Thursday, November 29, 2012

ኢትዮጵያ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ምርት እድገት አሳየች!

    

አቤ ቶኪቻው

ኢትዮጵያ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ምርት እድገት አሳየች!

አቶ ሃይለማም ሲፈሩ ሲተቡ ቆይተው ዛሬ የካቢኔ ሹመት ለማደረግ ፓርላማ ብቅ ብለው ነበር አሉ። ይዘዋቸው ከመጡዋቸው ካቢኔዎቻቸው መካከል ሌላ ሁለት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮችን ይገኙበታል።

አቶ ሃይለማሪያም ሲያስቡት ሲያስቡት ለአቶ ደመቀ ብቻ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነቱን መስጠት አይችሉትም ብለው ሰጉ መሰለኝ…(መሰለኝ ነው ያልኩት) ዛሬ አቶ ሙክታር ከድር እና አቶ ደብረ ፅዮን ገብረሚካኤልን ደጋፊ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አድርገው አሹመዋል። በጥቅሉ በአሁኑ ሰዓት ሀገራችን ሶስት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች አሏተው።

እኛ ሹመቱን ከላይ ከላይ የምናየው የመንግስታችን አድናቂዎች “እሰይ ሀገራችን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እድገት እመርታ አሳየች” ብለን ካገኘን ፅዋ ካጣን ደግሞ ግንባራችንን እያጋጨን ደስታችንን እንገልፃናል።

የምር ግን አቶ ሃይለማሪያም ያኔ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ይሰሩ የነበረ ጊዜ እንደው ሰውየው መለስ ሆነውባቸው “ተሸከሙ” ያሏቸውን ሁሉ “እሺ ጌታዬ” ይሏቸው ነበር እንጂ፤ የጫኑባቸው ሸክም በእጅጉ ከብዷቸው ነበር ማለት ነው!? አዎና ይኸው አቶ ደመቀ ሸክሙን አይችሉትም ብለው የጠረጠሯቸው ከራሳቸው ልምድ ተነስተው አይመስልዎትም!?

ሌላው ጥርጣሬ የኢህአዴግ “ፈላጭ ቆራጮች” (ይሄ “ፈላጭ ቆራጭ” የሚለው ቃል ኢህአዴግ ይፈልጣል ይቆርጣል ብሎ ለማሽሟጠጥ ታስቦ የገባ ቃል አለመሆኑን በቅንፍ አሰውቀን እንቀጥል) እና የኢህአዴግ ፈላጭ ቆራጮች አቶ ሃይለማሪያምን ለአንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ብቻ አምነው መተው ምቾት አልተሰማቸውም ይሆናል!

ለማንኛውም ዶክተር ቴውድሮስ አድሃኖምን ውጪ ጉዳይ ሚኒስትርነት ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል። ዶክተሩ ከጤና ጥበቃ የተነሱት ጤና ስለነሱ ይሁን ወይስ የውጭ ጉዳዩ ስራ ህክምና ስለሚያስፈልገው አልታወቀም። ሲታወቅ እናወጋዋለን!

 

 

አፈናው ከበረታ ገና በ“ፓፒረስ”ላይ እንጽፋለን!

 

አፈናው ከበረታ ገና በ“ፓፒረስ”ላይ እንጽፋለን!

ብሩክ ከበደ

ኢህአዴግ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረ በኋላ የምዕራባውያኖቹን ቀልብ ለመሳብ የሶሻሊዝም ካባውን በብርሃን ፍጥነት አውልቆ የመናገርና የመፃፍ መብትን “ሲፈቅድ” አስቦበትና ቆርጦ እንዳልነበር በዛወቅትም ሆነ አሁን ፕሬሱ ላይ የሚያደርሰውና እያደረሰ ያለው ችግር በቂ ምስክር ነው፡፡ ለስልጣናቸው መደላደልና ለርዳታ ፍጆታ ሲሉ “ፈቅደናል” ማለታቸው ያፀደቁትንም ሆነ የሕሊናን (equity) ሕግ እንዲደፈጥጡ አስችሏቸዋል፡፡

ሕዝብ የማወቅና የማሳወቅ መብቱ ሙሉ ለሙሉ እንዲገፈፍ በየወቅቱ የተለያዩ “ውሃ አይቋጥሬ” ምክንያቶች እየተፈጠሩ አፋኝ እርምጃዎች ተወስደዋል፡፡ በዚህ ተቃርኖአዊ አያያዝም በርካታ ጋዜጠኞች ታስረዋል፣ ተደብድበዋል፣ ተሰደዋል፣ ራሳቸውን አጥፍተዋል፡፡ ምንም ነገር ባልተሟላለትና በማይሟላለት ነፃ ፕሬስ ዙሪያም ለተሰባሰቡ ጋዜጠኞች ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች ማህበር ከአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ቀዳሚ የሆነውን ሽልማት ለኢነጋማ (አቶ ክፍሌ ሙላት ይመሩት ለነበረው ማህበር) መስጠቱ በዚያ አስቸጋሪ ሁኔታ ሳይበገሩ ይሰሩ ለነበሩት የነፃው ፕሬስ አባላት እውቅና የሰጠ ነበር፡፡

የእስላም ኢትዮጵያውያን የትግል ስልት

 

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

muslim ethiopians

በአለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ እስላም ኢትዮጵያውያን ማካሄድ የጀመሩት ትግል በዓይነቱም፣ በስፋቱም፣ በአስተሳሰቡም፣ በስሜቱም እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ ውስጥ ከአገዛዙ ጋር ከተደረጉ ትግሎች በጣም የተለየ ነው፤ በመጀመሪያ ደረጃ ትግሉ ለሃይማኖት ነጻነት ነው፤ ስለዚህም በአገዛዙ በኩል የፖሊቲካ ዓላማና የፖሊቲካ መልክ እየተሰጠው ሲሆን በእስልምና ምእመኖቹ በኩል ግን ትግሉን ከፖሊቲካ የጸዳ ለማድረግ ግሩም የሆነና የተሳካ ጥረት እያደረጉ ነው፤ ሁለተኛ የትግሉ ስልት ፍጹም ሰላማዊ በመሆኑ የአገዛዙን የጉልበት ስልት እያከሸፈ ያጋለጠው ይመስላል፤ አንዱና ዋነኛው የትግሉ ሰላማዊነት መግለጫ በቤተ መስጊድ መወሰኑ ነው፤ ይህ ስልት አዲስ አይደለም፤ በብዙ የአረብ አገሮች የሚጠቀሙበት ነው።

Wednesday, November 28, 2012

ሁለተኛው የኢህአዴግ መንግስት

(ከአስራት አብርሃም)
 

እናንተ፣ ያበሻ ሰዎች ተስፋን አትቁረጡ

ከስንት አመት ወዲያ

መልሰው ሊገዙ ንጉስ ጦና መጡ

 
ይህ ግጥም አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው የተሾሙ ጊዜ በፌስቡክ ላይ የተለቀቀ ነው። የገጣሚውን ማንነት ማወቅ ባልችልም ሀሳቡን የገለፀበት መንገድ ግን ሳላደንቅ ማለፍ አልችልም። ግሩም ድንቅ ነው!
በታሪክ እንደሚታወቀው የወላይታ የመጨረሻው ንጉስ ካዎ ጦና ነበሩ። ግዛታቸውን ላለማስነጠቅ አያሌ የመከላከል ጦርነቶች አካሄዷል፤ በኋላ ላይ በአፄ ምኒልክ ጦር ተሸንፈው፣ ግዛታቸውም ለሸዋው ሰፋሪ ጦር አስረክበው ለግዞት ተዳርጓል። ከዚያ በኋላ የወላይታ የሚባል ንጉስ አልነበረም። ለዚህ ነው ገጣሚው "ተስፋ አትቁረጡ" የሚል ስንኝ ያስቋጠረው። ከወላይታ፣ ኢትዮጵያን የሚገዛ መጣ ለማለት ተፈልጎ የተገጠመ ይመስላል። እውነትም ሰውዬ ኢህአዴግ ሆኑ እንጂ ከወላይታ መምጣታቸውስ ደስ የሚል እና ተስፋ የሚሰጥ ነው። ምክንያቱም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ "አቅም እስካለኝ ድረስ የአገሪቱን ከፍተኛ ስልጣን ለመያዝ የሚያግደኝ ነገር አይኖርም" ብሎ እንዲያስብ የሚያደርግ ነውና። ክፋቱ ግን አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ወደዚህ ስልጣን የመጡት በአቅም ብቃት ሳይሆን ለቀድሞው ጠቅላይ ሚንስቴር በነበራቸው ታማኝነት መሆኑ ላይ ነው። ይህን እውነት የሰውየው ነፍስ አባት በየዋህነት ለሪፖርተር ጋዜጣ ሰጥቷል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማስተዳደር ባቃታቸው ጊዜ ለአቶ መለስ ስልክ ደውለው "ኧረ እኔ አልቻልኩም ምን ማድረግ ይሻለኛል?" ብለው ያመለክታሉ።

Tuesday, November 27, 2012

በራስ አሉላ ስም የተሰየመው ት/ቤት በመለስ ተቀየረ

 

ከኢየሩሳሌም አርአያ

በትግራይ ተምቤን – አብዪአዲ የሚገኘውና በጀግናው ራስ አሉላ አባነጋ ስም ተሰይሞ የቆየው የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ስያሜው ተቀይሮ በመለስ ዜናዊ ስም እንዲሰየም መወሰኑን ታማኝ ምንጮች አስታወቁ።

በደርግ ዘመን የተሰራውና በራስ አሉላ ስም ተሰይሞ የ 9 – 10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ሲያስተምር ከቆየ በሑላ ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ የት/ቤቱን አቅም ለማሳደግ በሚል የ11-12ኛ መመሪያ ክፍሎችን ለመገንባት በአገር ውስጥና በውጭ አገራት የሚገኙ የአካባቢው ተወላጆች ገንዘብ አዋጥተው ስራው መከናወኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል። ግንባታው ተጠናቆ ባለፈው ነሃሴ ወር ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ እንዳለ አቶ መለስ በማለፋቸው ፕሮግራሙ መሰረዙን ሲታወቅ; ከሁለት ሳምንት በፊት በተከናወነው የምረቃ ስነ-ስርአት የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት በስፍራው እንደተገኙ ማወቅ ተችሎዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት አርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ልዩ ስሙ ጃንሱማ በተባለው ቦታ ወታደራዊ ጥቃት ፈጸመ

 

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በወያኔ ቅጥረኛና ምንደኛ የልዩ ሃይል ታጣቂ ቡድን ላይ የጀመረውን የማጥቃት ዘመቻ አጠናክሮ በመቀጠል ሕዳር 15-2005 ዓ.ምEthiopian People Patriots Front - EPPF አርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ልዩ ስሙ ጃንሱማ በተባለ ቦታ ባደረገው ውጊያ 14 የጠላት ወታደሮችን በመግደልና 12 በማቁሰል ከፍተኛ ወታደራዊ ድሎችን በማስመዝገብ ግንባሩ የተሰማራበትን ግዳጅ በድል እየተወጣ መሆኑን የግንባሩ ወታደራዊ መምሪያ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዘራፊውና ከነፍሰ-ገዳዩ የወያኔ አምባገነናዊ ገዥ ቡድን ለማላቀቅ ያለው ብቸኛ አማራጭ መንገድ በትጥቅ ትግል ስርዓቱን ማንበርከክ መሆኑን ጠንቅቆ ያወቀው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ሀገርንና ወገንን ለመታደግ ቆርጦ በመነሳት በሰሜኑ የሐገራችን ክፍል ወታደራዊ ስትራቴጅውን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ ሰሞኑን አርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ልዩ ስሙ ጃንሱማ በተባለው ቦታ ባደረገው የማጥቃት ዘመቻ 26 የጠላት ወታደሮችን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ወታደራዊ የበላይነትን የተቀዳጀ ሲሆን፣ ከሞቱት 14 የልዩ ሃይል ታጣቂ ቡድን መካከል አበበ የሚባለው የቀራቅር ተወላጅና አለልኝ የሚባል የደባርቅ ተወላጅ የሆኑት ከፍተኛ አመራሮች መሞታቸውን የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ወታደራዊ መምሪያ ገልጿል።

Monday, November 26, 2012

መቀሌ ዩኒቨርሲቲ እየታመሰ ይገኛል





መቀሌ ዩኒቨርሲቲ በተወሳሰበ ሙስና ውስጥ በመሆኑና የሙስናው ዋና ተዋናዮች ዶ/ር ክንደያ ገብረህይወት እና ዶ/ር ኣብዱልቃድር ከድር የተባሉ ምክትል ፕረዚደንቶች ይውረዱልኝ ብለው ከሶስት ወር በላይ የጠበቁት ጀርመናዊ ፕረዚደንት ችግር ላይ ናቸው።
የቦርድ ሰብሳቢው ኤርትራዊው ኣቶ ቴድሮስ ሓጎስ (የኢፈርት ቦርድ ሰብሳቢም ናቸው) ጀርመናዊውን በአካል እንዳስፈራሩዋቸው ታውቋል!
ይህ የሆነው ደግሞ ለትምህርት ሚንስትር ሳይቀር ግልባጭ ባደረጉት የአዲስ ምክትል ፕረዚደንቶች ሹመት የተነሳ ነው።
ጀርመናዊው ፕረዚደንት ከሶስት ወር በላይ/August-November/ የጠየቁትን ጥያቄ ሳይመልሱ ተኝተው የከረሙት ኣቶ ቴድሮስ ሓጎስ አውቆ የተኛ ቢቀሰቅሱት ይማታል የሚል አዲስ ዓይነት ቢሂል ፈጥረዋል! ከ300 million ብር በላይ ያባከኑን ሰዎች ገለል እንዲሉ መጠየቃቸው ሊመሰግኑ ሲገባ እንግዳውን German ሰውዬ እንደዚህ እንደውሻ የሚያስፈራሩዋቸው እነ ቴድሮስ ሓጎስ ወደ ማፍያነት መቀየራቸው ጉልህ ማሳያ ነው። ይህን ህዝብ ከመጤፍ እንደማይቆጥሩትና እንዳሻቸው መኖር እንደሚችሉ ግልፅ ማሳያ ነው። ይህ ህዝብ በሚከፍለው ግብርና በደሙ እየነገዱ የሚኖሩት እስከ መቼ ነው? ትግራይ ተማርሯል በማስፈራራት ና በጉልበት ልክ እንደ ትግራይ ህዝብ ደመኛው ለገሰ አስፋው ትግራይን ኤርትራዊው ቴድሮስ ሓጎስ እየገዙዋት ነው። የሚሰርቅን ሰው መጠየቅ ሲገባቸው ኣብሮዋቸው እንደሚሰርቅ በግልፅ በሚያሳይ መልኩ መከላከላቸው ይህ ስርዓት ምን ያህል እንደዘቀጠ፣ ወድቀቱም እንደቀረበ ያሳያል።