Saturday, December 13, 2014

አገር ውስጥ እየኖሩ መሞት፣ በስደት ጉዞ መሞት፣ በስደት እየኖሩ መሞት!


“መጪው ጊዜ ከኢህአዴግ ጋር ብሩህ ነው!”
ethiopians and their plight

* አገር ውስጥ “ባርነት”፤ ከአገር ተሰድዶ “ባርነት”

ከጥቂት ቀናት በፊት በአገራቸው መኖር ያቃታቸው 70 ኢትዮጵያዊያን ቀይ ባህርን በጀልባ አቋርጠው ወደ የመን ሲያመሩ በደረሰ አደጋ ሁሉም መሞታቸው ተገልጾዋል። ኢህአዴግ እነዚህ በእርግጥ ኢትዮጵያውያን ለመሆናቸው ማስረጃ እንደሌለውና “እያጣራ” መሆኑን በቃል አቀባዩ በኩል ተናግሯል፡፡
በዚህ ዓይነት ሁኔታ ከአገራቸው እየተሰደዱ ለባህር፣ ለአውሬ፣ … የተዳረጉት ወገኖቻችን ብዛት ተቆጥሮ አያልቅም፡፡ ይህንን ሁሉ አልፈው ወዳሰቡት የደረሱት ደግሞ በስደት የሚኖሩባቸው በተለይ የአረብ አገራት ይህ ነው የማይባል ሰቆቃ ይደርስባቸዋል፡፡ ይህንን ሁሉ የሚሰማው ወገን አሁንም በየኤምባሲው ቪዛ ለማስመታት በተገኘው ቀዳዳ ከአገሩ ለመውጣት ይጥራል፡፡ በዚህ በኩል ያልተሳካለት ድንበር በማቋረጥ አስጨናቂውንና አስፈሪውን ጉዞ ይጀምራል፡፡

Saturday, December 6, 2014

በአዳር ሰልፉ ኢህአዴግ “ተሸብሯል”


በስውርና በግልጽ አፈናው ተጧጡፏል

police 11
* የከምባታ ጠንባሮ ዞን ህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጉ ተገለጸ
* የሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ በፖሊስ ተከብቦ አደረ
የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በፖሊስ ተከብቦ ማደሩንና አባላት ከውጭ እንዳይገቡ መደረጋቸውን ለአዳር ሰልፉ ቅስቀሳ ዝግጅት ቢሮ ያደሩ የፓርቲው አመራሮችና አባላት ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ አመራሮችና አባላቱ እራት በልተው ወደ ፓርቲው ጽ/ቤት ሲመለሱ ቢሮው በፖሊስ ተከብቦ እንዳገኙትና ወደ ውስጥ እንዳይገቡ እንደተከለከሉ በቦታው የነበሩት የፓርቲው አመራሮችና አባላት ገልጸዋል፡፡
police 14አመራሮችና አባላቱ ፖሊስ ከ200 ሜትር ርቀት ውጭ ወደ ፖለቲካ ፓርቲ ጽ/ቤት መጠጋት እንደማይችል ቢከራከሩም ፖሊሶቹ “መመሪያ ተሰጥቶናል፤ አንሄድም!” ማለታቸው ገልጸዋል፡፡ አመራሮቹና አባላቱ ከፖሊስ ጋር ሲከራከሩ የአካባቢው ህዝብ በመውጣቱ ፖሊሶቹ ፓርቲው ጽ/ቤት እንደራቁ ታውቋል፡፡
በሌላ በኩል ከውጭ ወደ ቢሮ ከሚመጡበት ወቅት የፓርቲው ቢሮ አካባቢ ምንነቱ ያልታወቀ ወረቀት ተበትኖ እንዳገኙና እነሱ ሲደርሱ ፖሊሶቹ እንዳነሱት የፓርቲው የምክር ቤት አባል ወጣት እየሩስ ተስፋው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጻለች፡፡
*********************
በነገረ ኢትዮጵያ የፌስቡክ ገጽ ላይ የታተመው መረጃ እንደሚያመለክተው ፖሊስና ደህንነቶች ወደ ሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት የሚገቡና የሚወጡ አባላትንና አመራሮችን እያዋከቡ ይገኛሉ፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችንና አባላትን “እንፈልጋችኋለን!” በሚል እየያዙ ሲሆን በተለይ ደህንነቶቹ መታወቂያ አሳዩ ሲባሉ ፈቃደኛ ሊሆኑ አልቻሉም፡፡

Tuesday, November 4, 2014

ጎተራው ወዴት ነው?¡


(ጌታቸው አበራ)

gettera
ሀገር በብረት ሲታጠር — ‘ግንቦት ሃያህ’ ሲከበር፤
አዲስ ዓመት በመጣ ቁጥር — ዘመን በዘመን ሲቀየር፤
የስራ-ፈቶች ስብስብ መንጋ — ‘ፓርላማህ‘ሲከፈት ሲዘጋ..፤
ሱፍህን ገጥግጠህ — ከረባትህን ጠፍረህ፣
ወዝህን አሳምረህ — ካሜራ ፊት ቀርበህ፣
ጉሮሮህን..ጠርገህ — ፊትህ የከመርከውን ‘ሃያ ገጽ’ ገልብጠህ፣
ቁጥር እየቆጠርክ፣ አሃዝ እየጠራህ…፣
“ምናምን..ሺ.ቶን፣ ሚሊዮን ስልቻ፣
አምርተን አስገባን በዚህ ዓመት ብቻ…”፣
እያልክ ስትደሰኩር — ትንፋሽህ እስኪያጥር፣
ሰምቼህ ሳበቃ፣ የግርምት ጥያቄ እስኪማ ልሰንዝር፤
በልበ-ሙሉነት “ጠግብን በላን” ያልከው፣
ሕዝቡን ቆጥረህ ይሆን? ወይስ የቤትህን ያንተኑ ግሳት ነው?!

Saturday, October 25, 2014

ምጽዓት


የዝርፊያው ፉክክር የት ለመድረስ ነው?

goat-and-sheep
“በግዞትም ቤት አደባባይ ታስሮ ሳለ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፡– ሂድ ለኢትዮጵያዊውም ለአቤሜሌክ እንዲህ በለው፤ — የእሥራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤- እነሆ ለበጎነት ሳይሆን ለክፋት ቃሌን በዚህች ከተማ ላይ አመጣለሁ፤ በዚያም ቀን በፊትህ ይፈጸማል፤ በዚያ ቀን አድንሃለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ በምትፈራቸው ሰዎች እጅ አልሰጥህም፤ ፈጽሜ አድንሃለሁ፤ ነፍስህም እንደምርኮ ትሆንልሃለች እንጂ በሰይፍ አትወድቅም፤ በበእኔ ታምነሃልና ይላል እግዚአብሔር፡፡” ትንቢተ ኤርምያስ 39/15-18
ኑዛዜ ኤርምያስን አነበብሁ፤ጉድ ነው! አንድ የማውቀውን ነገር አረጋግጥሁ፤ ብዙ የማላውቃቸው ነገሮችን አወቅሁ፤ የማውቀው ነገር ሂሳብ የተማረ ሰው ምን ጊዜም ጭፍን ሎሌ መሆን የማይችል መሆኑን ነው፤ ሂሳብ የተማረውን ሰው ለጭፍን ሎሌነት የሚቀጥረው ሰው ግን አንጎሉ የፈረጠ ነው፡፡

Saturday, October 18, 2014

“የዲግሪና የዲፕሎማ ወፍጮ ቤቶች”


ተፈጭና ተመረቅ – አስተምሮ መለስ
degree mill
በእንግሊዝኛው አጠራር የዲፕሎማ/የዲግሪ ወፍጮ ቤት (diploma/degree mills) ይባላሉ፡፡ በርካታዎቹ ሠለጠነ በሚባለው ዓለም ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ “ወፍጮ ቤቶች” የ“ትምህርት መረጃ” ለማግኘት በጣም ቀላል ነው፡፡ ዋናው መስፈርት አስፈላጊውን “የትምህርት ክፍያ” መፈጸም ብቻ ነው ፡፡ ከዚያ በወርቅ ቅብ የተንቆጠቆጠ “የባችለር” ወይም “የማስተርስ” ወይም “የዶክትሬት (ፒ.ኤች.ዲ.)” ዲግሪዎችን ማፈስ ነው፡፡ በቀጣይ የሚሆነው የ…ሚ/ር ወይም የ…ሚኒስትር ደኤታ ወዘተ መሆንና “በሹመት መዳበር” ነው፡፡ ከዚያ ህዝብ አናት ላይ “በስያሜ” ተቀምጦ መጋለብ ነው።
ከዓመታት በፊት የአሜሪካው የመንግሥት ተጠያቂነት ቢሮ በዚህ ጉዳይ ላይ ምርመራ አካሂዶ ነበር፡፡ ያገኘውንም ውጤት ለእንደራሴዎች ምክር ቤት ሲያቀርብ “የወፍጮ ቤቶቹን” አሠራር በግልጽ ዘርዝሯል፡፡ ለምርመራው ያነሳሳው በአሜሪካ የመንግሥት መ/ቤቶች ውስጥ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ድረስ የሚሠሩ “ከወፍጮ ቤቶቹ” የትምህርት ማስረጃ የሸመቱ መኖራቸውን በማረጋገጡ ነበር፡፡ ይህንንም ተከትሎ ቢሮው ያቋቋመው መርማሪ ቡድን ለሦስት ዓመታት በርካታ ዲፕሎማዎችንና ዲግሪዎችን ከአሜሪካና ከሌሎች የውጭ አገራት በቀላሉ በድብቅ ለመግዛት መቻሉን አረጋግጧል፡፡
አሠራሩን እንዴት እንደሆነ ሲገልጽም፤ ከመርማሪ ቡድን አባላት አንዱ ተማሪ በመምሰል “የትምህርት ተቋማቱን” ዲግሪ እንደሚፈልግ መስሎ ይጠይቃቸዋል፡፡ ክፍያ ካጠናቀቀ መግዛት እንደሚችል “ወፍጮ ቤቶቹ” በነገሩት መሠረት የሳይንስ ባችለር ዲግሪ በባዮሎጂ እንዲሁም የሳይንስ ማስተርስ ዲግሪ በሜዲካል ቴክኖሎጂ “ሸምቷል”፡፡ ክፍያ ለጨመረም ሥራ ቀጣሪዎች የትምህርት ማስረጃውን ለማረጋገጥ ሲደውሉ ሊያነጋግሩበት የሚችሉበት የስልክ መስመር አብሮ ይሰጣል፤ በዚሁ አንጻር በየዲግሪዎቹ “የማዕረግ ተመራቂ” መሆን እንደሚቻል ተረጋግጧል፡፡ በአሜሪካ!!!

Saturday, August 30, 2014

አነጋጋሪው የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የፖሊሲ ስልጠና


[ተማሪዎች የስልጠና ሰነድ በማቃጠል ተቃውሟቸውን አሰምተዋል]

a a u
ተማሪዎችና የፖለቲካ ተቋዋሚ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ፖሊሲ ላይ ያተኮረው ለከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት ተማሪዎች የሚሰጠውሥልጠና ከጥሪው አንስቶ በግዳጅ የሚካሄድ መሆኑን ነው የሚናገሩት የኢትዮጵያ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የሁለት ሳምንታት የፖሊሲ ስልጠና ላይ መሆናቸውን መንግስት አስታውቋል ።
ነሐሴ የተጀመረው ይኽው ስልጠና ተማሪዎች በግዳጅ የሚሳተፉበት መሆኑን አንዳንድ ተማሪዎችና ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ይናገራሉ። መንግሥት ግን ይህን ያስተባብላል።
ተማሪዎችና የፖለቲካ ተቋዋሚ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ፖሊሲ ላይ ያተኮረው ለከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት ተማሪዎች የሚሰጠውሥልጠና ከጥሪው አንስቶ በግዳጅ የሚካሄድ መሆኑን ነው የሚናገሩት። በተለይ በስልጠናው የማይሳተፉ ተማሪዎች በመጪው አመት የትምህርት እድል እንደማያገኙ ይገልፃሉ ።ከዚህ በተጨማሪ የትምህርት ነጻነትና ፖለቲካዊ ሰበካ በመርህ ደረጃ አብረው የማይሄዱ ሆኖ እያለ ተማሪዎችም ይህን አስመልክቶ ቅሬታቸውን እንዳያሰሙ ተቃውሞ እንደገጠማቸው ነው የሚገልፁት። በትምህርት ላይ ሳሉ የኢህአዴግ አባል የሆኑ ተማሪዎች በኩል መመዝገባቸውንና የስልጠና ቅጽ መሙላታቸውን በስልጠናው የሚሳተፉ ተማሪዎች ይናገራሉ። ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ አንድ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ የስልጠናውን አጀንዳዎች ያብራራል።

ለነዋሪዎች አማራጭ የለም!


“ከተማዋ የሕዝብ መጸዳጃ ቤት ሆናለች”

addis ababa 1
በአዲስ አበባ ያለው የመጸዳጃ ቤት ችግር ከልክ ያለፈና መሆኑን የእንግሊዙ ዘ ጋርዲያን ጋዜጣ ዘገበ። ሐሙስ በወጣው የጋዜጣው ድረገጽ ላይ እንዳስነበበው ከ3 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ በሚኖርባት አዲስ አበባ ውስጥ ለሕዝብ መገልገያነት የዋሉት መጸዳጃ ቤቶች 63 ብቻ መሆናቸውን ዘግቧል። አማራጭ ያጡ የከተማዋ ነዋሪዎች ደግሞ ከተማዋ ወደ መጸዳጃ ቤትነት እየተለወጠች መሆኗን በምሬት ገልጸዋል።
ጋርዲያን “Wash Ethiopia Movement” የተባለ አገር በቀል ድርጅት ጠቅሶ እንደዘገበው በከተማዋ ከ10 ቤተሰቦች 9ኙ የጉድጓድ መጸዳጃ ቤት እንደሚጠቀሙና መቀመጫ ባለው መጸዳጃ ቤት የሚጠቀሙት ከ25 ቤተሰቦች አንዱ ብቻ መሆኑን ተናግሯል። በዘገባው መሠረት የከተማዋ ባለሥልጣናት የዛሬ ዓመት ይገነባሉ በሚል የ100ሚሊዮን ብር ዕቅድ የተያዘላቸው መጸዳጃ ቤቶች እንዳሉ መናገራቸውን ጠቅሷል።
A toilet in Addis Ababaበተመሳሳይ ሁኔታ 1ሺህ መጸዳጃ ቤቶችን ለመገንባት የዛሬ ዓመት ተይዞ የነበረ ዕቅድ እስካሁን ተግባራዊ እንዳልሆነ ጋዜጣው የመንግሥት ባለሥልጣንን ጠቅሶ ሲጽፍ ወደፊት መጸዳጃ ቤቶቹ እስኪሰሩ ድረስ በመንገድና ፎቅ “እየተዋበች” ያለችው ከተማ ነዋሪ የት ሄዶ ሊጸዳዳ እንደሚችል ባለሥልጣኑ ስለመናገራቸው የጠቆመው የለም። ይህ የመጸዳጃ ችግር “በአምስቱ ዓመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ባለራዕያዊ ዕቅድ” ውስጥ ስለመካተቱ ከገዢው “አውራ ፓርቲ” ባለሥልጣናት የተነገረ ነገር ስለመኖሩ የተገለጸ ነገር የለም። የአዲስ አበባ የመጸዳጃ ቤት ጉዳይና ሽታ አምስት ከንቲባዎችና ሁለት ጠቅላይ ሚኒስትሮች ተፈራርቀውበታል።
ጋዜጣው በቀን 200 ሰዎች ስለሚጠቀሙባቸው 4 መጸዳጃ ቤቶች ሲዘግብ “ለመጠቀም አስቸጋሪ፣ ለሴቶች የማይመቹ፣ ንጽህናቸው ያልተጠበቀና ጠረናቸው እጅግ የሚሰነፍጥ” መሆኑን አስረድቷል። የመጸዳጃ ቤቶቹ ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል ወ/ሮ ብርሃኔ በመጸዳጃ ቤቶቹ ንጽህና ጉድለት ምክንያት ከጥቂት ወራት በፊት በጠና ታምመው ሆስፒታል መግባታቸውን ገልጸዋል። በርካታ ያካባቢው ነዋሪዎችም በተስቦ፣ በተቅማጥና በሌሎች ተላላፊ በሽታዎች እንደሚጠቁ ተናግረዋል። መጸዳጃ ቤቶቹ የወንድና የሴት ተብለው ካለመከፋፈላቸው በተጨማሪ በተለይ ለሴቶች የሚመቹ ባለመሆናቸው አንዳንድ ሴቶች በፖፖ ቤታቸው እየተጠቀሙ ወደ መጸዳጃ ቤቶቹ እያመጡ እንደሚደፉ በግልጽ አስረድተዋል።

የአንዲት እናት ደብዳቤ፤


ለዝች ደብዳቤ ከአሌክሶ ሰዕል ወጪ የሚሆን ማገኘት አልቻልኩም፤ አሌስ ሰዕልህ ይባረክ!
ለዝች ደብዳቤ ከአሌክሶ ሰዕል ወጪ የሚሆን ማገኘት አልቻልኩም፤ አሌስ ሰዕልህ ይባረክ!
የአንዲት እናት ደብዳቤ፤
ይድረስ በውጪ ሃገር ለምትኖሪው ውድ ልጄ፤
ባለፈው ሰሞንልሽ… ያቺ ከበታቻችን ያለችው ቀጭኗ ሴትዮ… ምነው እንኳ ቀበሌ ገባ ወጣ የምትለው… እ… እርሷ ወደቤታችን ብቅ ብላ ነበር። እና ታድያ፤ ዲያስፖራዋ ልጅዎ እንዴት ነች… ብላ ብትጠይቀኝ ጊዜ ኧረ እኔ እንዲህ የምትባል ልጅ የለችኝም ፍቅርዬ አበራ… ማለትሽ ነው… ብዬ ጠይኳት፤ እርሷቴ ”በውጪ ሀገር የሚገኝ ማንኛውም ሰው ዲያስፖራ ነው የሚባለው” ብላ ነገረችኝ። አከል አድርጋም፤ ”በልማቱ ተሳታፊ ከሆነች ልማታዊ ዲያስፖራ ልማቱን አደናቃፊ ከሆነች ደግሞ የቀድሞ ስርአት ናፋቂ ነው የምትባለው!” ስትል ጨመረችልኝ፤ እኔም እንዳላወቀ እንዳልገባው ሆኜ፤ የወደፊቱ ስርዓት ናፋቂዎች የሚባሉስ የሉም…. ብዬ ብላት፤ ”ምን አሉኝ….” ብላ ስተደናበር፤ የለ…. እንደው ለቤተሰብ ሳታሳውቁ ስም መለዋወጥ ምን ይሉት ፈሊጥ ነው… ብዬ ገርሞኝ ነው…. እያልኩ፤ ሳዳርቃት ዋልኩልሽ… እንዲህ በሆነ ባለሆነ ያዝ ካላደረግናቸው የነርሱ ፓለቲካ ማለቂያም የለው ልጄ….
የሆነው ሁኖ… አንቺ እንዴት አለሽልኝ፤ እኔ እናትሽ ካንቺ ሃስብ እና ናፍቆት በቀረ እጅጉን ደህና ነኝ።
እንዳልኩሽ፤ ሰሞኑን የቀበሌ ሰዎች ወደቤት መጣ መጣ ማለት አብዝተውብናል… ምክኝያቱ ምን እንደሁ እስቲ ከእኛ እናንተ ታውቁታላችሁና ምን ፈልገው እንደሆነ አጣርተሽ ነግሪኝ፤ እውነቴን ነው ልጄ እንደውም አሁን ይቺን ኢሳቴን ከተከልኩ ኋላ ትንሽ ሻል አለኝ እንጂ ድሮማ ኢቶጵያ ቴሌቪዥን የሚለንን ብቻ እየሰማን የመረጃ ድርቅ ገብቶን ነበር። እርግጥ አንዳንድ ወቅት ዜናውን ገልብጦ በመስማት እውነቱን እንረዳዋለን ለምሳሌ፤ ”አንዳንድ አሸባሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ” የሚል ዜና የተነገረ እንደሆነ አንድንድ ጀግኖች እና ለሀገር ያገባኛል የሚሉ ወገኖች፤ ታግተዋል ማለት ነው… ብለን እየተረጎምን ሃቋን እናገኛታለነ!

Wednesday, August 27, 2014

የተማሪዎች ተቃውሞ ተጠናክሮ ቀጥሏል


(ሥርዓቱን ለ 20ዓመት አይተነዋል መቀየር አለበት!)

Addis_Abeba_University
  • የኢትዮጵያ የባህር በር ለኤርትራ መሰጠቱ ስህተት ነው
  • የኢኮኖሚ እደገቱ እውነት አይደለም
  • የትምህርት ስርዓቱ ወድቋል
  • የተማረ ሰው ክብር አይሰጠውም
አዲስ አበባ ውስጥ ሳውዝ ካምፓስ (ልደታ)፣ አቃቂ (AASTU)፣ ፍቼ የግብርና ኮሌጅ፣ ስድስት ኪሎ፣ አምስት ኪሎ፣ አራት ኪሎ፣ የአዲስ አበባ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስት ትምህርት ክፍልና ሌሎችም አካባቢዎች ከነሃሴ 15 ጀምሮ ስልጠና ላይ የሚገኙ የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኞች ተቃውሟቸውን ማሰማታቸውን እንደቀጠሉ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡ ተማሪዎቹ ገዥው ፓርቲ አለ በሚለው እድገት፣ የባህር በር፣ የተማረው የማህበረሰብ በሚደርስበት በደል፣ የትምህርት ጥራት፣ የመምህራን የእውቀት ደረጃ ማነስ፣ ድህነትና አጠቃላይ ኢኮኖሚ ውድቀት ላይ ጠንከር ያለ አስተያየትና ተቃውሞ መሰንዘራቸውን ተገልጾአል፡፡
የኢኮኖሚ እድገት
ተቃውሞ ከገጠማቸው ጉዳዮች መካከል የኢኮኖሚ እድገት አለ የለም የሚለው ሲሆን ተማሪዎቹ ‹‹በአክሱም ዘመን ገናና የነበረችው ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በኢኮኖሚው መስክ ጭራ›› መሆኗን በመግለጽ እድገቱ አለ መባሉ ስህተት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ተማሪዎቹ ጨምረውም “በቀን አንድ ጊዜ እንኳን መመገብ የማይችል ማህበረሰብ ይዘን አድገናል ማለት አንችልም” በሚል እድገት አለመኖሩን ተከራክረዋል፡፡ “ሀገራችን ውስጥ የምግብ፣ የቤት፣ የትምህርት፣ የኔትወርክና ሌሎች ችግሮች አሉ፡፡ ስኳርና ዘይት ለመግዛት ህዝብ ቀበሌ ተሰልፎ ነው የሚውለው፡፡ በ400 ብር ደምወዝ ቤተሰብ የሚያስተዳድር ህዝብ ያለባት ሀገር የሌሎችን እድገት ፈዛ እያየች ያለችን ሀገር አድጋለች ልንል አይገባም” ማለታቸው ተገልጾአል፡፡

Saturday, August 23, 2014

የውሸት አባት 2ኛ ሙት ዓመት


ነዶ የማያልቀው [ሻማ] የኢትዮጵያ ሕዝብ

skull candle
ግንቦት 20፣ 1983ዓም መለስ ወይም ለገሠ ወይም አስረስ ወይም ዜናዊ ወይም … ትክክለኛ ስሙን በውል የማናውቀው ከነጭፍሮቹ ቤተመንግሥት ገብቶ ራሱን አጼያዊ ፕሬዚዳንት፣ ቀጥሎም አጼያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ … በማድረግ ከሾመበት ቀን ጀምሮ የኢትዮጵያ ሕዝብ በኦፊሴል እንደ ሻማ ወይም እንደ ኩራዝ ተለኩሷል።
አቀጣጣዮቹ ምስለኔዎች ከሻማና ከኩራዝ ከፍ ብለው ብርጭቆ የለበሱ ፋኖሶች ሆነዋል። ለመለስና ለጭፍሮቹ የሚያበሩ ፋኖሶቹም (ኦህዴድ፣ ብአዴን፣ …)፣ ኩራዞቹም፣ ሻማዎቹም የበራላቸው ማሾዎች (ህወሃቶች) ሁሉም በአንድነት ዛሬ ላይ ደርሰዋል። ለኳሹም ተለኳሹም እያበሩ የአስለኳሹን ሁለተኛ ሙት ዓመት “እያከበሩ” ነው። በሌላ አነጋገር ለሙት መንፈስ እሣት አንድደው እየሰገዱ ነው። ተገድዶ እየነደደ ያለውን ሕዝብ፣ አዳዲሶቹ አስለኳሾች (የኃይለማርያም ደቦ አስተዳደር) ሕዝብን ሻማ ላደረገውና ከስሙ ጀምሮ በውል ማንነቱ ላልታወቀው ግለሰብ “ሻማ አብሩ” አሉለት።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ለሁለተኛው ሙት ዓመት “የውርስ መታሰቢያነት” ከዚህ በታች ያለውን የመክብብ ማሞን ጽሑፍ ሲያቀርብ በመለስ ሞት ላዘኑ ሁሉ ለሃዘናቸው መጉመጥመጫ እንዲሆን በማሰብ ነው። “የውሸት አባት” መለስ ነፍስ ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ ስዩመ አብዮታዊ ዴሞክራሲ አጼ አድርጎ ራሱን በመሰየም ሕዝብን እንደሻማ ባነደደበት ዘመናት ከአንደበቱ ሲወጡ የተመዘገቡ ውሸቶች ስፍር ቁጥር የላቸውም።
በተለይ ግን በ1997ቱ ምርጫ ሰሞን ሕዝብ እንደ ሻማ ከመቃጠልና ከመንደድ የራሱን መሪ እንዳይመርጥ የዋሸው ውሸት ከዚህ በታች ሰፍሯል። ታዲያ ሕዝብ እንደ ሻማ ከመቅለጥ የሚያድነውን እንዳይመርጥ ለገደበ ግለሰብ እንዴት ሻማ ይበራለታል?!
“ማሾዎቹ” ደረት ቢደቁ፣ ከበሮ ቢደልቁ፣ ፈንዲሻ ቢበትኑ፣ አሸንዳ ቢዘሉ፣ ሠርግና ምላሽ ቢያደርጉ፣ “አንጓይ ፍስስ” ቢሉ፣ … ምክንያት አላቸው። እንደ ዱር አውሬ “የአገር ቅርስ” ሲሉት ውለው ቢያድሩ ከልካይ ሊኖራቸው አይችልም። በሚሊዮን ሕዝብ ችግር ላይ ቆመው ለሙት መንፈስ ቢንደባለሉ ደንታ የላቸውም። ሚሊዮኖች በሚያዝኑበት አገር፣ እስር ቤትና ማጎሪያዎች ውሥጥ የታፈኑት ሲቃ በሚያሰሙበት አገር እነርሱ ሙት ዓመትን አስረሽ ምቺው ቢያደርጉት ማን ተዉ ሊላቸው ይችላል?! ምክንያቱም ብርሃን ይፈልጋሉ፤ ለዚያ ደግሞ ነዶ የማያልቅ ሻማ ያስፈልጋል።
ለማንኛውም መጪው የምርጫ ጊዜ ነውና የወደፊቱን ውሸት ከዚህ በታች በሰፈረው የመክብብ ማሞ ጦማር እያጣቀሳችሁ የ… ዜናዊን ሙት ዓመት አክብሩ። ለኢትዮጵያ እውነተኛ ስም ያለውና ለዘመናት በዚያው ስሙ የሚጠራ መሪ ይስጣት።
“ውሸታም!”
ሰሞኑን (ይህ ጽሁፍ የተጻፈው በመስከረም 2002/Sept. 2009 ነው) የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት የሳበ አንድ ክስተት በአሜሪካ ተፈጽሟል። ፕሬዚዳንት ኦባማ በምርጫ ዘመቻቸው ጊዜ ቃል የገቡለትን የጤና ጥበቃ ማሻሻያ አዋጅ እንዲጸድቅ የሕዝብ ተወካዮችን ሰብስበው ንግግር በሚያደርጉበት ወቅት ከተቃዋሚ የሪፓብሊካኑ ወገን የማርጎምገምና የተቃውሞ ድምጽ ተሰማ። በተለይ ግን የጤናው ማሻሻያ አዋጅ “ሕገወጥ ስደተኞችን አያካትትም” የሚል ንግግር ባደረጉ ጊዜ ከደቡብ ካሮላይናው እንደራሴ “ውሸታም!” የሚል ድምጽ አስተጋባ።

Sunday, August 17, 2014

የኢትዮጵያ መንግስት ኢቦላን ለምን ፈለገው…!?


Ethiopian-Airlineየኢትዮጵያ መንግስት ኢቦላን ለምን ፈለገው…!
ትላንት እነ ዮሃንስ ሞላ (ዮሃንስ ሞላ የብርሃን ልክፍት መድብል አሰናጅ ነው) እነርሱ የሚቀኙላትን ቅዳሜን የመሰለች ቀን ራሴን ክፉኛ ታምሜ አሳለፍኳት። ከመዕራብ አፍሪካ የመጣ ሰው ጋር ባለመገናኘቴ እንጂ የትኩሳቴ ነገር በሌላ የሚያስጠረጥር ነበር። (ሌላ የተባለው ኢቦላ ነው… ደጋግሞ በመጥራት ራሱ ይመጣብን ይሆን እንዴ እያልን ተሳቀን ሞትን እኮ ጃል…!
ከትላንት በስቲያ አይደል እንዴ… አየር መንገዳችን ከዩንጋንዳ ካምፓላ የመጣ አንድ ሰውዬ የበዛ ትኩሳት ታይቶበታል ብሎ ለኢቦላ መመርመሪያ ጣቢያ በተዘጋጀ ልዩ ስርፋ አስገብቶ የበዛ ምርመራ ሲያደረግለት ያየነው…!
እኔ የምለው እንዲህ ምልክት የሚመስል ነገር ሲታይ አፋጣኝ ምርመራ ማድረጉ ባልከፋ… ነገር ግን አየር መንገዳችን እስካሁንም ድረስ በመጨባበጥ ሁላ የሚተላለፈው አደገኛ ቫይረስ ወደተቀሰቀሰብት ምዕራብ አፍሪካ በረራ ማድረጉ ምኑን ተማምኖ ነው.. እንደሆነ ለምን አይነገረንም…!
በርካታ ሀገሮች፤ ለዛው በህክምናውም በመከላከሉም ዋዛ ያልሆኑቱ፤ ወደ ምዕራብ አፍሪካ ድርሽ አንልም ብለው ሲታቀቡ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ድርስ ምልስ፣ ድርስ ምልስ… እያለ እንደ ውሃ ቀጂ ሲመላልስ ብናይ የምርም ”የኢትዮጵያ መንግስት ኢቦላን ለምን ፈለገው…!” ብለን እየተጨነቅን እንገኛለን። መንግስት ኢቦላን አልፈለገውም ብሎ የሚሞግተን አካል ቢመጣ እንኳ ቢያንስ ነገር ሲፈልገው እያየን ነው ብለን እማኝነታችንን መስጠታችን አይቀሬ ነው…
እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ነገር ከገባ በቀላሉ አይወጣም። እንኳንስ ኢቦላ ይቀርና ኢህአዴግም እንኳ አልወጣ ብሎናል… (ልል ነበር ”ጽንፈኛ ዲያስፖራ ተቃዋሚ…” እንዳልባል ብዬ ትቼዋለሁ…) እውነቱን ለመናገር ግን አንድ መንግስት እንደ መንግስት ከሚያሳዩት ነገሮች አንዱ በህዝቡ ላይ ስጋት የሚሆኑ ነገሮች እንዳይከሰቱ መከላከል ነው። ሆን ብሎ በክፉ ልቦና ተነሳስቶ፤ አልያም ደግሞ በድንገት እና በነዋይ ፍቅር ተሳስቶ ህዝቡን ለስጋት የሚዳርግ ከሆነ መንግስት ሳይሆን መቅሰፍት ነው ብለን ከመደምደም ወደኋላ አንልም።
እናም አየር መንገዳችን፤ በበኩሌ ሳልናገር ብዬ እንዳይጸጽተኝ፤ ይሄ ኢቦላ የተባለ ክፉ ደዌ ወደ ሀገር ቤት ቢገባ ካንተ ራስ አንወርድም እና ካሁኑ ወደ አደገኛ ሀገሮች ከመብረር ክንፍህን ሰብስብ ለማለት እወዳለሁ!

Thursday, August 7, 2014

የዋሽንግተኑን የአፍሪቃ መሪዎች ጉባኤ ኢትዮጵያውያን ተቃወሙት


"ኦባማ ዝምታው ይብቃ"

ethio us
ኢትዮጵያውንና ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን በዛሬው እለት በዋሽንግተን ዲሲ የተከፈተውንና በዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ከአፍሪቃ መሪዎች ጋር የሚያደርጉትን ጉባኤ በመቃወም አደባባይ ወጥተዋል።
“በኢትዮጵያ የሚታየው የሰብዓዊ መብት ረገጣ እንዲቆም አዎንታዊና ተጨባጭ ግፊት በማድረግ ፋንታ፤ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶቹን አራማጆች በመደገፍ ሁኔታው ይበልጥ እንዲባባስ እያደረገ ነው፤” ሲሉ ከተለያዩ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች የመጡ መሆናቸውን ያስታወቁት የሰልፉ ተሳታፊዎች የኦባማን አስተዳደር ኮንነዋል።
ስብሰባውን አስመልክቶ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ወደ ርዕሰ-ብሔርነቱ በዘለቁ ወቅት ሃገራቸው ከነበረችበት የምጣኔ ኃብት ድቀት አሁን እያገገመች በመሆኗ ትኩረታቸውን ለአፍሪካ እየሰጡ መሆኑን የሚያሳዩ ክንዋኔዎችን እያደረጉ ነው በማለት ቀድሞ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሣደር የነበሩትና የጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር ዴቪድ ሺን መናገራቸውን ያሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ዘግቦ ነበር፡፡

Friday, August 1, 2014

ዘረኛው የትግሬ-ወያኔ ቡድን በሰሜን ጎንደር የዐማራ ሕዝብ ላይ የፈጸመው የዘር ማጽዳት እና የዘር ማጥፋት ወንጀል

end genocide now
የትግሬ-ወያኔ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት አቅዶ ሲነሳ፣ የግቡ መረማመጃ ያደረገው የኢትዮጵያዊነት መገለጫ የሆኑ ተቋሞችን፣ ኃይማኖቶችን፣ ዕሴቶችን እና በተለይም «ዐማራ» የተሰኘውን ነገድ ተወላጆች ነጥሎ ማጥፋት የሚል ሥልት በመከተል እንደሆነ ይታወቃል። በዚህም መሠረት የጥፋቱ ቅድሚያ ዒላማ ያደረገው ለትግራይ ሕዝብ በችግሩ ጊዜ ደራሽ እና የተራበ አንጀታቸውን ዳሳሽ በሆነው የወልቃይት፣ የጠገዴ፣ የጠለምትና የሠቲት ወረዳዎች ሕዝብ ላይ ነው። ወያኔ በእነዚህ የትግሬ አዋሣኝ ወረዳዎች ሕዝብ ላይ የጥፋት ክንዱን የዘረጋው በሦስት መሠረታዊ ምክንያቶች ነው።
የመጀመሪያውና ታላቁ ምክንያት የእነዚህ ወረዳዎች ሕዝብ ዐማራ በመሆኑ እና የትግራይ አዋሳኝ ስለሆነ የትግራይን ታሪክ ክፉውንም ሆነ ደጉን ጠንቅቆ የሚያውቅ በመሆኑ ነው። በዚህም ምክንያት የዚያ አካባቢ ሕዝብ የትግሬ-ወያኔ ለተነሳለት ፀረ-ኢትዮጵያ እና ፀረ-ዐማራ እንቅስቃሴ የማይተኛ እንደሆነ ስለሚረዳ ይህን ሕዝብ ብቻውን አቁሞ ማጥፋት ለወደፊቱ ግሥጋሴው ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥርላቸው በማመን የችግር ጊዜ ደራሻቸውን ሕዝብ ያለርኅራኄ ጨፍጭፈውታል።
ሁለተኛው ምክንያት «ታላቋን ትግራይ» ለመመሥረት ባላቸው ዕቅድ ለውጭ ግንኙነታቸው መውጫ መግቢያ እንዲሆናቸው ከሱዳን ጋር የሚዋሰኑትን እነዚህን ወረዳዎች ወደ ትግራይ ማጠቃለል ስለነበረባቸው ነው። ሆኖም የአካባቢው ሕዝብ «ነገዳችን ዐማራ፣ ጠቅላይ ግዛታችን ጎንደር ነው።» እያለ እንዳያስቸግራቸው በቅድሚያ ነባር ነዋሪውን ጎንደሬ አጥፍቶ በሠፋሪ ትግሬ ማስያዝ ለዓላማቸው ሥምረት ያገለግላል ብለው በማመናቸው ነው።

Friday, July 25, 2014

ፖሊሶቻችን ተዉ ቀልብ ግዙ!


Untitled-1ፖሊሶቻችን ተዉ ቀልብ ግዙ!
ይሄንን ፎቶ ልብ ብዬ እንዳየሁት፤
የሆነው ባለፈው አርብ የረመዳን ጁማዓ ጸሎት በሚደረግበት ወቅት ነበር። ሙስሊሙ ህብረተሰብ እንደተለመደው ሰላማዊ ተቃውሞውን ለማሰማት ገና ሲጀመር፤ ሌላ የፎቶ ማስረጃ እንዳሳየን ፖሊሶች ድንጋይ መወርወር ጀመሩ፤ (ይሄንን ስንናገር እየተሸማቀቅንም ቢሆን ግን እውነት ነው) በዚህም ብጥብጡ ተነሳ ፖሊሶች ያገኙትን መደብደብ ጀመሩ፤ ድብደባው እስላም ክርስቲያን ያለየ ለመሆኑ የሰማያዊ ፓርቲዋ ወይንሸት ሞላ እማኝ ነች። በእለቱ ፖሊሶች እና ደህንነቶች ያደረሱትን ስቃይ ድምጻችን ይሰማ ዎች ”ጥቁር ሽብር” ብለው ሰይመውታል።
በፎቶው ላይ የሚታዩት ሙስሊም ሰውዬም እንግዲህ ከተደብዳቢዎች አንዱ ነበሩ ማለት ነው። በዚህ ድብደባ ላይ የሚያስገርሙ ሁለት መሰረታዊ ነገሮች አሉ። አንደኛው እኒህ ሰውዬን ለመደብደብ ስምንት ፖሊሶች ከበዋቸዋል። ”አንድ ለአምስቱ አደረጃጀት ወደ አንድ ለስምንት አደገ” ብለን እንዳናሾፍ፤ እየተደደቡ ያሉት ሰብዓዊ ፍጡር ናቸው እና ለቀልድ አይመችም። ሁለተኛው እና በጣም የሚደንቀው ግን የፖሊሶቹ ፈገግታ ነው። አንዳንዶቹማ ፍንክንክ እያሉ ሲስቁ የሰርግ ጌሾ የሚወቅጡ እንጂ እንደነርሱ ሰው የሆንነ ፍጡር የሚደበድቡ አይመስሉም።
እነዚህ ፖሊሶች በአደባባይ እንዲህ ከደበደቡን በየእስር ቤቱ ጓዳማ ምን እያደረጉን እንደሆነ መገመት ይጨንቃል።
እወነቱን ለመናገር የመጨረሻው ቀን ቀርቧል። ሌላው ሁሉ ቢቀር እንዲህ እየተደበደብን ኢህአዴግን ከሚቀጥለው ምርጫ አናሳልፈውም። ኑሮ የሚደበድበን አንሶ ያልጠገቡ የመንግ ፖሊሶች ደግሞ እየደበደቡን መኖርን የምንመርጥ እኛ ማን ነን…
ፖሊሶቻችን ተዉ… ሞልቶ ለማይሞላ አዱኛ፤ ቀለባችሁን ብቻ አትመልከቱ ቀልብም ለመግዛት ሞክሩ።

Friday, July 18, 2014

በኢትዮጵያ የእንግሊዝ እርዳታ ፖሊሲ ተግባራዊነት እንዲፈተሽ ታዘዘ


dfid
የእንግሊዝ የባሕር ማዶ ትብብር ኤጀንሲ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ሲሰጥ ከራሱ የሰብዓዊ መብቶች ፖሊሲዎች ጋር በተጣጣመ መልክ መሆንና አለመሆኑ እንዲፈተሽ አንድ የእንግሊዝ ፍርድ ቤት መወሰኑን የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቹ ሂዩማን ራይትስ ዋች አድንቋል፡፡
ሌስሊ ሌፍኮው - የሂዩማን ራይትስ ዋች የአፍሪካ መርኃግብር ምክትል ዳይሬክተር
ሌስሊ ሌፍኮው – የሂዩማን ራይትስ ዋች የአፍሪካ መርኃግብር ምክትል ዳይሬክተር
የእንግሊዝ የባሕር ማዶ ትብብር ኤጀንሲ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ሲሰጥ ከራሱ የሰብዓዊ መብቶች ፖሊሲዎች ጋር በተጣጣመ መልክ መሆንና አለመሆኑ እንዲፈተሽ አንድ የእንግሊዝ ፍርድ ቤት መወሰኑን የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቹ ሂዩማን ራይትስ ዋች አድንቋል፡፡
የእንግሊዝ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትናንት፤ ሐምሌ 7/2006 ዓ.ም ባሣለፈው ውሣኔ የዓለም አቀፍ ትብብር መሥሪያ ቤቱ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ሲሰጥ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን የሚያሳዩ ማስረጃዎችን በበቂ ሁኔታ አይፈትሽም ሲባል የቀረበበት ክሥ ሙሉ የፍርድ ቤት ምርመራ የሚያስፈልገው ነው ብሏል፡፡
የሂዩማን ራይትስ ዋች የአፍሪካ መርኃግብር ምክትል ዳይሬክተር ሌስሊ ሌፍኮው ለዝግጅት ክፍላችን በሰጡት ቃል ይህ የእንግሊዝ ፍርድ ቤት ውሣኔ ገና የመጀመሪያ እርምጃና ሊደነቅ የሚገባው ነው ብለዋል፡፡
በጋምቤላ፣ በሶማሌ ክልልና በደቡብ ኦሞ እየተፈፀሙ ናቸው ያሏቸው አድራጎቶችም የቅርብ ፍተሻ የሚያስፈልጋቸው መሆናቸውን የጠቆሙት ሚስ ሌፍኮው ልማት ከሰብዓዊ መብቶች መከበር ጋር አብሮ መታየት እንደሚገባቸው ለጋሾች ሊገነዘቡ ይገባል ብለዋል ሚስ ሌፍኮው፡፡
መሠረታዊ የልማት ድጋፍ ይቁም የሚል አቋም ሂዩማን ራይትስ ዋች እንደሌለው ሌፍኮው አመልክተው የእንግሊዝ መንግሥት ለኢትዮጵያ በሚሰጠው እርዳታ ሰብዓዊ መብቶችን የሚረግጡ ፕሮጀክቶችን የሚያስፈፅሙ ባለሥልጣናት ደመወዝ እንደሚከፈል አመልክተዋል፡፡

የማይጮኹት . . . በዓሉ ግርማን የበሉት ጅቦች


heyans vs lion
ይህችን ውድ የሆነች ትንሽ ቁራሽ ሕይወት እንደ አብርሃም ቤት የለኝ፣ እንደ ሙሴ መቃብሬ ላይታወቅ፡፡ መኖር – መጻፍ – ሕይወትን በተስፋ ወደፊት እየኖርኩና ወደኋላም እያስተዋልኳት፡፡” በዓሉ ግርማ – ደራሲው
1እውቁን ጋዜጠኛና ደራሲ በዓሉ ግርማን በአጸደ ሕይወት ካጣነው፤ በዘንድሮው የካቲት 24 ቀን 2006 ዓ.ም. ሠላሳ ዓመታት  ተቆጥረዋል፡፡ ውድ ባለቤቱ ወይዘሮ አልማዝ አበራ በዘመነ ኢሕአዴግ ስለ ባለቤቷ ከቤት እንደወጣ መቅረት ጉዳይ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ቀርባ የጠቅላይ አቃቤ ሕግ ምስክርነቷን እንድትሰጥ ተደርጋ ነበር፡፡ ያንን የእሷን የፍርድ ቤት የምስክርነት ቃል የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አቅርቦ ካስደመጠንም ሁለት አሠርታት ዓመታት እንደዋዛ ሊቆጠሩ ነው፡፡ ውድ ባለቤቱ ወ/ሮ አልማዝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት  ያቀረበችውና እልክና ቁጭት የተመላበት የምስክርነት ቃሏ አንድምታ እንዲህ የሚል ነበር፡፡
“. . . የካቲት 24 ቀን 1976 ዓ.ም. ቀን ላይ አስፋው ዳምጤ እቤት ስልክ ደወለ፡፡ በዓሉ ቤት አልነበረምና ስልኩን አነስቼ ያነጋገርኩት እኔ ነበርኩ፡፡ የእግዜር ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ ‘. . . በዓሉ እንደመጣ እዚያ እቀጠሯችን ቦታ ባስቸኳይ እንድትመጣ ብሎሃል በዪልኝ . . . ’ ብሎ ስልኩን ዘጋ፡፡ በዓሉ ወደ አሥራ አንድ ሰዓት ገደማ ወደ ቤት ሲመጣ መልእክቱን ነገርኩት፡፡ ወዲያው ሻወር ወስዶ ወጣና ለመሄድ ሲጣደፍ፣ ’እደጅ ውለህ መምጣትህ ነውና እባክህ ትንሽ እህል ብጤ ቀምሰህ ውጣ’ ብለው፤ ‘አልችልም. . . ብርቱ ቀጠሮ አለንና ወደዚያው መፍጥን አለብኝ’ ብሎኝ ፈጥኖ ከቤት ወጣ፡፡  የማታ ማታ ወደቤት ይመለሳል ብዬ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ብጠብቅም የውሃ ሽታ እንደሆነ ቀረ፡፡ ቢቸግረኝ አስፋው ቤት ደወልኩ፡፡ ሚስቱ ስልኩን አነሳች፡፡ ‘. . . አስፋው እቤት ገብቷል?. . .’ ስል ጠየቅኋት፡፡ ‘. . . አዎን ገብቷል. . .’ አለችኝ፡፡ ይሄኔ ግራ በመጋባት፤ ‘. . . ባሌን ከቤት ጠርቶ ወስዶት የት ጥሎት ነው እሱ ተቤቱ የገባው?. . .’ እያልኩ አፋጠጥኳት፡፡ ቀጥዬም ‘እስኪ አቅርቢልኝና ላናግረው. . .’ ስላት፤ ‘የገባ መስሎኝ ነበር እንጂ አልገባም’ ብላ የመጀመሪያ ቃልዋን አጠፈችብኝ፡፡ የስልክ ንግግራችንም በዚሁ ተቋጨ፡፡ ሌሊቱንም እሱን ያየ እያልኩ በየቦታው እየደወልኩ ብጠይቅም፤ አየነው የሚል ሰው ሳላገኝ ነጋልኝ. . . አሁንም ለክቡር ፍርድ ቤቱ አቤት የምለው፤ አስፋው ዳምጤ ባለቤቴን በዓሉ ግርማን ከቤት ጠርቶ ወስዶ የት እንዳደረሰው ቀርቦ እንዲጠየቅልኝ ነው. . .” ስትል ነበር – ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ምጻኔዋን ያቀረበችው፡፡ ወ/ሮ አልማዝ ይህንኑ ካስፋው ዳምጤ ጋር የተያያዘ ጉዳይ፣ ለዚህ ጽሑፍ አቅራቢና ባሁኑ ጊዜ ተቀማጭነቱ ባሜሪካን አገር ለሆነ አንድ ሌላ ጋዜጠኛ ልንጠይቃት ወደ መኖሪያ ቤታቸው በሄድን ጊዜ ይህንኑ ሁኔታ ዘርዝራ አጫውታን እንደነበር ያስታውሳል፡፡

Sunday, July 13, 2014

ጥላቻ በዛ፣ ቂም አበበ፣ በቀል አፈራ!! ኢህአዴግም አልረካም


የአንዳርጋቸው ጽጌ ጉዞ አስቀድሞ እንዴት ታወቀ?

prisoners1
“እነሱ ሁለት አገር አላቸው። ኢትዮጵያን ይዘዋታል። በስደትም እንደፈለጋቸው እየኖሩ ነው። እኛ ግን አንድም አገር የለንም። በስደት እንኳን እንዳንኖር እየተደረግን ነው። ሸሽተን በተሰደድንበት ምድር እንኳን ዋስትና የለንም። ከዚህ በላይ ምን ይምጣ?” ይህንን የዛሬ ሶስት ወር ገደማ ለጎልጉል የተናገሩት በኖርዌይ የኢትዮጵያ ስደተኞች ማህበር ጸሐፊ ወ/ት የሺሃረግ በቀለ ነበሩ። የወ/ት የሺሃረግን ሃሳብ በመንተራስ ለጎልጉል አስተያየት የሰጡ እንዳሉት “አገር ውስጥም እስር፣ በስድት ምድርም ስጋትና እስር ካለ፣ የይለይለት መንፈስ መነሳቱ አይቀርም። ሰዎች የመኖር ተስፋቸው ሲመናመን የፈለገው ይምጣ ይላሉ። አሁን ኢህአዴግ ከስጋቱ ብዛት እየፈጸመ ያለው ድርጊት ሰዉን ሁሉ ወደዚሁ የሚያመራ ነው።”
ሰሞኑን ኢህአዴግ የወሰደውን፣ ቀደም ሲልም በተመሳሳይ ሲከናውን የቆየውን፣ ወደፊትም በቀጣይነት የሚገፋበትን እስርና አፈና አስመልክቶ የተፈጠረው ስሜት ከራር ነው። ኢህአዴግ ቋንቋው ሁሉ እስር መሆኑ እየፈጠረ ያለው ስሜት ኬላና ልጓሙ እንዳይፈርስ የሚሰጉ ጥቂት አይደሉም። የኢህአዴግ የአፈና መረብ ያልገባበት ቤትና መንድር እንዲሁም ክልል የለም። በሃይማኖት ቤትም ያለው እሳትና ችግር ቀን የሚጠብቅ ነው። ኢህአዴግ ግን ሁኔታዎችን ከመመርመር ይልቅ ቋንቋውና መፍትሄው እስርና አፈና ብቻ መሆኑ አስገራሚ እንደሆነ ስምምነት አለ።
የሰሞኑ አጀንዳ
“የጦር አውሮፕላን በመያዝ ኢህአዴግን ያመለጡ ወገኖች የመን አመቺ ብትሆንም እንደማይመርጧት ይናገራሉ። የመን ከቶውንም የማይታመን አገር እንደሆነ ሰፊ ግንዛቤ አለ። አቶ አንዳርጋቸው ታዲያ እንዴት ሰንአን ረገጡ? ምን ቀን ጣላቸው? እሳቸው በየመን ትራንዚት እንደሚያደርጉ አስቀድሞ መረጃው እንዴት ደረሰ? ከሦስት ሳምንት በፊት ስለሚያደርጉት በረራ ማን? እንዴት? መረጃ አስተላለፈ? የሚሉት ጉዳዮች በዋናነት መመርመር ግድ ነው። ቀጣዩ የቤት ስራም ይህ ነው።” ይህ በኢሜል ከደረሰን በፖሊሲያችን መሰረት ከማናትመው ሰፊ ጽሁፍ የተቀነጨበ ነው። ጽሁፉ ሌሎች የበረራ አማራጮች ስለመኖራቸውም ያወሳል። አቶ አንዳርጋቸው በተያዙበት ቅጽበት ወደ አዲስ አበባ መላካቸውና በበነጋታው ሽያጩ በትዕዛዝ ይፋ የሆነው የኢትዮጵያ ትምባሆ ሞኖፖል የትራንስ ኢትዮጵያ ሸሪክ ድርጅት ስለመሆኑም ይጠቅሳል።

Saturday, June 14, 2014

የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ጉዳይ ለምን አይቋጭም?


"የለዘብተኞችና የእስስት” ፖለቲካ ልዩነት እየፈጠረ ነው

ethio er
መለስ በሁለቱ አገሮች ድንበር ላይ “የጅራፍ ድምጽ እንኳን አይሰማም” በማለት ሲመጻደቁበት የነበረው የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በ”ወረራ” እና “ወረራን መቀልበስ” በሚል ድራማ ተጀምሮ ከተቋጨ አስራ አምስት ዓመት አልፎታል። ኢህአዴግና ሻዕቢያ ጉዳያቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ ወይም በጡንቻ መቋጨት ያልቻሉበት ምክንያት ለብዙዎች እንቆቅልሽ ሆኖ እስካሁን አለ። ሁለቱም ወገኖች ድንበር ላይ ወታደር አፍስሰው መቀመጣቸውን አስመልከቶ “አውቀው ነው” ከሚለው ውሃ የማይቋጥርአስተያየት ጀምሮ በርካታ ጉዳዮች በገሃድና በሹክሹክታ ሲሰማ ቆይቷል።
ጎልጉል የዜና ምንጮች ሰሞኑን ከአዲስ አበባ የላኩት መረጃ ግን በይዘቱ የተለየ ነው። ይህንኑ አዲስ ጉዳይ የሚመለከታቸው ክፍሎች አስተያት እንዲሰጡበት ያደረግነው ሙከራ ባይሳካም ዜናው ለውይይት የሚጋብዝ በመሆኑ አትመነዋል
የድንበር ውዝግቡ አንዲቋጭ ይፈለጋል?
የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ውዝግብ ጦርነት ከኢትዮጵያ ወገን ብቻ ከ100 ሺህ በላይ ጉዳዩ በውል ያልገባቸው ወገኖች ህይወት የተገበረበት ነው። የአይደር ትምህርት ቤት ህጻናትን ጨምሮ የበርካታ ሰላማዊ ዜጎችንና ህጻናትን ህይወትም ቀጥፎ አልፏል። አቶ መለስ ለዚህ ሁሉ ቀውስ ተጠያቂ ቢሆኑም በድንገት ተስፈንጥረው ፍርድ ቤት ህግ ሳይጠቀስባቸው አልፈዋል። “ታላቁ መሪ” በህይወት እያሉ በኤርትራ ጉዳይ በተፈጠረ አለመግባባት ትግራይ ውስጥ እስከመታገት ቢደርሱም ከጥንቃቄ ጉድለት በአንጋቾቻቸው ፈጥኖ ደራሽነት ተርፈው ተቃዋሚዎቻቸውን “ውህዳን” በማለት በየተራ አራግፈው ብቻቸውን “ውርስና ቅርስ” ለመሆን በቅተዋል።
ayider
አይደር
ከህንፍሽፍሽ፣ የልዩነት ጊዜ ጀምሮ አደባባይ የወጣው የልዩነት መሰረት በወቅቱ ይፋ ሲደርግ ኢትዮጵያውያንን አሳዝኖና አስቆጥቶ እንደነበር በወቅቱ በስፋት የተዘገበበት ጉዳይ ነው። ዛሬም ይህ ወቅት ዳግም እየተመለሰ እንደሆነ እየተሰማ ነው። “የኤርትራን ጉዳይ እንቋጭ” የሚሉ የከረረ አቋም ያላቸው ተነስተዋል። እነዚህ ወገኖች ሁለት አማራጭ በማቅረብ ሃሳባቸው ተግባራዊ ሊሆን እንደሚችል እየወተወቱ ነው።
የመጀመሪያው አሁን ያለው የመከላከያ አቅም የድንበሩን ውዝግብ በሃይል ለመቋጨት አቅም እንዳለው እየታመነ ለምን “ቸልተኛነት ተመረጠ” በሚል በቂ ጡንቻ ስለመገንባቱ አበክረው የሚከራከሩበት አግባብ ነው። ሁለተኛው ደግሞ “የኤርትራን ተቃዋሚዎች አደራጅተናል፤ ለምን እነሱ ወደ ኦፕሬሽን አይገቡም” የሚል እንደሆነ መረጃዎቻችን ያስረዳሉ።
ቸልተኞቹ ምን ይላሉ?
በዚህ ጉዳይ ቸልተኛ የሚባሉት የተለየ ምክንያት ያላቸው፣ ነገር ግን “ጦርነት አያዋጣም” በሚል በገሃድ የሚከራከሩ ወገኖች ናቸው። እነዚህ ውስን የብአዴንና የህወሃት ቁልፍ ሰዎች በትግራይ ድንበር አካባቢ አስተዳደር የሚሰሩትን ጨምሮ የኤርትራ ደም አላቸው። በደህንነትና በጸጥታ ክፍሉ አጠቃላይ መዋቀር ላይ ቁልፍ ቦታ ተጎናጽፈዋል። የመረጃ ምንጮቹ ማብራሪያ እንደሚያመለክተው እነዚህ ወገኖች “ኢሳያስን የክፉ ቀን መጠባበቂያ” ነው የሚሏቸው። ሰዎቹ ኢህአዴግ ላይ አንዳችም አይነት ስጋት እንደማይሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ዋና ዓላማቸው “ከመሃል አገር ወይም ከመካከል ለውጥ ካልተነሳ አርፈህ ተቀመጥ” የሚል ዓይነት መንገድ የሚከተሉ ናቸው።