Tuesday, December 4, 2012

በሳቅ ፍርስ አሉ

 

laughing lion
 

በሳቅ ፍርስ አሉ

አገራቸውን በመክዳት

ወገናቸውን ለመጉዳት

ያልነበረ ሕግ ጥሰው

በነስብሐት ነጋ – በነ መለስ ተከሰው

ሽብርተኛ ሲባሉ

‘በሳቅ ፍርስ አሉ’ አሉ፡፡

ሽ-ሽ-ት በሚል ርዕስ ላቀረብነው የአብዲ ሰኢድ ግጥም ግሩም የሆነ ምላሽ በመስጠት ጨዋታው ሞቅ ደመቅ ላደረጋችሁት dawit፣ ሽማግሌው፣ በለው፣ yeKanadaw kebede እና ዱባለ እጅግ ከፍ ያለ ምስጋናችን ይድረሳችሁ፡፡

በዚህ የግጥም ጨዋታችን የዘወትር ተሳታፊ የሆኑት የካናዳው ከበደ (yeKanadaw kebede) “ለሚቀጥለው የግጥም ጨዋታ አድርጓት” ብለው “በሳቅ ፍርስ አሉ” በሚል ርዕስ “አሸባሪ” በመባል ተከስሰው በእስር የሚማቅቁት ወገኖቻችንን በተመለከተ የላኩልንን ግጥም ነው ላሁኑ ጨዋታችን ያቀረብነው፡፡ እስካሁን ግጥም ስናቀርብ የነበረው ከሌሎች ቦታዎች ነበር አሁን ግን የካናዳው ከበደ የራሳቸውን ግጥም በመላክ ጨዋታው ከኛው ለኛው እንዲሁን ስላደረጉ በጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ስም ከልብ እናመሰግናለን፡፡ ሌሎቻችሁም እንዲሁ ለጨዋታ የሚሆን እጥር ምጥን ግጥም ከላካችሁልን በደስታ የምናስተናግድ መሆናችንን እንገልጻለን፡፡

 

 

Monday, December 3, 2012

ህወሓት ደብረጽዮንን ቀጣይ ጠ/ሚ/ር ያደርጋል!

 

የአሁኑ ምደባ ለመለስ ቀርቦ ነበር
debretsion gebremichael
 
ከአቶ መለስ መለየት በኋላ ወደ አደባባይ የወጡት ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊሆኑ እንደሚችሉ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ግምታቸውን ሰጡ። አገር ቤት ተቀምጠው በኢህአዴግ ላይ የሰላ ትችት በማሰማት ቀዳሚውን ስፍራ የያዙት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፍልስፍና መምህርና እንደ ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም የአደባባይ ምሁር በመባል የሚታወቁት ዶ/ር ዳኛቸው ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ይፋ እንዳደረጉት ለግምታቸው ምክንያት ሰጥተዋል።
አቶ መለስ በህይወት እያሉ የስልጣን ክፍፍሉን በሶስት ለመመደብ መታሰቡን ሰምተው እንደነበር ያስታወሱት ዶ/ር ዳኛቸው፣ ሃሳቡ ከስምምነት ላይ ሊደረስ ባለመቻሉ ተግባራዊ ሊሆን እንዳልቻለ አመልክተዋል። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ማንም ይሁን ማን ከዚህ ቀደም እንደነበረው ስልጣኑ በአንድ ሰው ላይ ተጭኖ ሊቀጥል እንደማይችል ከስምምነት ላይ በመደረሱ አሁን የተደረገው ምደባ ተግባራዊ ሊሆን እንደቻለ በማመልከት ስለቀጣዩ ጠ/ሚኒስትር ግምታቸውን አኑረዋል።
“በእኔ ግምት” አሉ ዶ/ር ዳኛቸው የወደፊቱን ሲተነብዩ “… ህወሃት የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ ለመያዝ በሁለት መንገድ እየሄደ ነው፡፡” ሕወሓት አሁንም ቢሆን ስትራቴጂካዊ ቦታ ላይ መቀመጡን ያመለከቱት ዶ/ር ዳኛቸው ህወሃት ቁልፍ ቦታዎችን መያዙን ለቀጣዩ ዋና ስልጣን መንደርደሪያ አድርጎ እንደሚጠቀምበት ጠቁመዋል።

Sunday, December 2, 2012

የጁነዲን መጨረሻ አልታወቀም

 

junedin sado1
 
ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም የኢትዮጵያን ታላቅ የሥልጣን መቀመጫ ሲረከቡ “ለተደረገልን ምደባ አመሰግናለሁ” ማለታቸውን ተከትሎ የከፍተኛ ባለሥልጣናት ሹመት “ምደባ” የሚል ስያሜ አግኝቷል። ትላንት ለተወካዮች ምክር ቤት በቀረበ የሽግሽግ ምደባ አቶ ጁነዲን ሳዶ ከምደባ ተዘለው ከሃላፊነታቸው መነሳታቸው ይፋ ሆኗል።
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ጁነዲን ሳዶ ወንበራቸውን ለአቶ ሙክታር ከድር እንዲያስረክቡ ተደርጓል። ኦህዴዱ አቶ ሙክታር የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ማዕረግ ታክሎላቸው አቶ ጁነዲን ሲመሩት የነበረውን የሲቪል ሰርቪስ ተቋም እንዲመሩ ሲደረግ አቶ ሃይለማርያም ስለአዲሱ ተሿሚ አቶ ሙክታር ቁርጠኛነትና ብቃት ሲያብራሩ ስለ አቶ ጁነዲን ከሃላፊነት መነሳት ግን ያሉት ነገር የለም።
አድሃና ሃይለ
ለዚህም ይመስላል የመድረክ አባል ብቸኛው ተቃዋሚ አቶ ግርማ ሰይፉ “ህዝብ የማወቅ መብት አለው” በማለት ስም ሳይጠሩ አቶ ጁነዲን የተነሱበት ምክንያት እንዲገለጽ “የተከበረውን” ፓርላማ የጠየቁት። ሚኒስትሮች ሲሾሙ መልካም ነገራቸው የሚገለጸውን ያህል ከስልጣን ሲነሱም ምክንያቱና በደላቸው ለህዝብ ሊነገር እንደሚገባው ሲጠይቁ መረጃው በፓርላማ ውስጥ ላሉት ሁሉ ጠቃሚ እንደሚሆን በማመላከት ነበር።

Saturday, December 1, 2012

ህወሃት አረጋግቶ አገገመ

 

ብቸኛው ተቃዋሚ የንግድ ሚኒስትሩን ሹመት ኮነኑ

Assigned EPRDFist

 

ኢህአዴግ “አረጋግቶ አገገመ” ከተባለው አዲሱ “ምደባ” መካከል የንግድ ሚኒስትር ተብለው በተሰየሙት ላይ ብቸኛው የፓርላማ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉ ጠንካራ መከራከሪያ በማቅረብ ተቃወሙ። አቶ ግርማ የሚሾሙ ብቻ ሳይሆን የሚነሱ ባለስልጣናት ከሃላፊነታቸው የተነሱበት ምክንያትም ለህዝብ መቅረብ እንዳለበት አሳሰቡ። አቶ ሃይለማርያም ተቃውሞውን “መክረንና ገምግመን ያደረግነው ነው” ሲሉ ተከላከሉ። አቶ ግርማ ብሩ (አሁን አምባሳደር) ሲመሩት የነበረውን ሚኒስቴር መ/ቤት “ስያሜና ምልክት መለየት የማይችል” በማለት አንቋሸሹት።

ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ አገሪቱን በመሩበት ሶስት ወራት ካቢኒያቸውን በደንብ መገምገማቸውን በግምት በመግለጽ ተቃውሞ ያቀረቡት አቶ ግርማ ሰይፉ በምደባው በተወሰነ ደረጃ እንደሚስማሙ ተናግረዋል። የንግድ ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ጫኔን ምደባ የተቃወሙት በማስረጃ ነው። የዓለም ባንክ ለንግድ ምዝገባ የማያመቹ አገሮችን ዝርዝር ጥናት ይፋ ሲያደርግ ኢትዮጵያ ከ185 አገሮች የ165ኛ ደረጃ ማግኘቷን፣ ለዚህም የዳረጉት ቀደም ሲል በተጠባባቂ ሚኒስትርነት ለረዥም ጊዜ ያገለገሉት አቶ ከበደ ጫኔ በመሆናቸው አዲሱ ሹመት እንደማይገባቸው አቶ ግርማ በተቃውሞ ተናግረዋል። በተጨማሪም ህዝብ የማወቅ መብት ስላለው ከፍተኛ ባለሥልጣናት ከሃላፊነታቸው ሲነሱ ምክንያቱ ይፋ ሊሆን እንደሚገባው ማሳሰቢያ አቅርበዋል።

አዲሱ የስልጣን ክፍፍልና አመክንዮው

 

(በዳዊት ተሾመ)

muktar debretsion tedros

እንደ መግቢያ

ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረውን የካቢኒያቸውን ሽግሽግና አዲስ ተሿሚ ሚኒስትሮቻቸውን ትላንት (ህዳር 20፣ 2005 ዓ.ም) በፓርላማ በመገኘት አሹመዋል:: አዲሱ ካቢኔም ሶስት ም/ጠ/ሚኒስትሮች ሲኖሩት የአራት ሚኒስቴሮችን ሽግሽግም ያካተት ነው:: የቀድሞ ሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር ሚኒሰቴር አቶ ጂነዲ ሳዶ ከሃላፊነት በማንሳት በአቶ ሙክታር ከድር ተተክተዋል:: የጤና ጠብቃ እና የንግድ ሚኒስትር ሚኒሰቴር ዲኤታ የነበሩት ዶ/ር ከሰተብርሃን አድማሱና አቶ ከበደ ጫኔ እንደየቅደምተከትል ለሚመሯቸው ተቋሞች ሚኒስቴር ሆነዋል:: የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር ማዕረግ የተሾሙት የሚከተሉት ናቸው:: ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል የኢንፎርሜሽንና ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የፋይናንስና የኢኮኖሚ ዘርፍ አስተባባሪ፣ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትሩ አቶ ሙክታር የመልካም አስተዳደር ማሻሻያ ዘርፍ አስተባባሪ እንዲሆኑ ሲደረግ በመስከረም ወር ከጠ/ሚ ሃይለማርያም ጋር የተሾሙት የትምህርት ሚኒስትር ሚኒሰቴሩ አቶ ደመቀ መኮንን የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እንዲሆኑ ተሹመዋል:: በዚህም የተነሳ በምስራቅ አፍሪካ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ ሶስት ም/ጠ/ሚኒስትሮች ይኖሯታል ማለት ነው::

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ወታደራዊ ጥቃት ፈፀመ

 

Ethiopian People Patriotic Frontበሰሜን ጎንደር መተማ ልዩ ስሙ ዘባጭ ባህር በተሰኘ ስፍራ ህዳር 20-2005 ከወያኔው የመከላከያ ሰራዊት ቅጥረኛ ጋር የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር አገር አድን ሰራዊት ባካሄደው ውጊያ 13 /አስራ ሶስት/ የእብሪተኛው ቡድን ታጣቂዎች በመግደልና 17 /አስራ ሰባት/ በማቁሰል እንዲሁም ተተኳሽ መሳሪያዎችን በመማረክ ከፍተኛ ድል ተቀዳጅቷል።

በእለቱ በተካሄደው ውጊያ የወያኔው ታጣቂ ኃይል ተጨማሪ ሰራዊት በአካባቢው ያዘመተ ሲሆን፡ አርበኛው ሰሞኑን በተከታታይ እየወሰደ የሚገኘው ድንገተኛ ወታደራዊ ማጥቃት እርምጃ የህዝቡን ትኩረት ከመሳቡም ባሻገር በኢትዮጵያውያን ዘንድ የፀረ-ወያኔ ትግል መነሳሳት አብይ ሚና እየተጫወተ መሆኑን በርካቶች እየገለጹ መሆኑም እየተገለጸ ነው።

የፖለቲካ ትግል የመጨረሻ አማራጭ የሆነው የትጥቅ ትግልን መፍትሄ አድርጎ ለአመታት ያህል የጊዜ፣ የእውቀት፣ የጉልበት ብሎም የህይወት መስዋዕትነት እየከፈለ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ኢትዮጵያን ከጎጠኛውና መሰሪው ኃይል የመከላከል አኩሪ ጥረቱን ዛሬም እንደ ትላንቱ ሳያሰልስ የሚገፋበት መሆኑን አስታውቋል።

ሰራዊቱ የተለመደውን ጀብድ በፈፀመበት አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች የግንባሩን ሰራዊት እየተቀላቀሉ መሆኑን የገለጸው የድርጅቱ ወታደራዊ መምሪያ ግንባሩ በተከታታይ የወሰደውንና እየወሰደ የሚገኘውን ወታደራዊ ማጥቃት የመላውን ኢትዮጵያ ህዝብ ድጋፍ የሚጠይቅ እንደመሆኑ መጠን ለሁለንተናዊ የአርበኝነት ትግሉ የተቻለውን በማበርከት ከስርዓት ለውጡ ተጠቃሚ የሚሆንበት አገር ለመገንባት መነሳት ይገባዋል የሚለውን መልዕክት ያስተላለፋል።

 

 

የዛሬ ኅዳር 21 የችሎት ውሎ

* አቃቤ ሕግ ባለፈው ሳምንት በመደናበር የዛሬውን ችሎት ደግሞ በሽወዳ ፈጽሞታል
* ሕግ የማይገዛቸው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ዛሚ ኤፍ.ኤም ‹‹ሕግ ይግዛችሁ›› ተብለዋል
* ልደታ አካባቢ ፌዴራል ፖሊሶች ‹‹እስላም ማየት አስጠላን›› ሲሉ ውለዋል


የዛሬ ኅዳር 21 የችሎት ውሎ

ባለፈው ሳምንት ገልጸነው እንደነበረው ዛሬም መሪዎቻችንን ከሕዝብ እይታ ለመሰወር ፖሊስ በደረቅ ሌሊት ነበር ከቃሊቲ ወደ ልደታ ፍርድ ቤት ያመጣቸው፡፡ ሌቱ እስኪነጋና የችሎት ሰዓት እስኪጀምርም በፍርድ ቤቱ ግቢ ውስጥ በፖሊስ ጥበቃ እንዲቆዩ ተደርጓል፡፡ ችሎቱ ከተሰየመ በኋላም የመሪዎቻችን ጠበቆች የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ዛሚ ኤፍ.ኤም ጣቢያዎች ደንበኞቻችን በተጠረጠሩበት ወንጀል ጥፋተኛ ሳይባሉ ጣቢያዎቹ ግን በተቃራኒው ከፍተኛ የስም ማጥፋት ስራ ላይ ስለተሰማሩ እዚህ ችሎት ውስጥ ካሉ ይውጡልን ብለው ጠይቀዋል፡፡ ዳኛው ችሎቱ ለማንም ክፍት በመሆኑ ይህን ሊያዙ እንደማይችሉና ጣቢያዎቹ የተባለውን ተግባር እየፈጸሙ ከሆነ ግን ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አዘዋል፡፡

ቀጥሎ በቀጥታ የባለፈውን ሳምንት የጠበቆች የመጀመሪያ መቃወሚያ፤ መቃወሚያ ለማቅረብ ቀጠሮ አስይዞ ወደ ነበረው ችሎት የተገባ ሲሆን አራቱ ጠበቆችም በመተጋገዝ መቃወሚያቸውን ለፍርድ ቤቱ አቅርበዋል፡፡ የመሪዎቻችንና ወንድሞቻችን ጠበቆች አንስተውት ለነበረው አንኳር እና ጠንካራ የተብራራ መቃወሚያ ሲያደምጥ አቃቤ ሕግ ባለፈው ሳምንት ችሎት በመደናገጥ እና በመደናበር ስሜት ውስጥ እንዳልታየ ዛሬ ደግሞ ችሎቱ ላይ ‹‹መቃወሚያው የተብራራ አይደለም›› የሚል ምላሽ ሰጥቷል፡፡ መሪዎቻችን የተከሰሱት ከሕግ ውጪ እንደሆነ፣ በዋነኝነት የተከሰሱበትና በ2001 የጸደቀው የጸረ ሽብር ሕጉ ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌዎችን የጣሰ ነው፣ ክሱ የሕግ ትርጓሜ ጉዳዮችን ስለሚያስነሳ መታየት ያለበት ሕጋዊ ስልጣን በተሰጠው ፌዴሬሽን ም/ቤት ነው፣ ይህ ፍ/ቤት ይህንን ክስ የማየት ስልጣን በሕግ አልተሰጠውም እና ደንበኞቻችን በነጻ ይሰናበቱልን የሚሉ መከራከሪያዎችን ከአገሪቱ እና ከአለም አቀፍ ሕግጋት ጋር ተዋድደው የቀረበለት አቃቤ ሕግ፤ ምላሽ ለመስጠት ሳምንት ያህል ተዘጋጅቶም ሊሰጥ የቻለው ምላሽ ‹‹ይሄ ፍርድ ቤት አያየውም ካላችሁ ለምን እዚህ መጣችሁ?›› ብሎ መሪዎቻችንን እና ጠበቆቻቸውን ግራ በገባው ሽወዳ መጠየቅ ነበር፡፡ አቃቤ ሕግ መሪዎቻችንን በግድ ከቤታቸው ወስዶ እንዳሳሰራቸውና ከሶም (ለምን መጣችሁ ባለበት) ፍርድ ቤት እንዳቀረባቸው እንኳ በውል አያውቅም፡፡