Friday, August 2, 2013

ዜና በጨዋታ፤ ኢትዮጵያ 2ኛ ወጣች… በሩጫ አይደለም!


Ethiopia_shaded_relief_map_1999,_CIAዜና በጨዋታ፤ ኢትዮጵያ 2ኛ ወጣች… በሩጫ አይደለም!
ሀገራችን ኢትዮጵያ በአፍሪካ ፈጣን እድገት እያስመዘገቡ ካሉ ሀገራት ተርታ መሆኗ ይታወቃል፡፡ ከአፍሪካ ብቻ ደግሞ እንዳይመስለን ከአለምም ፈጣን እድገት እስመዘገቡ ካሉ ግንባር ቀደሞቹ ውስጥ ናት፡፡ ከዚህ አርፍተ ነገር ጋር ልንጋጭ ነው… ልንጋጭ ነው…. ቀበትዎትን ያጥብቁ ራስዎን ያዘጋጁ….
ኢትዮጵያ በምድር ላይ ካሉ ደሀ ሀገሮች ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ ዩናትድ ኔሽን ባወጣው አመታዊ ሪፖርት በ Multidimensional Poverty Index የፈጀውን ይፍጅ ብለን በአማርኛ ብንተረጉመው፤ በዙሪያገባው ድህነት ሰንጠረዥ… ኢትዮጵያችን ሁለተኛ ወጥታልናለች፡፡
በዚህ ዝርዝር ውስጥ የሚገኙት ሀገሮች በሙሉ አፍሪካዊ ሀገሮች ሲሆኑ ሱማሌ እንኳ ከአቅሟ ስድስተኛ ሆና፤ ባለ ፈጣን እድገቷ ኢትዮጵያ እንደ አትሌቲክስ ሩጫው ሁሉ በድህነት ሩጫም የሚደርስባት ሳይገኝ ሁለተኛ መውጣቷ የሃያ ሁለት አመት ልፋታችን ውጤት ነው ሲሉ አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የለመኑን ባለስልጣን ጠቅሰዋል፡፡
ወሬው የተገኘው ዘ አፍሪካን ኢኮኖሚስት ከተባለ ድረ ገጽ ነው፡፡
ቆይማ እንደውም ከአንድ እስከ አስር ያለውን ዝርዝራቸውን ኮፒ ፔስት ላድርግልዎ…
  1. Niger
  2. Ethiopia
  3. Mali
  4. Burkina Faso
  5. Burundi
  6. Somalia
  7. Central African Republic
  8. Liberia
  9. Guinea
  10. Sierra Leone
ከዚህ በፊት ከአለም ጠቅላይ ሚኒስተሮች ሶስተኛው ሃብታም እርሳቸው መሆናቸውን፣ እንዲሁም በቅርቡ ከአለም ጠቅላይ ሚኒስትር ሴት ልጆች ደግሞ የእርሳቸው ልጅ አንደኛ ሳትሆን እንደማትቀር መዘገባችን እና መጠርጠራችን ይታወቃል፡፡
አሁንም እንላለን፤ እንኳንም ሁላችንም ተያይዘን ደሃ አልሆንን፡፡ የሀብታም ሀገራት ባልስልጣኖች ልብ ካላቸው፤ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እስመዘገቡ ካሉት ባለስልጣኖቻችን እና ከልጆቻቸው ጋር ጋር ይፎካከሩ!

No comments:

Post a Comment