[ተማሪዎች የስልጠና ሰነድ በማቃጠል ተቃውሟቸውን አሰምተዋል]
ተማሪዎችና የፖለቲካ ተቋዋሚ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ፖሊሲ ላይ ያተኮረው ለከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት ተማሪዎች የሚሰጠውሥልጠና ከጥሪው አንስቶ በግዳጅ የሚካሄድ መሆኑን ነው የሚናገሩት የኢትዮጵያ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የሁለት ሳምንታት የፖሊሲ ስልጠና ላይ መሆናቸውን መንግስት አስታውቋል ።
ነሐሴ የተጀመረው ይኽው ስልጠና ተማሪዎች በግዳጅ የሚሳተፉበት መሆኑን አንዳንድ ተማሪዎችና ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ይናገራሉ። መንግሥት ግን ይህን ያስተባብላል።
ተማሪዎችና የፖለቲካ ተቋዋሚ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ፖሊሲ ላይ ያተኮረው ለከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት ተማሪዎች የሚሰጠውሥልጠና ከጥሪው አንስቶ በግዳጅ የሚካሄድ መሆኑን ነው የሚናገሩት። በተለይ በስልጠናው የማይሳተፉ ተማሪዎች በመጪው አመት የትምህርት እድል እንደማያገኙ ይገልፃሉ ።ከዚህ በተጨማሪ የትምህርት ነጻነትና ፖለቲካዊ ሰበካ በመርህ ደረጃ አብረው የማይሄዱ ሆኖ እያለ ተማሪዎችም ይህን አስመልክቶ ቅሬታቸውን እንዳያሰሙ ተቃውሞ እንደገጠማቸው ነው የሚገልፁት። በትምህርት ላይ ሳሉ የኢህአዴግ አባል የሆኑ ተማሪዎች በኩል መመዝገባቸውንና የስልጠና ቅጽ መሙላታቸውን በስልጠናው የሚሳተፉ ተማሪዎች ይናገራሉ። ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ አንድ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ የስልጠናውን አጀንዳዎች ያብራራል።