Sunday, May 11, 2014

ከቦታቸው መፈናቀልን የተቃወሙ ኢትዮጵያዊያን እስራትና ግድያ እናወግዛለን!


eprp yl
ሰሞኑን ከአዲስ አበባ አቅራቢያ ያሉ ብዙ ከተሞችን በዋና ከተማው ስር ለመጠቅለል የወያኔ አጋዛዝ “ የተቀናጀ የልማት ማስተር ፕላን” በሚል ያወጣውን አቅድ፣ የማፈናቀል እርምጃ ነው ብለው በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን ለማሰማት ሰልፍ የወጡ ዜጎችን በጅምላ ገድሏል፣ ብዙዎቸን አቁስሏል፣ በገፍ አስሯል። በአምቦ ከተማ ብቻ አስካሁን በተገኑት መረጃዎች በትንሹ 47 የሚሆኑ የተገደሉና ብዙ የቆሰሉ ሲገኙበት፣ በጅማ ካምፓሶች፣ ወለጋ፣ መቱ፣ ቦሉ ሆራ፣ አዳማ ሃረሚያና በሌሎች አካባቢዎች ተመሳሳይ የጭካኔ አርምጃ ወስዷል። ኢሕአፓ-ወክንድ ይህን የወያኔ ኢሰብአዊ ድረጊት አጅግ በመረረ ቃል ያወግዛል። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)

No comments:

Post a Comment