Saturday, September 28, 2013

ሀገር ማለት


(ሠዓሊ አምሣሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

faces-of-ethiopia


በዚህ ርእሰ ጉዳይ ላይ አስቀድሞ ደራሲ በዓሉ ግርማ በኋላም ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ ግጥሞቻቸውን ጽፈው ነበር፡፡ ሌላም የጻፈ ይኖራል፡፡ ነገር ግን እነኝህ የሥነ-ጽሑፍ ሰዎች ግጥሞቻቸውን ሲጽፉ የተቆነጸለ ወይም የተሳሳተ ትርጉም ሊያሰጥ በማያስችል ሁኔታ ግጥሞቻቸውን ባለመጻፋቸው እንደምገምተው እነሱም ሊሉ ባልፈለጉት መንገድ ተተርጉሞ የቅጥረኞች መጠቀሚያ እስከመሆን ድረስ በቃና ሕዝብን ለማደናገሪያ አገለገለ፡፡ ከሕዝቡ ጥቂት የማይባል ወገንም በመወናበድ ይሄንን የተሳሳተ ትርጉም ይዞ ማንጸባረቅ ያዘ፡፡  ይህም መሆኑ ሀገር በሕዝብ ልብ ውስጥ የነበራት ቦታና ትርጉም ከመዛባቱም ባሻገር በወደፊት የሀገር ህልውና ላይ ከባድ አደጋ የጋረጠ  ሆኖ ቁጭ አለ፡፡ እናም እንደዜጋ አሳሰበኝና ይሄንን የተሳሳተ ትርጉም ለማረም የሀገርን ትርጉም ሳይቆነጸል ሳይጎነጠል ለማስፈር ተገደድኩና ይህችን ግጥም ጻፍኩ፡፡  ግጥሙ እንዳልኩት የሀገርን ምንነትና ሙሉ ትርጉም ለማስቀመጥ ሲባልና ሁሉም ሰው ሊገባው ሊረዳው በሚችል አገላለጽ ሲገለጽ ትንሽ ሊረዝም ችሏል፡፡ ለዚህ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ በግጥሙ ላይ የተገለጹትን ተግሳጾችንና ስድቦችን ሁሉንም በግጥሙ ላይ ከተወከለው ገጸ ባሕርይ ተውሻለሁ ለራሱ ለባለቤቱ መመለስ ይኖሩባቸዋልና፡፡

የልማት መጀመሪያው ሰብዓዊ መብትን ማክበር ነው!


ሞረሽ ወገኔ (ብሪታኒያ) የተሰጠ መግለጫ

Moresh


የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ::

Friday, September 27, 2013

ስበር ዜና – አንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ታሰሩ!

September 27, 2013


የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ዛሬም ታግተው ወደ አራዳ ፓሊስ ጣቢያ ተወስደዋል፡፡ አብረዋቸው የታሰዩት አመራሮችና አባላት እንደሚከተለው 
እንዘረዝራለን !
Millions of voices for freedom - UDJ
በፖለስ የታሰሩ አመራሮችና አባላት በከፊል
ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ – የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር
የተከበሩ ግርማ ሰይፉ – የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር
አቶ ስዩም መንገሻ – የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ
አቶ ዳንኤል ተፈራ – የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
አቶ አስራት ጣሴ – ዋና ጸሃፊ
አቶ ተክሌ በቀለ – የፋይናንስ ጉዳይ ኃላፊ
አቶ ሽመልስ ሃብቴ – የማህበራዊ ጉዳይ ኃላፊ
አቶ ሃብታሙ አያሌው – የህዝብ ግንኙነት ም/ኃላፊ
አቶ ብሩ በርመጂ – የብሔራዊ ምክር ቤት አባል
አቶ አበበ አካሉ – የብሔራዊ ምክር ቤት አባል
አቶ እንግዳ ወ/ፃዲቅ – የብሔራዊ ምክር ቤት አባል
አቶ አለባቸው ነጋሽ – አባል
አቶ መካንንት ብርሃኑ – አባል
አቶ እንዳልካቸው ባዩ – አባል
አቶ ብስራት ተሰማ – አባል
አቶ ወንደሰን ክንፉ – አባል
አቶ ኃይሉ ግዛው – አባል
አቶ ደረጀ ጣሰው – አባል
አቶ ገዛህኝ – አባል
አቶ ባዩ ተስፋዬ – አባል
አቶ ወርቁ – አባል

Thursday, September 26, 2013

ሰማያዊ ፓርቲ ሕገ-መንግስት አረቀቀ

‘‘የአሁኑ ሕገ-መንግስት የኢህአዴግ ፕሮግራም ቅጂ ነው’’ ኢንጂነር ይልቃል

semayawi 12


በቅርቡ የተመሰረተው የሰማያዊ ፓርቲ ‘‘የዜጎች የቃል ኪዳን ሰነድ ለዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ’’ በሚል መርህ ወደፊት የፖለቲካ ሥልጣን ሲይዝ የሚመራበትን አዲስ ህገመንግስት ማርቀቁን አስታወቀ። ረቂቅ ሰነዱ ላይ ምሁራንና ባለሙያዎች ውይይት ካደረጉ በኋላ ለሕዝብ እንደሚቀርብ ፓርቲው አስታውቋል።
የፓርቲው ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት በአዲሱ ረቂቅ ሕገ-መንግስት ላይ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ውይይት እንደሚደረግ አስታውቀዋል። በውይይቱ ላይ ከዚህ በፊት የነበሩ ሦስት ህገ-መንግስቶች ድክመትና ጥንካሬ ምንድን ነው? አዲስ በሚረቀቀው ህገ-መንግስት ምሰሶዎች ምን ይሆናሉ፣ ስልጣንና ሕዝብን እንዴት ማገናኘት ይቻላል በሚሉ ወሳኝ ንድፈ ኀሳቦች ላይ የጠለቀ ውይይት እንደሚደረግ አስታውቀዋል።
‘‘የአሁኑ ሕገ-መንግስት የኢህአዴግ ፕሮግራም ቅጂ ነው’’ ያሉት ኢንጂነር ይልቃል እያረቀቁ ያሉት ሕገመንግሥት የሰነድ ዝግጅቱም ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁንና ምሁራን በሚያደርጉት ውይይት ከዳበረ በኋላ ለሕዝቡ ውይይት ቀርቦ ለባለሙያዎች ተመርቶ ዝርዝር ህጎች እንዲፃፉ ይደረጋል ብለዋል።
ፓርቲው ሰላማዊ ሰልፍ የሚያካሂደው ሕዝቡን ለማነቃቃትና ለማስተማር አባላትንም ለመመልመል ቢሆንም በተጓዳኝ ፓርቲውን ለማጠናከርና ምን አይነት ስርዓት እንገነባለን የሚለውንም ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም ኢንጂነር ይልቃል ገልፀዋል።
ሰማያዊ ፓርቲ ሕገ-መንግስት ባለበት ሀገር ሌላ ሕገ-መንግስት ከማውጣት የሚያግደው ነገር እንደሌለ የጠቀሱት ኢንጂነር ይልቃል፤ ፓርቲው እያካሄደ ያለው ትግል በሕገ-መንግስት የማይመራን አገዛዝ በዲሞክራሲያዊ ስርዓት የመተካት ስለሆነ አዲስ ህገ-መንግስት ማስፈለጉ የግድ ነው ብለዋል።
የፓርቲው ዋና አላማ በሀገሪቱ ሕጋዊ ስርዓትን መትከል በመሆኑ አሁኑ ባለው ሕግ-መንግስት በሚደረግ ምርጫ አብላጫ ወንበር ማግኘቱን ሲያረጋግጥ አዲሱን ሕገ-መንግስት ተግባራዊ ያደርጋል ብለዋል። በዚህ ሀገር ምርጫ ከተካሄደም ሰማያዊ ፓርቲ 99.6 በመቶ አብላጫ ወንበር ለማግኘት የሚያግደው ነገር እንደሌለም እርግጠኞች ነን ሲሉ አያይዘው ገልፀዋል።

“ወሲባዊ ጂሃድ (ጂሃድ አል-ኒቃ)” በሶሪያ!


ሳዑዲ ሞት የፈረደችባቸውን ወደ ሶሪያ አዝምታለች

tunisian girls


የቱኒዚያ ሴቶችና ልጃገረዶች በሶሪያ የአሳድን መንግሥት እየተፋለሙ ከሚገኙት እስላማዊ አማጺያን ጋር “ወሲባዊ ጂሃድ” በመፈጸም በጦርነቱ ላይ ተሳትፏቸውን እየገለጹ መሆናቸው ተነገረ፡፡ በሌላ በኩል በዚሁ ጦርነት ላይ በሳውዲ አረቢያ የሞት ፍርድ የተበየነባቸው ወንጀለኞች እንዲሳተፉ እየተላኩ መሆናቸው ተረጋገጠ፡፡
በያዝነው የመስከረም ወር መጀመሪያ አካባቢ የቱኒዚያው የአገር ውስጥ ሚኒስትር ሎትፊ ቢን ጄዱ በአገሪቱ ፓርላማ ፊት ቀርበው እንደተናገሩት በጦርነቱ ከፍተኛ መስዋዕትነት እየከፈሉ ለሚገኙት ተዋጊዎች ማደፋፈሪያ እንዲሆንና በትግሉ የነርሱንም ድርሻ ለመወጣት የቱኒዚያ ሴቶችና ልጃገረዶች ራሳቸውን በ“ወሲባዊ ጂሃድ” በመስጠት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትር ሎትፊ ቢን ጄዱ (ፎቶ: አልጃዚራ)
ሚኒስትር ሎትፊ ቢን ጄዱ (ፎቶ: አልጃዚራ)
በአረቡ ዓለም በሚገኙ የዜና ማሰራጫዎች በሰፊው የተዘገበው ይህ ዜና እንደሚያስረዳው ሚኒስትሩ ጉዳዩ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ጠቁመዋል፡፡ “እነዚህ ሴቶች” አሉ ሚኒስትር ቢን ጄዱ “እነዚህ ሴቶች (ሶሪያ በሚቆዩበት ጊዜ) ከ20፣ 30፣ 100” አማጺያን ጋር በመተኛት የወሲብ “አገልግሎት” ይፈጽማሉ፡፡  “ወሲባዊ ግንኙነቱንም የሚያደርጉት በ“ጂሃድ አል-ኒቃ” (ማለትም ወሲባዊ ቅዱስ ጦርነት) ስም ሲሆን ወደ ቱኒዚያ የሚመለሱትም እርጉዝ ሆነው ነው” በማለት ሚኒስትሩ ለተከበሩት የፓርላማው አባላት በግልጽ አብራርተዋል፡፡
ከጂሃዲስቶቹ ልጅ አርግዘው የሚመጡት ሴቶች ቁጥር ምን ያህል እንደሆነ ሚኒስትሩ አልጠቆሙም፡፡ ሆኖም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሴቶች በጉዳዩ ላይ እንደሚሳተፉ ከዚህም በተጨማሪ ከ3ሺህ በላይ ቱኒዚያውያን የአማጺያኑን ኃይል ለመደገፍ እንደዘመቱ ይነገራል፡፡ ይህ የቱኒዚያውያኑ ቁጥር በአሳድ ላይ ጂሃድ በማወጅ የሶሪያን አማጺዎች ከተቀላቀሉት የሌላ አገር ዜጎች ከፍተኛውን ቁጥር የያዘ ነው፡፡
ሚኒስትሩ እንደሚሉት ከሆነ እርሳቸው ሥልጣን ከያዙ ካለፈው ዓመት መጋቢት ወር ጀምሮ “ስድስት ሺህ ያህል ወጣቶች በሶሪያ የእርስበርስ ጦርነት እንዳይሳተፉ ለመከልከል” መቻሉን ለፓርላማው አስረድተዋል፡፡ አል አረቢያ ሚኒስትሩን ጠቅሶ እንደዘገበው የቱኒዚያን ድንበር በማቋረጥ ወደ ሶሪያ ለመዝመት የሚፈልጉ ወጣቶችን ለመከላከል በቱኒዚያ የድንበር ቁጥጥር መጠናከሩን ገልጾዋል፡፡ በተጨማሪም በዚህ ድንበር በማሻገር ተግባር ላይ የተሰማሩ 86 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አል አረቢያ ጨምሮ ዘግቧል፡፡

ደጃች ውቤ ሠፈር ሊፈርስ ነው


ቅርስም ሆነ ሌላ ነገር ከባቡር ተርሚናሉ ጋር የሚገናኝ ከሆነ (ይፈርሳል)-የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር

wubie bereha


“በቅርስነት ሊጠበቅ ሲገባው በድንገት ሊፈርስ ነው መባላችን አሳዝኖናል” የአካባቢው ነዋሪዎች

ከአዲስ አበባ ከተማ ምሥረታ ጋር ተያይዞ በቀደምትነት ከተመሠረቱ አካባቢዎች ቀዳሚነቱ የሚነገርለትና በተለምዶ “ውቤ በረሃ” በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ደጃች ውቤ ሠፈር፣ በከፊል የሚፈርስ መሆኑ ለነዋሪዎች ተነገራቸው፡፡
በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ አምስት ንዑስ ቀበሌ 05 ከጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት ወደ አፍንጮ በር በሚወስደው መንገድ በቀኝ በኩል በ11.6 ሔክታር ቦታ ላይ ያሉ ነዋሪዎች እንደሚነሱና ከ100 ዓመታት በላይ ያስቆጠረው ሠፈር እንደሚፈርስ ለነዋሪዎቹ የተነገራቸው፣ መስከረም 11 ቀን 2006 ዓ.ም. በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ለግማሽ ቀን በተደረገ ውይይት ነው፡፡
ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በስተቀኝ በኩል በሚያስወጣው አስፓልት እስከ አደባባዩ ድረስ የተገነቡ የመኖሪያ ቤቶች፣ የንግድ ቤቶችና የተለያዩ ቢሮዎች፣ ሆቴሎችና ምግብ ቤቶችን ጨምሮ እስከ አፍንጮ በር ድልድይ መዳረሻ ድረስ እንዲፈርሱ ምክንያት የሆነው፣ የባቡር ተርሚናልና ኃይል መስጫ ጣቢያ ሊገነባበት በመሆኑ እንደሆነ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት በተደረገው የግማሽ ቀን ስብሰባ እንደተነገራቸው ነዋሪዎቹ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
ነዋሪዎቹ እንደገለጹት፣ በጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አደባባይ ፊት ለፊት ከሚገኙት ንግድ ቤቶች ጀምሮ ከሦስት ሔክታር በማይበልጥ ቦታ ላይ ያሉ ነዋሪዎች እንደሚነሱ ቀድመው ተነግሯቸዋል፡፡ መስከረም 11 ቀን አስቸኳይና ድንገተኛ ስብሰባ እንዳለና ማንም ቢቀር ኃላፊነቱ የራሱ እንደሆነ በማስጠንቀቅ ነዋሪዎች እንዲገኙ ከተደረገ በኋላ፣ በሰሙት ጉዳይ እጅግ በጣም መደንገጣቸውንና ማዘናቸውን አስረድተዋል፡፡
የባቡር ተርሚናልና ኃይል መስጫ ጣቢያ ግንባታ በሚል በዳር ያሉት እንደሚነሱ በቅድሚያ ከተነገራቸው በኋላ በድንገት “የሚያስፈልገው ስምንት ሔክታር ነው፡፡ የሚቀረው 3.6 ሔክታር ተቆርጦ መቀጠል ስለሌለበት ለመልሶ ማልማት መፍረስ አለበት፡፡ ይኼ ደግሞ ተወስኖ አብቅቷል” መባላቸው ተገቢ አለመሆኑንና ኅብረተሰቡን መናቅ እንደሆነ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

Wednesday, September 25, 2013

ከለውጡ በኋላስ? (ጋዜጠኛ ተመሰገን ደሳለኝ )


September 24, 2013

ኢህአዴግ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ (በውስጥም በውጪም ተግዳሮቶች) መገፋቱን በሚያመላክቱ የፖለቲካ አጀንዳዎች ላይ የሚያጠነጥን አንድ ፅሁፍ (‹የአብዮቱ የምፅዓት ቀን ምልክቶች›› በሚል ርዕስ) አቅርቤ እንደነበር ይታወሳል፤ ይዘቱም በመጪዎቹ ወራት ወይም ዓመት ስርዓቱ ‹ምርጫ› አሊያም ‹ህዝባዊ› እምቢተኝነት ከሚያመጣው ‹ማዕበል› (እንደበረከት ስምዖን አገላለፅ ‹ናዳን በሚገታ ሩጫ›) የማምለጥ ዕድሉ የጠበበ መሆኑን የሚያመላክት ነው፤ ይሁንና አንድ አብዮት ታላቅ (ውጤታማ) ሊባል የሚችለው አምባገነን ስርዓትን በመቀየሩ ብቻ ስላልሆነ (ሥር-ነቀል ለውጥ የሚፈጥር አብዮት ዋጋ የሚኖረው የዲሞክራሲ ተቋማትን መሰረት መጣል ሲችል ነውና) በቀጣይ መፃኢ ዕድሉ ላይ መነጋገሩ አስፈላጊ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡
Journalist Temasegan Dasaleg
በዚህ ፅሁፍህ ተጠየቅም ‹ከስርዓቱ ለውጥ በኋላ፣ ማን ነው አማራጩ?› የሚለው ጥያቄ ትኩረት ይደረግበት ዘንድ አመላክታለሁ፡፡
ምክንያቱም በጠለፉ መንገድ ከቀሩ አብዮቶች ታሪክ ተምረን፣ ‹መጥነን ካልደቆስን› የሚከፈለውን ዋጋ በብላሽ የሚያስቀር አሳዛኝ ሁናቴ ሊፈጠር ይችላልና (ቭላድሚር ኤሊች ሌኒን ‹‹አብዮት፣ ለአብዮት ብቻ ሲባል መካሄድ የለበትም›› እንዲል፣ ከኢህአዴግ መገላገሉ መልካም ቢሆንም፣ የአገላጋዩን ማቀፊያ ከወዲሁ መምረጡ ወይም የምንጠይቀውን ማወቁ ብልህነት ነው)

አማራጩ ተወልዷልን?
ከኢህአዴግ በኋላ የሚተካው አማራጭ ተዘጋጅቷል? …ይህንን ቀዳዳ አስቀድሞ መድፈኑን አስቸኳይ ያደረገው፣ ለውጡ የሚመጣበት መንገድ ‹ከህዝባዊ እምቢተኝነት› ይሆናል የሚለው ቅደመ-ግምት ነው፡፡ ከታዓማኒና በዕኩል አሳታፊ ምርጫ የሚነሳ ሽግግር (‹ሕዝብ የሚፈልገውን ያውቃልና ውሳኔው መከበር አለበት› ከሚለው የዲሞክራሲ ፅንሰ-ሃሳብ በመነሳት) አሳሳቢነቱ ከአደባባይ ተቃውሞ የሚመነጨውን ያህል አይደለም፤ ስለዚህም ከስጋት ነፃ መሆን የሚቻለው በሰላማዊ መንገድ ለመታገል መሰረታቸውን ሀገር ቤት አድርገው በህግ የተመዘገቡ የፖለቲካ ድርጅቶች የቤት ስራቸውን ሰርተው ዝግጁ ሆነው ሲጠብቁ ብቻ ነው፡፡ ይህ ግን የድርጅቶቹን ቁጥር ከሰማኒያ በላይ ከማሻቀብ ያለፈ አስተዋፅኦ የሌላቸውን አሰስ-ገሰስ ‹ፓርቲ›ዎች በሙሉ እንደሚመለከት ተደርጎ መወሰድ የለበትም፡፡
ነፍስ ይማርና በ‹‹ልዕልና ጋዜጣ›› እልፍ አእላፍ ችግሮቹን ማረም ከቻለ መድረክ ተስፋ ሊጣልበት ይችላል ብዬ እንደማስብ መፃፌን አስታውሳለሁ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የመድረክ አሰላለፍ ሊቀየር በማጋደሉ (ከአንድነት ጋ አብሮ መቀጠሉ ማጠራጠሩ) እና ሰማያዊ ፓርቲ አዎንታዊ እንቅስቃሴ ከማድረጉ አኳያ ተፎካካሪ ሊሆን የሚችልበት ዕድል በመፍጠሩ፣ በአጀንዳው ላይ ማካትቱን ተገቢ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ ይሁንና ሌሎች ፓርቲዎችን እዚህ ጋ ያላነሳሁበት፣ ከላይ ከጠቀስኩት በተጨማሪ ሶስት ምክንያቶች አሉኝ፤ ቅቡልነትን ማጣት፣ እንቅስቃሴ አልባ መሆን እና በገዥው ፓርቲ ስፖንሰርነት መተንፈስ የሚሉ፡፡