Monday, November 26, 2012
Friday, November 23, 2012
በአዲስ አበባ የሚገኘው የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ሊፈርስ ነው
ህዳር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- በአዲስ አበባ የሚገኘው የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልትሊፈርስ ነው:፡ ዛሬ በሸገር ኤፍ ኤምላይ ቀርበው መግለጫ የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሀላፌ እንዳሉት ከባቡር ስራ ጋር በተያያዘ የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ይነሳል::ሆኖም መነሳቱ በጊዜዊነት ነው ሀዲዱ ከተሰራ በሆላ ወደቦታው ይመለሳል ብለዋል:: የኢሳት ምንጮች ከፕሮጀክት መሀንዲሶች አካባቢ የተገኘን መረጃ ጠቅሰው እንደገለጡት የሀዲዱ ዲዛይን ላይ ለሚነሳው የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ላይ ቦታ የለም እናም ሀውልቱ እንደፈረሰ የመቅረቱእድል የሰፋ ነው ሲሉ ገልጠዋል:፡ በተያያዘ መረጃ በዲዛይን ላይ የአጼ ሚኒሊክ ሀውልት ተመሳሳይ እጣ ፈንታ ሊገጥመው እንደሚችል ታውቆል:: መንግስት ጊዚያዊ ነው ቢልም ዲዛይኑ የሚያረጋግጠው ግን ሀውልቶቹ እስከወዲያኛውም ወደቦታቸው እንደማይመለሱ ነው::ከፍተኛ ተቃውሞ የቀረበበትና በሲኖዶስ እንዲፈርስ የተወሰነው የአቡነ ጳውሎስ ሀውልት ቆሞ የታላቁ አርበኛና መስዋእት አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ሊፈርሱ ነው መባሉ በእርግጥ አነጋጋሪ ሆኖል።
ኢህአዴግና ስርአቱ፤ በዘመመ ጎጆ የነገሰ የእብዶች ተስካር
Bizuayehu Tsegaye
ሰላም እንደምን ከረምን አንባቢያን? ክዚህ ቀደም ‘Bureaucracy; the pillar EPRDF rusting’ በሚል አርእስተ አንድ መጣጥፍ ለአንባቢያን አካፍዬ ነበር። ምናልባትም በሃገርኛ ብታካፍለን ያለኝ አንድ አንባቢ ነበርና አማርኛ መተየቢያ ‘ንድፈ ቁስ‘ ስፈልግ ሳፈላልግ ሰነበትኩ። ተሳክቶም ይህዉ በእንዲህ ዳግም መጣሁ።
አርእስቱ ታዲያ በሀገራችን የማህበራዊ አገልግሎት አሰጣጥ ልምድ ሲደመጥ የኖረን ቅራኔ መነሻ ያደረገ ነበር። የብልሹ አሰራር ልምድ በአሁኑ አስተዳደር አጀማመር ፣ ያለፈበትን ደረጃ ፣ በወቅቱ ያለበትን ሁኔታ ፣ በዚህ የተነሳ ወደፊት ለመተግበር የሚገደዉን አሉታዊ እጣፈንታ እንዲሁም የመፍትሄ ሀሳብ በመጠቆም የተገነዘብኩትን ያህል ለማካፈል ሰፍሮአል።
ለመነሻ ያህልም በአሁኑ ወቅት ቁጥር የሌለዉ ብሶት በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ማሰማት እንግዳ አለመሆኑን ፤ እንዲያዉም በአግልግሎት አሰጣጡ እና በ አገልግሎት ሰጪ አካላት መሃከል ስላለዉ መስተጋብር ትዝብት ለመዳሰስ ሞክሯል። መሳካቱ በምላሻችሁ የሚረጋገጥ ይሆናል። አንባብያንም በጉዳዩ የየግል አመለካት ኖርአችሁ ለማካፈል ትፈቅዱ ይሆናል። ለዚህ ግልጥ የሃሳብ ልዉዉጥ የምክንያትነት ‘ማእረጉ’ን ግን ከእኔ ዘንድ እንድታኖሩት ተጠቁሞ ነበር። አሁንም እንዳለ መሆኑን በማስተላለፍ…እንዲህ ቀርቦአል።
በሐገራችን እንዳብዛኛዉ የወቅቱ ኢትዪጲያዊ ወጣት ሁሉ ያኔ ወያነ/ኢህአዴግም በእስተዳደር ልምዱ ልጅእግር ፤ ይበልጥ ሊገልጠዉ በሚችል ቃል እንጭጭ አሊያም ጥሬ ሳለ ይብዛም ይነስ አገልግሎታቸዉን ለተጠቃሚዉ ማህበረሰብ ለማድረስ ፍሬ ያለዉ የመተዳደሪያ ህገ ደንቦች እንዲሁም በሚወጡት ህግጋት የሚገዙ/ለመገዛት ዝግጁ የሆኑ አካላት ነበሩ። በእድሜ ጠና ያሉም ይህ የቀድሞዉ አስተዳደር ዉርስ የፈጠረዉ ተጥኖ ሊሆን እንደሚችል ሊገምቱ ይችላሉ ማለት ስህተት ላይሆን ይችላል።
Friday, November 16, 2012
"ሰንበት ምሳ"
አቤ ቶኪቻው
እኛ ሰፈር ሽሮሜዳ የሰንበት ምሳ የሚባል ነገር አአለ። እሁድ እሁድ ቤተሰቦች ለልጆቻቸው የሚሰጡት ሳንቲም፤ አንዳንዴም ወዳጅ ለወዳጁ በእሁድ ቀን የሚያበረክተው ስጦታ (ብዙ ጊዜ ይህ ስጦታ ወይ ስሙኒ ወይ ደግሞ ሃምሳ ሳንቲም ነው) ብቻ ግን "ሰንበት ምሳ" ነው የሚባለው። ሰሞኑን በሌላ መስኮት ልመጣ አስቤ ተጠፋፍተን ሰነበትን አይደል!? እስቲ ዛሬ በዝች ሰንበት "ሃይ" እንባባል…
ይቺ ፅሁፍ አዲስ ታይምስ (ፍትህ) ትላንት ይዛት ትወጣ ዘንድ ልኪያት ነበር። ከርዕሷ በቀር እንዳለች ናት! (አ…ሃ አንዳንድ ቦታ ትንሽ ነካ ነካ ተደርጋለች) እስቲ ለማንኛውም እንቋደሳት፤ ተጀመረች…
Thursday, November 15, 2012
በደራ ወረዳ የተፈጸመው ኢሰብዓዊ ድርጊት አነጋጋሪነቱ ቀጥሎአል -የወንጀሉ ተባባሪዎች የሆኑ 3 ፖሊሶች እስካሁን አልተያዙም
ህዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በደራ ወረዳ በገብሮ ቀበሌ የፍትህና ጸጥታ ሹም የሆነ ግለሰብ ከሶስት ፖሊሶች ጋር በመ ሆን በቀበሌው የሚኖርን አንድን ግለሰብ መሳሪያ ደብቀሀል በሚል ሰበብ ግለሰቡንና ባለቤታቸውን ልብሳቸውን በማስወለቅ እርቃናቸውን እንዲታሰሩ ማድረጉን፣ እንዲሁም ባልየው ብልቱ በገመድ እንዲታሰር ከተደረገ በሁዋላ ህዝብ በተሰበሰበበት አደባባይ እርቃኑዋን የሆነቸው ባለቤቱ አስጸያፊ ድርጊቶችን እንድትፈጽም፣ በሰደፍ በመመታቱዋም የስድስት ወር ልጇን እንድታስወርድ መደረጉን የገበሮን የቀበሌ ሊቀመንበር፣ የወረዳውን አስተዳዳሪና አንድ የምክር ቤት አባልን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።
ዜናው በኢሳት ይፋ ከሆነ በሁዋላ ኢትዮጵያውያን የተሰማቸውን ስሜት እየገለጹ ነው። አንድ በደቡብ ክልል ተወላጅ የሆኑ ሰው በአካባቢያቸው በደራ ከተፈጸመው የሰብአዊ መብት ጥሰት ያለነሰ ድርጊት በአለታ ወንዶ መፈጸሙን ገልጸዋል
ሌላው ኢትዮጵያዊ ደግሞ ለዚህ ሁሉ ድርጊት ተጠያቂው ስርአቱ ነው ሲል መንግስትን ከሷል
ከፈረንሳይ አገር ትእግስት የምትባል ሴት በሰጠችው አስተያየት ድርጊቱ ድንጋጤን እንደፈጠረባት ተናግራለች
ሌላ በውጭ አገር የሚኖር ኢትዮጵያዊ በበኩሉ የመንግስቱ ሹም የሰራው ስራ እጅግ እንዳሳዘነው ገልጾ ፣ ህዝቡ እንዲህ አይነት ግፍ ሲፈጸም ዝም ብሎ መመልከቱ ጥያቄ እንደፈጠረበት ተናግሯል
በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆኑት ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ ፣ ድርጊቱ ሴትነታችን፣ እናትነታችን ከሁሉም በላይ ኢትዮጵያዊነታችን የተዋረደበት ጊዜ ላይ መድረሱን ያሳያል ብለዋል
ወ/ሮ ሰብለ ወርቅ ታደሰ እንዳሉት መንግስት እንዲህ አይነት ሰዎችን በዙሪያው አሰልፎ ስልጣን ለላይ ለመቆየት ማሰቡንና ፣ በስልጣን ላይ እስከቆየ ድረስ እንዲህ አይነት የሰብአዊ መብት ጥሰት ሲፈጸም ችላ እንደሚል የቀደመ ልምዳቸውን በማንሳት ተናግረዋል
ወ/ሮ ሰብለ በመጨረሻም ህዝቡ እርምጃ መውሰድ ካልቻለ ባርነታችን መቀጠሉ አይቀሬ ነው ብለዋል
ሌላው የሰብአዊ መብቶች ተማጋች የሆኑት አቶ ብዙነጽ ጽጌ በበኩላቸው ድርጊቱ ከባህላችን የወጣ በመሆኑ ሀዘንና ድንጋጤ የተሰማቸው መሆኑን ገልጸው፣ አሁን ባለው ስርአት በህግ መፍትሄ ይመጣል ብለው እንደማያስቡ ገልጸዋል።
አቶ ብዙነህ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አጠቃላይ የስርአት ችግር የሚፈጥረው መሆኑን ተናግረዋል
ምንም እንኳ አሰቃቂ ድርጊቱን የፈጸመው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ቢውልም እስካሁን ድረስ ለፍርድ እንዳልቀረበ ታውቋል። ከግለሰቡ ጋር በመተባባር ወንጀል የፈጸሙ ሶስት የወረዳው ፖሊሶችም በቁጥጥር ስር አልዋሉም።
የወረዳው ባለስልጣናት በትናንትነው እለት መረጃውን ለኢሳት ያቀበለውን ሰው ለመለየት እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ተሰብስበው እንደነበር ለማወቅ ተችሎአል።
Wednesday, November 14, 2012
ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ በጀርመን አገር ዋና ከተማ በርሊን ላይ ተደረገ
በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአይነቱ ልዩ የሆነ በተለያዩ መፈክሮች እና በኢትዮጵያ ባንዲራ ያሸበረቀ ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ በጀርመን ዋና ከተማ በርሊን አደረጉ። ሰላማዊ ሰልፉን ያዘጋጀው በጀርመን የፖለቲካና የሲቪክ ማህበራት አንድነት ድርጅት (EPCOU) ሲሆን በእለቱም ከተለያዩ የጀርመን አካባቢ የሚኖሩ ቁጥራቸው ከ290 በላይ የሚገመት ኢትዮጵያውያን ተሳትፈዋል::መነሻውን በርሊን ከተማ SPD (ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ) ዋና ቢሮ ፊት ለፊት ያደረገው ሰላማዊ ሰልፍ የኢትዮጵያውን አምባገነን ስርአት ቁንጮ የሆነውን ስብሃት ነጋ በጀርመን ተጋብዞ ንግግር እነዲያደርግ መጋበዙ ኢትዮጵያውያንን እጅግ በጣም ያሳዘነ እና ያስቆጣ ድርጊት መሆኑን በመፈክር አሰምቷል። የሰላማዊ ሰልፍኛው ተወካዮች ከሶሻል ዲሚክራቲክ ፓርቲ ተወካይ ጋር አጠር ያለ ንግግር አድርገው የተዘጋጀውን ፅሁፍ ለተወካዩ ሰተዋል። ሰላማዊ ሰልፈኞቹ SPD (ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ) ዋና ቢሮ ፊት ለፊት ሲያሰሙት ከነበረው መፈክር መካከል ስብሃት ነጋ ስለ ሰብአዊ መብትና ዲሞክራሲ የመናገር የሞራል ብቃት የለውም ! Shame on SPD for inviting Ethiopian dictator Sebehat Nega ! እና ሌሎችም ይገኙበታል።
Friday, November 9, 2012
“ኦባማ መጀን” ወይስ “በእውቀት” መደራጀት?
የአሜሪካ ምርጫ ሲጠናቀቅ ተሸናፊው ሚት ሮምኒ ደጋፊዎቻቸው በተሰበሰቡበት አዳራሽ ምስጋና ካቀረቡ በኋላ እንዲህ አሉ፡- “… ሁለታችንም ለምንወዳት አገራችን የምንመኘውን ለማድረግ በተለያየ አቅጣጫ ሞከርን፤ … ሕዝባችን ደግሞ የሚፈልገውን መሪ መረጠ፤ … ስለዚህ ፕሬዚዳንቱን ደውዬ አነጋሬያቸዋለሁ፤ ባገኙትም ድል እንኳን ደስ አለዎ ብያቸዋለሁ፤ … በተለይ ለእርሳቸው፣ ለቀዳማዊ እመቤት እና ለልጆቻቸው ሁሉ መልካሙን እመኛለሁ፤ … አገራችን ከባድ ፈተናዎች ተጋርጠውባታል፤ … ባለቤቴና እኔ ለፕሬዚዳንቱና ቤተሰባቸው ከልብ እንጸልያለን፤ በሥራቸው ስኬት እንዲያገኙና ታላቋን አገራችንን በመምራት የሚያከናውኑት ሁሉ የተሳካ እንዲሁን እመኛለሁ፡፡” ይህንን ካሉ በኋላ ወደተለመደው ህይወታቸው ሄዱ – የፖለቲካ ገዳም ገቡ፡፡ ይህ ንግግር ወደራሳችን እንድንመለከት የሚያደርግ ነው፡፡ የእኛስ ፖለቲከኞች ዕድሜ ልካቸውን የፖለቲካ አክሮባት እየሰሩ አንደ ፓርቲ ሲያቋቁሙ፤ ሌላ ሲያፈርሱ፤ አንዱን ሲጠልፉ ሌላውን በሾኬ ሲሉ … ከመቆየት ይልቅ የሚሞክሩትን ሞክረው አልሆን ሲል በክብር ለተከታዩ ቦታ ለቅቀው ወደ ፖለቲካ ገዳማቸው የሚገቡት መቼ ይሆን?
የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በድጋሚ መመረጥ ብዙ የተጠበቀ ቢሆንም የአሜሪካ ሚዲያ እንደተለመደው በሕዝቡ ውስጥ በፈጠረው የ“አፍጥጣችሁ እዩኝ” ፍላጎት ምክንያት አንድን ምሽት በስሜት ውጥረት እንዲያልፍ አድርጓል፡፡ “ተስፋ” እና “ለውጥ” የተሰኙ ልብን የሚያማልሉ ቃላትን በመላው ሕዝብ ዘንድ በማስረጽ የዛሬ አራት ዓመት እጅግ ከፍተኛ በሆነ የሕዝብ ድጋፍ የተመረጡት ባራክ ሁሴን ኦባማ እንደገና ለተጨማሪ አራት ዓመታት ተመርጠዋል፡፡ አራት ዓመት መለስ ብለን ስንቃኘው የታሰበው “የለውጥ ተስፋ” ተግባራዊ ሆነ ወይስ ተጨማሪ አራት ዓመታትን “አዲስ ንጉሥ እንጂ ለውጥ መቼ መጣ” በእንግሊዝኛ የሚያስዘፍን ነው?
Subscribe to:
Posts (Atom)
