Sunday, February 9, 2014

የአፍሪካ 100 ምርጥ ዩኒቨርሲቲዎች


አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ - 53ኛ!!

aa university
በዓለማችን የሚገኙ የትምህርት ተቋማትን በማወዳደር ደረጃ የሚያወጣው (4 International Colleges & Universities (4icu)) የአፍሪካ ምርጥ የተባሉትን ዩኒቨርሲቲዎችን ዝርዝር ከጥቂት ሳምንታት በፊት አውጥቶ ነበር፡፡ ድርጅቱ በርካታ መረጃዎችን በመሰብሰብ እንዲሁም ለማንም ወገን ያላዳላ ጠለቅ ያለ ሒሳባዊ ትንታኔ በማድረግ ደረጃውን እንደሚያወጣ በድረገጹ ላይ ጠቁሟል፡፡
ከአንድ እስከ ሃያ ባሉት ዝርዝር ውስጥ የደቡብ አፍሪካና የግብጽ ዩኒቨርሲቲዎች ደረጃውን በብዛት ተቀራምተውታል፡፡ ታንዛኒያ፣ ናይጄሪያ፣ ዩጋንዳ፣ ቦትስዋና እና ኬኒያ እስከ ሃያ ባለው ደረጃ በመግባት የአገራቸውን የትምህርት ተቋማት ብቃት አስመስክረዋል፡፡
ከተመሠረተ 60ዓመታት ያለፉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (በቀድሞ ስሙ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ) እስከ መቶ ባሉት ዝርዝር ውስጥ የ53ኛ “ክብር” ተጎናጽፎዋል፡፡ ከተመሠረቱ ጥቂት ዓመታት በሆናቸው ዩኒቨርሲቲዎች ተበልጦ ለዚህ የበቃው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቀደምት ዓመታት የበርካታ አፍሪካውያን ኩራት ነበር፡፡
ህወሃት/ኢህአዴግ ሎሌዎቹን ከየቦታው ሰብስቦ ሥልጣን በያዘ ማግስት መጀመሪያ የወሰደው እርምጃ ኢትዮጵያ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ያስተማረቻቸውን 42 ምሁራን በሁለት መስመር ደብዳቤ ማባረር ነበር፡፡ በአቶ መለስ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ዶ/ር ዱሪ መሐመድ ያባረሯቸው እነዚህ ምርጥ ምሁራን እንደ ምሁርነታቸው በነጻ በማሰባቸውና ተማሪዎችንም እንደዚያው እንዲያስቡ በማድረጋቸው እንጂ በደብዳቤው ላይ እንደተገለጸው ተፈላጊ ባለመሆናቸው እንዳልነበር የታወቀ ነው፡፡
ኢህአዴግ ሥልጣን ከያዘ በየቦታው የፈለፈላቸው የካድሬ ማምረቻ “ዩኒቨርሲቲዎች” ስሙን ከመያዝ በስተቀር እስከ 100 ባሉት ዝርዝር አንዳቸውም ለመገኘት አለመብቃታቸው የኢትዮጵያን የትምህርት ጥራት ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ የሚያሳይ ነው፡፡

ወያኔ: የነፃው ፕሬስ ፀር!


(ቅዱስ ዮሃንስ)

censorship
ነፃ- ፕሬስ ለነፃነት፤ ለፍትህና ለእኩልነት የሚኖረውን አስተዋፅኦ የሚገነዘቡ ገዢዎች ፕሬሱ ለአንባገነንነት አገዛዛቸው የሚመች ስለማይሆን ይፈሩታል፤ ይጠሉታል፤ ያጠፉታል። ወያኔም እያደረገ ያለው ይህንኑ ነው።
ነፃ ፕሬስ የሀሳብ ነፃነት መብት አልፋና ኦሜጋው ነው ብል ማጋነን አይሆንም። የነፃ ፕሬስ መኖር የሚያረጋግጠው ጋዜጠኞች ያለምንም ጭንቀትና ፍርሃት የሚያስቡትን፡ የሚሰማቸውን፡ የሚሰሙትን እንዲሁም ምርምር አድርገው የደረሱበትን ዜናዎች በነፃ ለመፃፍና ለማሰራጨት ብሎም ሕዝብ እንዲወያይበት ለማድረግ ያላቸው ያልተገደበ መብት ነው። ይህም ጤናማ ሕብረተሰብ ለመፍጠር ብቻ ሳይሆን ለእድገቶቹም ጉልህ ድርሻ አለው።  ነፃ ፕሬስ የኃሳብ ነፃነት ተግባራዊ ለመሆኑ ዋስትናም መፈተኛም ነው። ኃሳብን ያለምንም ጭንቀትና ፍርሃት በነፃ ለመግለፅ መቻልና መለዋወጥ እንደ ምግብና መጠጥ፤ ሁሉ ሰብአዊ ክቡርነትን የተላበሰ ሕይወት ለመጎናፀፍም አስፈላጊም ናቸው። ሃሳብን በነፃ የመግለፅ መብት መኖርና ዋስታናው ዴሞክራሲያዊ በሆነ ሕግ መረጋገጥ ማለት ዘላቂነት ላለው ዴሞክራሲያዊ እድገት ለማገኘትም ዋና መሰረት ነው።
የተሳካ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት የነፃ ፕሬስ አስፈላጊነት ትልቅ ቦታ እንዳለው ከልብ ይታመናል፡፡ ያለነፃ ፕሬስ ዴሞክራሲ አለ ብሎ መናገር ማወናበድ እንጅ እውነት ሊሆንም አይችልም፡፡  የነፃ ፕሬስ መኖር በራሱ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት መኖር መገለጫ ነውና፡፡ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ሲኖርም ነፃ ፕሬስ ይኖራል፡፡ ወደ እኛ ሃገር ስመለስ ግን ነገሮች ሁሉ የተገላቢጦሽ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ ወያኔ መንግስት ሆኖ ላለፉት 23 ዓመታት ሃገሪቱን ሲያስተዳድር ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን በወረቀትና በቃል እንጂ ከዚያ በዘለለ በተግባር ሲፈፅም አላሳየንም፡፡ ለመተግበር የሞከራቸውንም እንደ ቀንዳውጣ ቀንድ መልሶ ሸሽጎታል፡፡ ስለዚህ በዴሞክራሲያዊ ስርዓት የማያምን አምባገነን ስርአት ስለሆነ ለነፃው ፕሬስ ፀር በመሆን ተገቢውን ጥበቃና እንክብካቤ በመስጠት ፋንታ አጥፊና ደምጣጭ ሆኖ እየሰራ ይገኛል።

Monday, February 3, 2014

ዳር ሆነው የሚመለከቱት የጎሳ ፖለቲካ ምሱ “ደም”!!


(ርዕሰ አንቀጽ)

image1
“ህወሃት” የሚባለው የትግራይ ነጻ አውጪ ትግራይን መቼና ከማን ነጻ እንደሚያወጣ በውል የተቆረጠ ቀን ባይኖርም ህገ መንግስታዊ ዋስትና ግን አለው በሚል እየተተቸ 23 ዓመታትን አስቆጥሯል። አገር እየመራም ነጻ አውጪ፣ በረሃም እያለ ነጻ አውጪ፣ በአህጉርና በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲወከልም ነጻ አውጪ!!
ይህንን የተለመደና ግራ የሚያጋባ እውነት ያነሳነው ወደን አይደለም። ይህ የህወሃት ግልጽ መለያና ከመለያው የሚነሳው ትንታኔ ለማንም የተወሳሰበ ይሆናል ብለንም አንገምትም። ኢህአዴግ የሚባለው የ”ሎሌዎች” ስብስብ ያበጀውና የሚመራው ህወሃት ከሌሎቹ በተለየ በነጻ አውጪ ስም 23 ዓመት አገር ሲገዛ ሌሎቹ “የነጻ አውጪ” ስም አለመያዛቸው ግን ሁሌም ሊመረመር የሚገባው ጉዳይ ይመስለናል።
አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ “ነጻ” መውጣት ያለባቸው ህወሃቶች ሳይሆኑ ሌሎች የአገራችን ህዝቦች፣ የትግራይን ንጹሃንን ጨምሮ ነው። ህወሃት ሲጠነሰስ ጀምሮ የነበሩትን ቀደምት አመራሮች በሂደት እየበላ አራት ኪሎ የደረሰው፤ ህወሃት መጥበብ የጀመረው ገና ከጥንስሱ ጊዜ ጀምሮ ነው። ስለ ህዋሃት የሚወጡ የምስክሮች ሪፖርቶችና መረጃዎች እንደሚያረጋግጡት ህወሃት በደም የታጠበ፣ በደም የተለወሰ፣ የበርካታ ንጹሃን ደም ያጨማለቀው፣ ታሪኩ ሁሉ በደም ዙሪያ የተሰራ፣ አሁንም ከዚሁ የደም ቁማር ነጻ መሆን ያልቻለ መሆኑን ነው።

Tuesday, January 21, 2014

ርዕዮት አለሙ ጋዜጠኛ እንጅ አሸባሪ ናት ብየ አላምንም!


(ነቢዩ ሲራክ)

reeyot
የጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙን ስራዎች በቅርብ ተከታትያለሁ! ውንጀላ እስራቷን ፣ ህክምና እንድታገኝ መደረጓን እና የቤተሰብ እና የወዳጆችዋ ጉብኝት እንዳታገኝ መከልከሏን ሰምቻለሁ ! ይህ ሁሉ በዚህች የመናገር የመጻፍ ነጻነቷን ተጠቅማ ህገ መንግስታዊ መብቷን በተጠቀመች ወጣት ጋዜጠኛ ላይ የሚከፈል መስዋዕትነት ቢሆንም ስቃይ መከራዋ ፣ በደል መገፋቷ ያንገበግበኛል!እናም እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ተተገፈፈቸው መብቷ ይመለስ ዘንድ በሚደረገው ሰላማዊ እንቅስቃሴ ደጋፊ ነኝ ! ርዕዮት አሸባሪ አይደለችም ብየ አምናለሁና ፊርማየን ለድጋፍ ሳስቀምጥ ኩራት ይሰማኛል !
ፍትህ ለጋዜጠኛ ርዕዮትና ለመሰሎቿ ስመኝ ለኢትዮጵያስ እንኳንም ተወለድሽ የምላት አሁንም በኩራት ነው! ግጥሙን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ::

Monday, January 20, 2014

“ወደው አይስቁ”


"ሉሲ ኦሮሞ ናት። ጎንደርም ከኦሮሞ ላይ የተቀማች ሃገር እንደሆነች ጥናት አድርገን ጨርሰናል"

foreign
የጥምቀት በዓልን ተሰባስበን በምናከብርበት አንድ ቤት ውስጥ ካለወትሮው ፓልቶክ ተከፍቷል። በዚያ የበዓል ድባብ፤ የፓልቶክ ንትርክ መከፈቱ ሳይገርመን፣ ርእሱ የሁላችንንም ቀልብ መሳቡ። በእርግጥ አንድም ቁም ነገር በንግግሩ አልሰማንም። አዲሱን ቋንቋ ልዋስና የፓልቶኩ ተናጋሪዎች ሙድ  የሚያስይዙ ነበሩ። ሰዎቹ በዚህ ከቀጠሉ የእነ ክበበው ገዳን ገበያ መዝጋት እንደሚችሉ አያጠራጥርም።
የድምጽ መነጋገርያውን የያዘው ሰው ጉሮሮውን ጠራርጎ ንግግሩን እንዲህ ሲል ጀመረ።  “የምኒሊክ ወንጀል በጡት መቁረጥ ብቻ አያበቃም። …  የወንዶች ብልትም ተቆርጧል።…”
በአኖሌ ሃውልት የምትገረሙ ነፍጠኞች ካላችሁ። በዚህ ብዙም አትደነቁ። ገና የወንድ ልጅ ሃፍረተ-ስጋ በሃውልት መልክ በአደባባይ ይቆምላችኋል። “የባሰ አታምጣ!” ነው ነገሩ። ሜንጫዎቹ ሰክረዋል። አእምሮዋቸውም ስቷል።  የሚናገሩትን አያውቁትም። የማየውቁትን ነገር ሁሉ ይናገራሉ። እነሱ የሚናገሩትን ደግሞ በምኒሊክ ቤተ-መንግስት ያሉ ሰዎቻቸው በተግባር ይፈጽሙላቸዋል።
anole3ተናጋሪው የእለቱ የክብር እንግዳ መሆኑ ነው። በጉዳዩ ላይ ብዙ ጥናት እንዳደረገም አስቀድሞ ገለጻ ተደርጓል። ሰዎቹ የወንዶች ብልት መቆረጥን የፈጠራ ታሪክ ያነሱት ያለምክንያት እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ጡትን በአደባባይ ያቆሙ እብዶች፣  የወንድ ብልትን አያቆሙም ማለት አንችልም። “ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም!” ይላል የሃገሬ ሰው። ስለ አኖሌ የፈጠራ ውጤት በያዝነው አዲስ አመት አውርተን ሳንጨርስ፤ ይኸው የባሰ ነገር እየመጣ ነው። ምኒሊክ የወንድ ብልትምም ቆርጠዋል ነው እያሉን ያሉት – ጨዋታቸውን ሲያራዝሙት። አጼ ሚኒሊክ ለካ የጉጂ ኦሮሞ ኖረዋል።  ትንሽ ቆይተው ጉጂዎች የወንድ ብልት መቁረጥ የተማሩት ከምኒሊክ ነው ይሉናል።  እዚህ ላይ ሰዎቹ እየቀለዱ ብቻ አይደለም።  እየቀለዱብንም ነው። ወዳጆቼ ግን አሁንም ሙድ ይዘዋል።…
በነዚህ ቀልደኞች ዘና እንል ይሆናል። አንድ የዘነጋነው ነገር አለ።  የሴት ልጅ ጡት በአደባባይ ሃውልት የተሰራለት በእኛ ምድር ላይ ብቻ ነው። ይኸውም በእኛ ዘመን። ሴት ልጅ በሃገራችን ትከበራለች። የውስጥ አካልዋ እንዲህ በአደባባይ ላይ ሲውል ክብርዋን ይቀንሰዋል። የሴትን ልጅ ጡት በአደባባይ ላይ አውለው፤ ህጻናትና አዋቂው እንዲመለከተው ማድረግ በባህላችንም እጅግ ነውር ነገር ነው።
“ምሁሩ” የታሪክ ተንታኝ ንግግሩን በዚህ አላበቃም። ማብራራቱን እንደቀጠለ ነው።  “…ይህንን ታሪክ ለማወቅ የታሪክ መጽሃፍ ማንበብ አይጠበቅባችሁም። በኢንሳይክሎፔዲያ ላይም ግዜያችሁን አታባክኑ። በቀላሉ ጉግል አደርጉና ታገኙታላችሁ… ” አለ። ጉግል ስናደርግ ይህንኑ መረጃ በራሱ ድረ-ገጽ ላይ ልናገኘው እንችል ይሆናል።

Wednesday, January 8, 2014

በጅዳ እና አካባቢው የኢትዮጵያውያን ክራሞት


saudi ethio j
ካሳለፍነው ወር ጀምሮ ወደ ሃገራቸው እንዲገቡ በተደረገው ጥሪ እጃቸውን የሰጡ መኖሪያና የስራ ፈቃድ የነበራቸው ዜጎች ባቀረቡት ቅሬታ “ወደ ሃገር እንዳንገባ ተደርገን እየተጉላላን ነው!” ብለውኛል። በቀን በሚሰጠው ደረቅ ብስኩትና ጥራቱ ባልተጠበቀ ሩዝ መጉዳታቸውን የገለጹልኝ ሲሆን መፍትሔ የሚሰጠን የኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ የሳውዲ መንግስት ተወካዮች አጥተው ቀን በጸሃይ ፣ ማታ በብርድና በቁር እንግልት እንደደረሰባቸው ተናግረዋል። ወደ ሃገር እንግባ ብለው በተደረገው ጥሪ እጃቸውን የሰጡት መኖሪያና የስራ ፈቃድ የነበራቸው ዜጎች እዚህ በጅዳ ሽሜሲ ብቻ ሳይሆን በሪያድ እስር ቤቶች እንዳሉ እንግልት እየደረሰብን ያሉ ነዋሪዎች ምሬታቸውን ገልጸውልኛል።
ሁከት በጅዳ የንጉስ አብድልአዚአዚዝ አውሮፕላን ማረፊያ-
ከጅዳ መካው የሽሜሲ መጠለያ ተነስተው ወደ ሃገር ለመሳፈር  በጅዳ የንጉስ አብድልአዚአዚዝ አየር መንገድ ማረፊያ አውሮፕላን ማረፊያ የደረሱ ቁጥራቸው 1500 በላይ የሆኑ ኢትዮጵያውያን “የያዛችሁት እቃ ከሚፈቀደው ኪሎ በላይ ነው!” በሚል የተፈጠረው አለመግባባት  ማክሰኞ ከቀትር በኋላ መጠነኛ ሁከት ተቀስቅሶ እንደነበር እና ከሰአታት በኋላ መረጋጋቱን ተደጋጋሚ መረጃ ደርሶኛል።  የማክሰኞው ሁከት መነሻ የተመላሾችን የተከማቸ እቃ ለማየት ወደ ቦታው የደረሱትን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሃላፊ በቦታው መድረሳቸውን ተከትሎ ሲሆን በእንግልቱ የተበሳጩት ዜጎች ሁከት መቀስቀሳቸው በአይን እማዘኞች ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ  ለመረዳት ችያለሁ። የአይን እማኞች አክለውም ዜጎች ከሃላፊው ጋር ሊጋጩ ሲሉ በጸጥታ አስከባሪዎች ብርታት መትረፋቸውን ከቦታው  በሰአቱ የደረሰኝ መረጃ ያስረዳል። ግርግሩ ለሰአት ያህል የቀጠለ ቢሆንም በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት አልደረሰም። ሁኔታውን ለማረጋጋት በቦታው የተገኙ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊሶች ማረጋጋት ከፈጠሩ እና ሁኔታው ከተረጋጋ በኋላ የአየር መንገዱን ሃላፊ ለጥያቄ ወስደዋቸው እንደነበርና ሃላፊውን ለማስለቀቅ የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች እና ጅዳ የመጡት የሪያዱ አንባሳደር ወደ ቦታው በመንቀሳቀስ ከሰአታት በኋላ ሃላፊውን ይዘው ምሽት ላይ መመለሳቸውን ተጨባጭ መረጃ ደርሶኛል።

ዋናውን “ሌባ” ማን ይከሰዋል?


አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ የ“ሰው” ንግድ!

ethio human trafficking
ኢህአዴግ ልዩ ምክንያት ከሌለው በስተቀር የውጪ ጠላት አያፈራም የሚሉ በርካታ አስተያየት ሰጪዎች አሉ። ምክንያት ካለው ግን ቅንድቧን አንደተላጨችው ነገረኛ ሴት ለመጋጨት ይፈጥናል። ከፊትለፊቱ ገንዘብ ካየ ደግሞ ኢህአዴግ ገደል ሜዳው ነው የሚሉም አሉ። ገንዘብ በሌለበት ቦታ ኢህአዴግ አይታይም በማለት ከበረሃው ኑሮ ጀምሮ የሚከሱት ጥቂቶች አይደሉም። በቅርቡ በሳዑዲ አረቢያ ምድር በሁለት ምድብ ተከፍለው የሚሰቃዩትን ወገኖች አስመልክቶ የያዘው አቋምም ከዚሁ መርሁ የተቀዳ እንደሆነ የሚከራከሩ በርካታ ናቸው። “ምን ያድርግ የኖረው የአገሪቱ ችግሮች ሁሉ ተቆልለው እሱ ላይ ወደቁ” በማለት ኢህአዴግን ለኢትዮጵያ የተቀመጠ “የተቀባ” መፍትሔ አድርገው የሚያወድሱ አሉ።
ኳስ ሜዳ ያደገችው ኑሪያ መሐመድ አሁን የምትኖረው ኳታር ነው። ኑሮ እንዳሰበችው የተመቻቸ ባይሆንላትም ወደ አገርዋ ለመመለስ አትፈልግም። አታስበውም። “ኢትዮጵያ ምን አለ?” ከማለቷ በቀር ለምክንያቷ ብዙ ማብራሪያ መስጠት አትፈልግም። አገሯ እሷንና መሰል ወገኖቿን ለማኖር አልቻለችም። በኳታር ባይመቻትም የታናናሽ እህቶቿንና የምትወዳቸውን እናቷን ጉሮሮ መሸፈን የሚያስችላትን አቅም አግኝታለች። ይህ ለእርሷ ታላቅ በረከት ነውና ችግሯን በበረከቷ እያዋዛች ትኖራለች። በኳታር በረሃ!!
ኑሪያ ኳታር የሄደችው አሜሪካን ግቢ በሚገኝ አንድ የጉዞ ወኪል ቢሮ ውስጥ ሰዎችን ወደ አረብ አገራት የመላክ ህጋዊ ፈቃድ አለው በተባለ ሰው አማካይነት ነው። የላካትን ሰው በአካል አታውቀውም። ቢሮውንም የረገጠችው የመጓጓዣ ቲኬትና ሰነዶቿን ለመቀበል ብቻ ነው። በወቅቱ እዛው ቢሮ ወደ ሳዑዲ ለመሔድ በዝግጅት ላይ የነበረች እህት ተዋውቃለች። ልጅቷ ከደቡብ ክልል ሆሳዕና ከተማ የመጣች ነበረችና ቤቷ ወስዳ ጋብዛታለች። በዚያው በመሰረቱት ጓደኝነት ከያሉበት ሆነው ይጠያየቁ ነበር። እድሜ ለጊዜና ለስልጣኔ!!