Thursday, November 29, 2012

የእስላም ኢትዮጵያውያን የትግል ስልት

 

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

muslim ethiopians

በአለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ እስላም ኢትዮጵያውያን ማካሄድ የጀመሩት ትግል በዓይነቱም፣ በስፋቱም፣ በአስተሳሰቡም፣ በስሜቱም እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ ውስጥ ከአገዛዙ ጋር ከተደረጉ ትግሎች በጣም የተለየ ነው፤ በመጀመሪያ ደረጃ ትግሉ ለሃይማኖት ነጻነት ነው፤ ስለዚህም በአገዛዙ በኩል የፖሊቲካ ዓላማና የፖሊቲካ መልክ እየተሰጠው ሲሆን በእስልምና ምእመኖቹ በኩል ግን ትግሉን ከፖሊቲካ የጸዳ ለማድረግ ግሩም የሆነና የተሳካ ጥረት እያደረጉ ነው፤ ሁለተኛ የትግሉ ስልት ፍጹም ሰላማዊ በመሆኑ የአገዛዙን የጉልበት ስልት እያከሸፈ ያጋለጠው ይመስላል፤ አንዱና ዋነኛው የትግሉ ሰላማዊነት መግለጫ በቤተ መስጊድ መወሰኑ ነው፤ ይህ ስልት አዲስ አይደለም፤ በብዙ የአረብ አገሮች የሚጠቀሙበት ነው።

Wednesday, November 28, 2012

ሁለተኛው የኢህአዴግ መንግስት

(ከአስራት አብርሃም)
 

እናንተ፣ ያበሻ ሰዎች ተስፋን አትቁረጡ

ከስንት አመት ወዲያ

መልሰው ሊገዙ ንጉስ ጦና መጡ

 
ይህ ግጥም አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው የተሾሙ ጊዜ በፌስቡክ ላይ የተለቀቀ ነው። የገጣሚውን ማንነት ማወቅ ባልችልም ሀሳቡን የገለፀበት መንገድ ግን ሳላደንቅ ማለፍ አልችልም። ግሩም ድንቅ ነው!
በታሪክ እንደሚታወቀው የወላይታ የመጨረሻው ንጉስ ካዎ ጦና ነበሩ። ግዛታቸውን ላለማስነጠቅ አያሌ የመከላከል ጦርነቶች አካሄዷል፤ በኋላ ላይ በአፄ ምኒልክ ጦር ተሸንፈው፣ ግዛታቸውም ለሸዋው ሰፋሪ ጦር አስረክበው ለግዞት ተዳርጓል። ከዚያ በኋላ የወላይታ የሚባል ንጉስ አልነበረም። ለዚህ ነው ገጣሚው "ተስፋ አትቁረጡ" የሚል ስንኝ ያስቋጠረው። ከወላይታ፣ ኢትዮጵያን የሚገዛ መጣ ለማለት ተፈልጎ የተገጠመ ይመስላል። እውነትም ሰውዬ ኢህአዴግ ሆኑ እንጂ ከወላይታ መምጣታቸውስ ደስ የሚል እና ተስፋ የሚሰጥ ነው። ምክንያቱም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ "አቅም እስካለኝ ድረስ የአገሪቱን ከፍተኛ ስልጣን ለመያዝ የሚያግደኝ ነገር አይኖርም" ብሎ እንዲያስብ የሚያደርግ ነውና። ክፋቱ ግን አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ወደዚህ ስልጣን የመጡት በአቅም ብቃት ሳይሆን ለቀድሞው ጠቅላይ ሚንስቴር በነበራቸው ታማኝነት መሆኑ ላይ ነው። ይህን እውነት የሰውየው ነፍስ አባት በየዋህነት ለሪፖርተር ጋዜጣ ሰጥቷል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማስተዳደር ባቃታቸው ጊዜ ለአቶ መለስ ስልክ ደውለው "ኧረ እኔ አልቻልኩም ምን ማድረግ ይሻለኛል?" ብለው ያመለክታሉ።

Tuesday, November 27, 2012

በራስ አሉላ ስም የተሰየመው ት/ቤት በመለስ ተቀየረ

 

ከኢየሩሳሌም አርአያ

በትግራይ ተምቤን – አብዪአዲ የሚገኘውና በጀግናው ራስ አሉላ አባነጋ ስም ተሰይሞ የቆየው የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ስያሜው ተቀይሮ በመለስ ዜናዊ ስም እንዲሰየም መወሰኑን ታማኝ ምንጮች አስታወቁ።

በደርግ ዘመን የተሰራውና በራስ አሉላ ስም ተሰይሞ የ 9 – 10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ሲያስተምር ከቆየ በሑላ ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ የት/ቤቱን አቅም ለማሳደግ በሚል የ11-12ኛ መመሪያ ክፍሎችን ለመገንባት በአገር ውስጥና በውጭ አገራት የሚገኙ የአካባቢው ተወላጆች ገንዘብ አዋጥተው ስራው መከናወኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል። ግንባታው ተጠናቆ ባለፈው ነሃሴ ወር ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ እንዳለ አቶ መለስ በማለፋቸው ፕሮግራሙ መሰረዙን ሲታወቅ; ከሁለት ሳምንት በፊት በተከናወነው የምረቃ ስነ-ስርአት የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት በስፍራው እንደተገኙ ማወቅ ተችሎዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት አርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ልዩ ስሙ ጃንሱማ በተባለው ቦታ ወታደራዊ ጥቃት ፈጸመ

 

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በወያኔ ቅጥረኛና ምንደኛ የልዩ ሃይል ታጣቂ ቡድን ላይ የጀመረውን የማጥቃት ዘመቻ አጠናክሮ በመቀጠል ሕዳር 15-2005 ዓ.ምEthiopian People Patriots Front - EPPF አርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ልዩ ስሙ ጃንሱማ በተባለ ቦታ ባደረገው ውጊያ 14 የጠላት ወታደሮችን በመግደልና 12 በማቁሰል ከፍተኛ ወታደራዊ ድሎችን በማስመዝገብ ግንባሩ የተሰማራበትን ግዳጅ በድል እየተወጣ መሆኑን የግንባሩ ወታደራዊ መምሪያ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዘራፊውና ከነፍሰ-ገዳዩ የወያኔ አምባገነናዊ ገዥ ቡድን ለማላቀቅ ያለው ብቸኛ አማራጭ መንገድ በትጥቅ ትግል ስርዓቱን ማንበርከክ መሆኑን ጠንቅቆ ያወቀው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ሀገርንና ወገንን ለመታደግ ቆርጦ በመነሳት በሰሜኑ የሐገራችን ክፍል ወታደራዊ ስትራቴጅውን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ ሰሞኑን አርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ልዩ ስሙ ጃንሱማ በተባለው ቦታ ባደረገው የማጥቃት ዘመቻ 26 የጠላት ወታደሮችን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ወታደራዊ የበላይነትን የተቀዳጀ ሲሆን፣ ከሞቱት 14 የልዩ ሃይል ታጣቂ ቡድን መካከል አበበ የሚባለው የቀራቅር ተወላጅና አለልኝ የሚባል የደባርቅ ተወላጅ የሆኑት ከፍተኛ አመራሮች መሞታቸውን የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ወታደራዊ መምሪያ ገልጿል።

Monday, November 26, 2012

መቀሌ ዩኒቨርሲቲ እየታመሰ ይገኛል





መቀሌ ዩኒቨርሲቲ በተወሳሰበ ሙስና ውስጥ በመሆኑና የሙስናው ዋና ተዋናዮች ዶ/ር ክንደያ ገብረህይወት እና ዶ/ር ኣብዱልቃድር ከድር የተባሉ ምክትል ፕረዚደንቶች ይውረዱልኝ ብለው ከሶስት ወር በላይ የጠበቁት ጀርመናዊ ፕረዚደንት ችግር ላይ ናቸው።
የቦርድ ሰብሳቢው ኤርትራዊው ኣቶ ቴድሮስ ሓጎስ (የኢፈርት ቦርድ ሰብሳቢም ናቸው) ጀርመናዊውን በአካል እንዳስፈራሩዋቸው ታውቋል!
ይህ የሆነው ደግሞ ለትምህርት ሚንስትር ሳይቀር ግልባጭ ባደረጉት የአዲስ ምክትል ፕረዚደንቶች ሹመት የተነሳ ነው።
ጀርመናዊው ፕረዚደንት ከሶስት ወር በላይ/August-November/ የጠየቁትን ጥያቄ ሳይመልሱ ተኝተው የከረሙት ኣቶ ቴድሮስ ሓጎስ አውቆ የተኛ ቢቀሰቅሱት ይማታል የሚል አዲስ ዓይነት ቢሂል ፈጥረዋል! ከ300 million ብር በላይ ያባከኑን ሰዎች ገለል እንዲሉ መጠየቃቸው ሊመሰግኑ ሲገባ እንግዳውን German ሰውዬ እንደዚህ እንደውሻ የሚያስፈራሩዋቸው እነ ቴድሮስ ሓጎስ ወደ ማፍያነት መቀየራቸው ጉልህ ማሳያ ነው። ይህን ህዝብ ከመጤፍ እንደማይቆጥሩትና እንዳሻቸው መኖር እንደሚችሉ ግልፅ ማሳያ ነው። ይህ ህዝብ በሚከፍለው ግብርና በደሙ እየነገዱ የሚኖሩት እስከ መቼ ነው? ትግራይ ተማርሯል በማስፈራራት ና በጉልበት ልክ እንደ ትግራይ ህዝብ ደመኛው ለገሰ አስፋው ትግራይን ኤርትራዊው ቴድሮስ ሓጎስ እየገዙዋት ነው። የሚሰርቅን ሰው መጠየቅ ሲገባቸው ኣብሮዋቸው እንደሚሰርቅ በግልፅ በሚያሳይ መልኩ መከላከላቸው ይህ ስርዓት ምን ያህል እንደዘቀጠ፣ ወድቀቱም እንደቀረበ ያሳያል።

ኢሳትን አያችሁ የተባሉ ወታደሮች ታሰሩ፤ ሠራዊቱ ዉስጥ የተፈጠረዉ መከፋፋል አሁንም እንደቀጠለ ነዉ

 

 

ኢሳትን አያችሁ የተባሉ ወታደሮች ታሰሩ፤ ሠራዊቱ ዉስጥ የተፈጠረዉ መከፋፋል አሁንም እንደቀጠለ ነዉ

[ግንቦት 7 ዜና] ሰሜን ኢትዮጵያ ዉስጥ በባድሜ ግንባር ወታደራዊ ክበባቸዉ ዉስጥ ቁጭ ብለዉ በናይልሳት የሚተላለፈዉን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንን ሲከታተሉ የተገኙ በርካታ ወታደሮች ለሁለት ሳምንታት ታስረዉ በከባድ ማስጠንቀቂያ መለቀቃቸዉን ትግራይ ዉስጥ የሚገኙ ወታደራዊ ምንጮቹን በመጥቀስ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት ዘገበ። አንድ ስማቸዉና ማዕረጋቸዉ እንዳይጠቀስ የጠየቁ ከፍተኛ መኮንን በስልክ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት ወታደሮቹ የታሰሩት በክበባቸው ውስጥ ቁጭ ብለዉ የኢሳትን ዝግጅት ሲከታተሉ ሲሆን ከ 14 ቀናት እስርና እንግልት በኋላ የተፈቱት የዲሻቸውን አቅጣጫ ወደ ናይል ሳይት ያዞሩት ሳያዉቁ በስህተት መሆኑን ለበላይ አለቆቻቸው ተናግረዉ ዳግመኛ ኢሳትን እንደማይመለከቱ ቃል ከገቡ በኋላ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

የሱዛን ራይስ ሸፍጥ በቤንጋዚው ጥቃት ላይ!

    

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

Click here for English version

Click here for PDF

በሴፕቴምበር 2 2012 የአሜሪካዋ አምባሳደር በተባበሩት መንግስታት: ሱዛን ራይስ በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የቀብር ስርአት ላይ ስሜታዊ ሆና የሚያቅለሸልሽ ቃላት ያዘለ ንግግር አነብንባ ነበር፡፡ መለስን፤ ‹‹የማይደክምና ራሱን የማይወድ››በአጠቃላይ እሱነቱ ለስራውና ለቤተሰቡ የሆነ ብላዋለች፡፡ ‹‹ጠንካራ፤ በእምነቱ የጸና እና በእርግጥም ለጂሎችና ለደደቦች እሱ እንደሚጠራቸው ትእግስቱ ትንሽ ነበር፡፡ ሱዛን ራይስ ይህን ቅጥ ያጣና ከአንድ አሜሪካን ከሚያህል ሃገር ወኪል ጨርሶ ሊሰማ የማይገባ ያልተገራ ንግግር ስታደርግ ጅልና ደደብ የሚለውን ቃል በድፍረትና በአጥንኦት የለጠፈችው በኢትዮጵያዊያን ነጻ ጋዜጠኞች፤የተቃዋሚ መሪዎች፤ተሟጋቾች፤የፖለቲካ እስረኞች፤የሲቪል ማሕበረ ሰብ መሪዎች፤እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ላይ ነው፡፡ የንግግሯን ቪዲዮ በመመልከት ሴትዮዋ ይህን ንግግር የመለስን ተቃዋሚዎች በመጨረሻ ጡጫ ደረታቸዉን ብላ ለመለስ የአስከሬን መሸኛ አድርጋ ማቅረቧ እንደነበር ያስታውቃል፡፡

Susan Rice, the U.S. Ambassador to the U.N. Addis Ababa speech, Alemayehu G. Mariam‹‹ አንድ አይነት ላባ ያላቸው ወፎች አብረው ይከንፋሉ›› ይባባል፡፡ ራይስ እንደ መለስ ሁሉ ተቃዋሚዎቿንና ሃሳቧን የማይጋሯትን ትሳደባለች ታንቋሽሻለች፡፡ በስቴት ዲፓርትመንት አካባቢ የሚያውቋት በዘለፋ በቁጣና በማስፈራራት አነጋገራዎ ነው፡፡ በዚህም አጉል ደንፊ ተብላ ትታወቃለች፡፡ አለያም በጣም በሚያውቋት ዘንድ ‹‹የቻይና መደብር በሬ›› (አተራማሽ ወይም በጥባጭ ማለት ነው) ይሏታል፡፡ በስብሰባዎች ላይ በቃላት ርችት፤በአፈነበልባል፤በጣት ቀሳሪነት ራይስ ትታወቃለች፡፡ በአንድ ወቅት በአሜሪካን ዲፕሎማቶች ዋና ታዋቂ በነበሩት ሪቻርድ ሆል ብሩክ ላይ የበላዮች ስቴት ዲፓርትመንት አባላት ስብሰባ ላይ በአሜሪካንና በሌላውም ዓለም በሳቸው ደረጃ ካሉ ሰዎች የማይጠበቀውንና ጸያፍ ተብሎ የሚጠራውን ድርጊት በአደባባይ የመሃል ጣታቸውን ቀስረውባቸዋል ይባላል፡፡