አለብኝነት የሚያረግቡ፣ ብሎም የሚያተኑ ስራዎች ለመስራት ለተጀመረው ስራ ይህ ውጤት ከፍተኛ መነቃቃት ይሆናል” ሲሉ ጉዳዩን በቅርበት በመከታተል እዚህ ያበቁት ክፍሎች አስረድተዋል።

Wednesday, February 13, 2013

በአልቃይዳ ሰበብ ቻይናን መቆጣጠር


የኦባማ አስተዳደር መጪው የአፍሪካ ዕቅድ

 
February 13, 2013 10:11 am By  Leave a Comment

የአገራቸውን አጠቃላይ ሁኔታ እና መጪው ጊዜ ምን እንደሚመስል፤ የአገራቸውን የወደፊት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ፣ … ሁኔታ እንዲሁም አሜሪካ በቀጣይ ዓመታት የምትከተለውን የአጭርና የረጅም ጊዜ የውጪ ፖሊሲ ዕቅድ በተመለከተ ለሁለተኛ ጊዜ ከተመረጡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ማክሰኞ ምሽት ለምክርቤቱ ንግግር ያደረጉት ፕሬዚዳንት ኦባማ በርካታ ጉዳዮችን ዳስሰዋል፡፡ አፍሪካና ቻይናም የንግግራቸውን ሙሉ ቀልብ የሳቡ ነበሩ ባይባልም ሳይጠቀሱ አልታለፉም፡፡ በተለይ ስለአፍሪካ እንዲህ ብለዋል፤-


‹‹… የተለያዩ አፍቃሪ የአልቃይዳ ወኪሎችና አክራሪዎች ከአረብ ምድር እስከ አፍሪካ ብቅ እያሉ መጥተዋል፤ እነዚህ ቡድኖች ሊያመጡ የሚችሉት አደጋ እንደዚያው እያደገ መጥቷል፡፡ ይህንን አደጋ ለመቋቋምም በአስር ሺዎች የሚጠጉ ልጆቻችንን በመላክም ሆነ አገራትን መቆጣጠር አያስፈልገንም፡፡ ይልቁንም እንደ የመን፤ ሊቢያ እና ሶማሊያ ያሉት አገሮች የራሳቸውን ደኅንነት እንዲያጠናክሩ እንረዳቸዋለን፤ በማሊ እያደረግን እንዳለነው አሸባሪዎችን እየተዋጉ ያሉትን ወዳጆቻችንንም እንደግፋለን፡፡ እንደአስፈላጊነቱም ባለን አቅም ሁሉ በአሜሪካውያን ላይ አደጋ ሊጥሉ በሚችሉ አሸባሪዎች ላይ ቀጥተኛ እርምጃ እንወስዳለን፡፡›› የማሊ ጉዳይ
የፈረንሣይ ወታደሮች ባማኮ ማሊ አየርማረፊያ (ፎቶ: ሬውተርስ)
በአፍሪካዊቷ ማሊ እየተከሰተ ያለው ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ሆኗል፡፡ አሸባሪነትን ማክሸፍ አለብን ብለው የተነሱት ምዕራባውያን ማሊን ከተለያየ አቅጣጫ እያዋከቧት ይገኛሉ፡፡ የቀድሞ ቅኝ ገዢዋ ፈረንሳይ ጦር በመላክ ውጊያውን እየመራች ነው፡፡ ሁሉም እየተጫወቱት ያለው ሙዚቃ ‹‹በአሸባሪነት ላይ ጦርነት ከፍተናል›› የሚል ነው፡፡
እንግሊዝ ጦርነቱ ረጅም ጊዜ ቢፈጅም በዚሁ መቀጠል እንዳለበትና አስፈላጊውም ሁሉ መስዋዕትነት መከፈል አንዳለበት በየሚዲያው እያስተጋባች ትገኛለች፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ዴቪድ ካሜሮን የማሊው ቀውስ ‹‹ወራትን የሚጠይቅ ምላሽ ሳይሆን ዓመታትን እንዲያውም አስርተ ዓመታትን የሚጠይቅ›› እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡ ይህንኑ የአገራቸውን ሃሳብ በመደገፍ የብሪታኒያ ልዩ ኮማንዶ ወደ ማሊ በመሄድ የፈረንሣይን ጦር የሚያግዝ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም ሰው ዓልባ የቦምብ ጥቃትና የአየር ላይ ስለላም ታካሂዳለች፡፡

Friday, February 8, 2013

ልዩነት አያስፈራም

የሚያስፈራውና የሚያሳፍረው በዚህ ላይ የተመሰረተው ድንቁርናና ማደንቆሪያ ነው

difference

ባለፉት 21 ዓመታት በልዩነት ላይ የተመሰረተው፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የተነዛው የዘረኝነት መርዝ ቀላል አይደለም። መላ ኢትዮጵያን ቀስ በቀስ እየወረረው መጥቶ ማሰብ ይችላል ተብሎ የሚጠበቅበትን፣ ጥቂት ያልሆነ “ምሁር” የሚባለውን ሁሉ ሳይቀር በነጻ ጭንቅላት እንዳያስብ እያደረገው ነው። ሰለሆነም ነው፣ ማሰብ የሚገባው እንደዚህ ካሰባ፣ የፖለቲካና የስለላ ማዕከሎች ጥናቶች፣ አልፈው ተርፈው ረዥም ታሪክ ያላትን ኢትዮጵያ ሃገራችንን ከእንግዲህ በሃያ ዓመታት ውስጥ ከሚወድቁት መንግስታት ተርታ ውስጥ ያስገቧት። ይህ መቼም፣ ሆነም አልሆነም፣ እራሱ መገመቱ እንኳን፣ እያንዳንዱን የዛሬውን የኢትየጵያ ሃገር ወዳድ ሊያሳስበው ብቻ ሳይሆን፣ ራሱን አስይዞ የሃሳብ ያለህ አሰኝቶ ሊያስጮኽው ይገባል። ደግሞም የመንግሥትንና የአባሪዋቹን ታሪካዊ አካሄድና ዛሬ የሚወስዱትን ኢትዮጵያን የማፈራረስ እርምጃዎች ላስተዋለ አይሆንም ብሎ መከራከር አይቻልም። ስለሆነም የችግሩን ስረ መሰረታዊ መንስኤ መረዳት ብቻ ሳይሆን፤ ሀገር ወዳድ ነኝ የሚል ሁሉ ከዳር እስከዳር አንድ ሆኖ መነሳትም አለበት።

የወንዝ ውሃ እያሳሳቀ ነው የሚወስደው !

ይህ እንዳይሆን፣ በዘረኝነት የተበከለውን የሰው ደካማን አስተሳሰብ፣ በመሰረታዊ ትክክለኛ ሃሳብ ለማደስም ጭምር፣ በዚህ በኩል በተጨባጭ ልምዶች የተደገፉ ለምሳሌነት የሚያግዙ እርማጃውችን ደግሞ ደጋግሞ ማስተጋባት ያስፈልጋል፣ ይጠቅማል። – ኢትዮጵያ ለዘላለም እንድትኖርና ህዝባችን በፍትህ፣ በሰላምና በአንድነት እንዲበለጽግ ለምናደርገው ትግል !

በዚህ አኳያ፣ እኔ የማደንቀው፣ የወንድሜ የኦባንግ ሜቶ ልምድና ሃሳቦች እንደምሳሌዎች የሚቀርቡ ናቸው እላለሁ። ስለሆነም ነው፣ እዚህ እንደገና (ሰንበት ያለም ቢሆን) ላንባቢ ለማሳሰብ የምወደው። (አባሪውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)

ኢትዮጵያ ሃገራችንን፣ በሃያ ዓመታት ውስጥ ይደርሳል ከተባለው አደጋ ለማዳንና ፣ መልሶ ለማቋቋም ዘሬውኑ መነሳት አለብን!

ሕሊና ብርሃኑ