ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ መሞታቸው ሁሉም ሰው ያሳዘነ ጉዳይ ነው፡፡ ለምን ከተባለ ሁሉም ሰው ከመሞት የሚያመልጥ ባይኖርም
የአሟሟታቸው ሁኔታ ግን ለየት ባለ ሁኔታ ስለተፈፀመ በጣም ያሳዝናል፡፡ መጀመሪያ በሪፖርተር ጋዜጣ አንድ የመንግሥት ቃለ-አቀባይ መነሻ በሌለው ሁኔታ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ የጤና ችግር የለባቸውም የሚል መግለጫ ሰጠ፡፡ ሰዉየው ይህ ያሉበት ምክንያት ምንድነው? ስለጤናቸው ምን ተብሎ እና ነው ይህን መግለጫ የሰጡ ማለት ጀመረ፡፡ በስተጀርባ አንድ ነገር እንዳለ ጥርጣሬ ውስጥ ገባ፡፡ ቆየት ብለው ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ታመው ህክምና እንደገቡና ህመሙም የሚያሰጋ እንዳልሆነ መግለጫ ተሰጠ፡፡ ቆየት ብለውም በተለይ አቶ በረከት ስምዖን በዕረፍት ላይ መሆናቸው በቅርብ ግዜ ሥራቸው እንደሚጀምሩ መግለጫ ሰጡ፡፡
ይህ ሁላ ሲሆን ግን አንድ ደ/ር እንኳ ስለየጤንነታቸው ጉዳይ መግለጫ የሰጠ አልነበረም፡፡ ይህ ህዝቡ በበለጠ ጥርጣሬ ውስጥ
ከተተው፡፡ የታመመ ሰው ስለህመሙ የሚያቅና ሁኔታውን ማብራራት የሚችል ሃኪም ነው ስለ ጠቅላይ ሚኒስቴር የጤንነት ጉዳይ
የሚነገረን ያለ በመንግሥት ሥልጣን ባሉ ሰዎች ነው ይህንን ነገር እንዴት ነው በማለት ራሱ በራሱ መወያየት ጀመረ፡፡ የሃኪም
መግለጫ ሳይሰማ ዜና ዕረፍታቸው ተሰማ፡፡ መሞታቸው በጣም አሳዝኖናል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ባህሪያት ለተነሱለት ዓላማ በፅናት የሚተገብሩ ሰው ነበሩ፡፡ የሆነ ሐሳብ አቅርበው ተቀባይነት ካላገኘ ሞተው ይገኛሉ፡፡ በሐሳባቸውና
በአመለካከታቸው የሚነሱ ልዩነቶች ፍፁም አያስተናግዱም፡፡ ለማስተናገድ ቢሞኩሩም የትም አይደርስም ብለው የገመቱት እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ በዓቅም የሚቀናቀናቸው ሰው አይወዱም፡፡ ብዙ አብነቶች ማቅረብ ይቻላል፡፡ አቶ አርከበ ዕቁባይ አቶ መለስ እንደሚጠሩዋቸው “ጅብ” ናቸው፡፡ ጅብነታቸው በሥራ ነው፡፡ የትግራይ ም/ፕሬሲዳንት በነበሩበት ጊዜ አንዳንድ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ሲሞኩሩ አዲስ አበባ ወስደው የአዲስ አበባ ከንቲባ ሁነው እንዲሾሙ አደረጉ፡፡ በዚ ጊዜ በተለይ በነጋዴው የአገልግሎት አሰጣጥ ለውጥ ሲያስመዘግቡ ቀለም ከመቀባት የማያልፍ ሥራ ነው የሠራኸው ብለው መዓት ወረዱባቸው፡፡ ከዛ በኋላ የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስቴር ድኤታ ሁነው እንዲሠሩ ተደረገ፡፡ ከዛ በማንሳት ደግሞ አማካሪ ብለው ሰው በማያያቸው (አቅማቸው ህዝቡ በማያየው ዋሻ) እንዲገቡ አደረጉ፡፡ይህ ሁሉ መነሻው ስጋት ነው፡፡ አቶ አርከባ በግልፅ መቃወም አልደፈሩም እንጂ ውስጣቸው ከኛ በላይ የአቶ መለስ በላያቸው ላይ ያደረጉት ዘመቻ ያውቁታል፡፡ በዚህ ቅሬታ ነበር በህወሐት ማእከላዊ ኮሚቴ ለፖሊት ቢሮ ምርጫ አልፈልግም ብለው ራሳቸው ያገለሉት፡፡
አቶ መለስ በተለይ “ከተሃድሶ” በኋላ እሳቸው እንደአስተማሪ የቀረው ማእከላዊ ኮሚቴ የህወሐት/ኢህአዴግ እንደተማሪ ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ የሚማርበት ሁኔታ ነው የነበረ፡፡ የዚህ ጉዳት በጣም ብዙ ነው፡፡ አቶ መለስ ብቁ ሰው ማፍራት አልቻሉም፡፡ በተለይ በትግራይ፡፡ ወጣቱ ትውልድ ሥልጣን ላይ እንዲወጣ አይፈለግም ለምን አይታመንማ፡፡ ነባሩ ታጋይ ደግሞ እሳቸውን በዓቅም የሚወዳደር አጥላልተው ሞራሉ እንዲነካ ያደርጉታል፡፡ እነ አባይ ፀሃዬ፣ሥዩም መስፍንና አርከበ ዕቁባይ የዚህ አብነቶች ናቸው፡፡
አቶ መለስ ስልጣን ሙሉ በሙሉ ሳይቆጣጠሩ ጊዜ ያሳዩት የነበረ በህሪ ብዙም አይስተዋልም ነበር፡፡ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች
ለነበሩ ሰዎች የሚያሳዩትን ስህተቶች ማረም፣ ለህዝብ ተብሎ ሐቅም ቢሆን ህዝቡ ካልተቀበለው ድርጅቱ ተቀብሎ ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅብናል ሲሉ ይስተዋሉ ነበር፡፡ ስልጣን ሙሉ በሙሉ በተቆጣጠሩበት ጊዜ ጀምሮ ግን አንድ ቀንም ህዝቡን ያነሳው ጥያቄ ወይም አንፈልገውም ያለውን ነገር ተቀብለው አያውቁም፡፡ ለምሳሌ፡ የሊዝ አዋጅ መጥቀስ ይቻላል፡፡ ህዝብ ሲቃወም የተቃዋሚ ድርጅቶች ሐሳብ ነው ተብሎ ይፈረጃል፡፡ ያነሳ ሰውም እንዲሁ፡፡ ለስልጣን ብለው ዲሞክራሲ ያፍናሉ፡፡ እስከአሁን የተካሄዱ ምርጫዎች ህያው አብነቶች ናቸው፡፡ የተካሄዱ ምርጫዎች ሁሉም በማጭበርበር እንጂ ህዝቡ በነጻነት ያካሄደው ምርጫ አይደለም፡፡ ህዝቡ የፈለገው ፖለቲካዊ ፓርቲ መርጧል ማለት ፍፁም አይቻልም፡፡እርግጥ ነው በ1997 ዓ.ም ዲሞክራሲ ባልገመቱት ሁኔታ ህዝቡ ተነሳስቶ እነሱን ገፍትሮ የመሰለውን የፖለቲካ ፓርቲ መምረጥ በቅቶ ነበር፡፡ በተለይ የአዲስ አበባ ህዝብ በድፍን ቅንጅትን መርጦ ነበር፡፡ ቅንጅት መከራን ተቀብሎ ህዝብን ለማገልገል ስላልተነሳ የህዝብን ድምጽ መንገድ ላይ ጥሎት ሄደ፡፡ የዚሁ ጠባሳ አሁን የምናየው ያለን ዓይነት ምርጫ እንድናስተናግድ ተገደናል፡፡ ይህም ሆኖ ቅንጅት ሥልጣን ይይዛል ከሚል ፍራቻ ምርጫው ከተካሄደ በነገታው አዲስ አበባ ለኦሮምያ ክልል ተሰጥታለች ብሎ በፓርላማ እንዲታወጅ አገረጉ አቶ መለስ፡፡ ይህ የልጆች ጨዋታ ግን ደግሞ ይቅር የማይባል የታሪክ ስህተት ለምን ተደረገ ብለን ካልን የቅንጅትን ዓቅም ለማዳከም ተብሎ ነበር፡፡ ለዚህ ነው አቶ መለስ ለሥልጣን ብለው የማያደርጉት ነገር የለም ያልነው፡፡ በፍትሕ በኩል ስንሄድ፤ ዳኛችና ዓቃቢያነ-ህግ በሙያቸው ባላቸው ብቃት ሳይሆን በፖለቲካ ተአማኒነታቸው ብቻ ነው ዳኛችና ዓቃቢያነ ህግ ሊሾሙ የቻሉት፡፡ ይህ በህዝብ ላይ ከፍተኛ የፍትሕ ዕጦት ፈጥሮ ህዝቡ ዕሪ እያለ ይገኛል፡፡ ሁሉም ነገር አሁን በጉቦ ነው የሚፈፀመው፡፡ ከቀበሌ እስከ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፍትሕ አካላት፡፡ መሬት በካድሬዎች ስለሚስተዳደር እንደፈለጉት እያደረጉት ይገኛል፡፡ በሌሎች የመንግሥት ሥራዎችም ኃላፊነት የሚሰጣቸው በፖለቲካ አባልነታቸው ነው ብቃት፣ትምህርት፣ስራ ልምድ አይሰራም፡፡
ይህ ማንን እየጎዳ ይገኛል ? ህዝብ ነዋ፡፡ ታድያ ህዝብ የሚጎዳ ከሆነ ለምን ተመረጠ ? ለስልጣን ተብሎ፡፡ ስልጣንን ከህዝብ ማስቀደም ማለት ነው? በትክክል፡፡ ሙስናን በሚመለከት፡- ጠ/ሚኒስቴር መለስ ሙስና መዋጋት አይፈልጉም፡፡ ለምን ? በሥልጣን ላይ ያሉ ሰዎች በፈፀሙት ህግ ፊት በማቅረብ ፍርድ እንዲገኙ አይፈልጉም፡፡ ምክንያት፡- 1ኛ. የቀኝ እጃቸው የሆኑ በሙስና የተዘፈቁ በመሆናቸው አሳልፈው መስጠት አይደፍሩም፡፡
2ኛ. ለቅርብ ወዳጆቻቸው ካላጋለጡ ሌለሎች ማጋለጥ ድፍረት አያገኙም፡፡ በዚህ ምክንያት ከድሃው ህዝብ ብዙ ሚሊዮን የአገሪቱ
ሃብት ጥቂት ባለሥልጣናት እያግበሰበሰት ይገኛል፡፡ አድልዎ ወገናዊነት በሰፊው ይስተዋላል፡፡ ከዩኒቨርስቲ ተመርቆ የሚወጣው ወጣት በመንግሥትም ይሁን በፖለቲካ ድርጅቶቻቸው ስም የተቋቋሙ የኢኮኖሚ ካምፓኒዎቻቸው ለመቅጠር አንችልም ራስህ ተደራጅተው ሥራ ፍጠር ይሉታል፡፡ ወጣቱም ሌላ አማራጭ ስለሌለው በድንጋይ ጠረባ፣በኮብል ስቶን ሥራ፣በብሎኬት፣በልስን እና በሌሎች የሥራ ዘርፎች ሳይወድ በግድ ያልፍልኝ ይሆናል በሚል ተስፋ ሲንቀሳቀስ ይገኛል፡፡ የባለሥልጣኖች ልጆች ግን በነዚህ የወጣቶች የኢኮኖሚ ድርጅቶች ብለው በሚጠሩዋቸው ድርጅቶች አንድም የለም፡፡ የሚበዙ ውጭ አገር ተምረው በዛው የቀሩ ናቸው ሌሎች ደግሞ ትእምት በሚባል የህወሐት ካምኒ ተቀጥረውና ሃላፊ በመሆን ወፈር ያለ ደመወዝ እየተከፈላቸው የተንደላቀቀ ኑሮ ይኖራሉ፡፡