Monday, March 24, 2014

ከመይ ቀኒኩም ዶከተር ቴውድሮስ ጥያቄ አለኝ!


Drከመይ ቀኒኩም ዶከተር ቴውድሮስ ጥያቄ አለኝ!
ሰላም ወዳጄ የዛሬው ሰላምታችን በትግርኛ ነው ፤ ከመይ ቀኒኩም፤ እንዲህ እንዲህ እያልን በሰማኒያውም በሄረስቦች ቋንቋ ቢያንስ ሰላምታ እንለማመድ እንጂ… ቀጥታ ወደ ጉዳያችን ስናሳልጥ፤
የውጪ ጉዳይ ሚኒስትራችን ዶክተር ቴውድሮስ አድሃኖም ይባላሉ። የገባቸው አይነት ነገር ስለሚምስሉ ደስ ይሉኛል። ባለስልጣኖቻችንን ትዊተር እና ፌስ ቡክ መጠቀም ያለማመዷቸው እርሳቸው ናቸው። አቶ መለስም አቶ ሃይለማርያምም ትዊተር የነበራቸው ቢሆንም የአቶ ዶከተር ቴውድሮስን ያሀል ግን ተንቀሳቃሽ አልነበሩም።
ቲውተር ላይ በሚያደርጉት ቀልጣፋ እንቅስቃሴ ጎሽ ጎሽ ስንላችው ወደ ፊስቡክም የተቀላቀሉት ዶክተር ቴውድሮስ ቅልጥፍናቸውን እና ከማህበረሰቡ ጋር ለመቀራርብ የሚያደርጉትን ጥረት አድንቀንላቸው ሳናበቃ ጥያቄ እንጠይቃቸው ዘንድ የሚያስገድድ አንዳች ነገር ተመለከትን።
በፌስ ቡክ ገድግዳዬ ጥጋት ላይ በሰዕሉ ላይ እንደሚታየው አይነት ማስታወቂያ አየሁ። ማስታወቂያው “ዶከተሩን ውደዳቸው” የሚል ነው። ትዝ ሲለኝ፤ ይህንን ውትወታ ሳየው ቆይቻለሁ። ፌስ ቡክ ለዶክተሩ ይህንን ውትወታ የሚያደርግላቸው በብላሽ አይደለም። እኔም እንደ አቅሚቲ የእርሳቸው አይነት ገጽ ስላለኝ ፌስ ብክዬ፤ “ክፈለኝና ላይክህን (ወዳጅህን) ላብዛልህ ብሎኝ ያውቃል።” ዋጋውን ሳየው “ደሃ እንትን አይልሽ” አይነት ነው። ዋጋው መወደዱ ብቻም ሳይሆን ወዳጅ ለማብዛት መክፈል የሆነ ደስ የማይል ነገር አለው፤ እናም ፌስ ቡ ክ ዬ… ወዳጅ በፍቅር እንጂ በገንዝብ አይገዛም ብዬ “ላጥ በል” ብዬዋልሁ።
እናልዎ ዶክተር ቴውድሮስ አድሃኖም ግን የመጣው ይምጣ ብለው ተስማምተው፤ በፌስ ቡክ ገጻቸው “ላይክ” (እውድዎታለሁ) የሚላቸው ሰው እንዲበዛላቸው ፌስ ቡክ እየወተወተላቸው ነው። ለዚህም በቀን በትንሹ ሃያ አምስት ዶላር ይከፍላሉ። እንግዲህ የሂሳብ ማሽናችንን አውጥተን እንምታው፤ እናንተ ዶላር ወደ አሰራ ዘጠኝ ከሰላሳ ምናምን ደርሷልና፤ እሺ ምናምኗን እንተዋት እና በ አስራ ዘጠኝ ከሰላሳ እንምታው፤ አራት መቶ ሰማኒያ ሁለት ብር ከ ሃምሳ ሳንቲም ይመጣል።፡ይሄንን በወር ብንመታው አስራ አራት ሺህ አራት መቶ ሰባ አምስት ብር ይደርሳል።
እና ዶክተርዬ የምጠይቅዎ ምንድነው መሰለዎ…
አንደኛ እንዲህ በገንዘብ የሚገዙት ወዳጅ ሁሉ የምር ወዳጅ ነው በለው እያሰቡ ነውን… ?
ሁለትኛ እንዴት ነው ነገሩ ፈራንካዋ ከየት እየመጣች ነው ለፌስ ቡክ ማስታወቂያ የምትከፈለው… ምንስ የኢኮኖሚያችን እድገት ጣራ ቢነካ እድገቱ ለእርስዎ መዋደጃ ብቻ ነው እንዴ… ?

No comments:

Post a Comment