Wednesday, November 27, 2013

በሳውዲ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰው ሰቆቃ ቀጥሏል


ነፍሰጡር ኢትዮጵያዊት በአሰቃቂ ሁኔታ ሞታለች

saudi ethio13


ሪያድ አሚራ ኑራ ዩኒቨርስቲ በሚገኝ ጊዜያዊ መጠለያ ሜዳ ላይ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና በሳውዲ ፖሊሶች መሃከል በተነሳ ግጭት አንዲት ነፍሰጡር ኢትዮጵያዊት በአውቶብስ ተገጭታ ህይወቷ አለፈ።
ሪያድ መንፉሃ እየተባለ ከሚጠራ አካባቢ ሰሞኑንን በሳውዲ ፖሊሶች ታፍሰው ከከተማይቱ 120 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ወደ ምትገኝ፡ በተለምዶ ሚንዛህሚያ እየተባለ የሚጠራ እስርቤት ተወስደው ከነበሩ 10 ሺህ ኢትዮጵያውያን መሃከል ግማሽ ያህሉ በ17 አውቶብስ ተጭነው ማምሻውን ሪያድ ከተማ አሚራ ኑራ እየተባለ የሚጠራ ዩኒቨርስቲ ሜዳ ላይ መጣላቸውን ተከትሎ ከባድ ሁከት መቀስቀሱን ከሪያድ የሚደርሱ መረጃዎች ያመለክታሉ።
ይህን ተከትሎ በዩኒቨርስቲው ግቢ ውስጥ በኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች እና በሳውዲ ፖሊሶች መሃከል ከባድ ግጭት መከሰቱን የሚገልጹት እነዚህ ምንጮች አዲት ነፍሰጡር ሴት ከድንጋይ ውርወራው ለማምለጥ ከግቢው ለመውጣት ሲበሩ በነበሩ አውቶብሶች በአንዱ ተጭፍልቃ መሞቷን ገልጸዋል። ግጭቱ በጣም ዘግናኝ፡ አሰቃቂ እንደነበር የሚገልጹት የአይን ምስክሮች የሳውዲ ፖሊሶች ማንም ሰው ካሜራ እንዳይቀርጽ ለማገድ ከአካባቢው ኢትዮጵያውያኑንን በማራቅ አስከሬኑን ነጭ ነገር ሸፍነው በቅጽበት በአምቡላንስ ተጭኖ ወደ ሆስፒታል እንዲወሰድ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
ዛሬ ረፋዱ ላይ በ17 አውቶብስ ተጭነው ሚንዛህሚያ እየተባለ ከሚጠራ አካባቢ እንደመጡ ከሚነገርላቸው ኢትዮጵያውያን መሃከል በአብዛኛዎቹ ሴቶች ህጻናት እና ነፍሰጡር እንደሆኑ የሚናገሩት ምንጮች አውቶብሶቹ የተጠቀሰው አካባቢ ሲደርሱ በውስጥ የነበሩ ኢትዮጵያውያኖች ኤርፖርት እንወስዳችሃለን ብላችሁ እዚህ ባዶ ሜዳ ላይ አምጥታችሁ ለምን ትበትኑናላችሁ በማለት ከአውቶብሱ አንወርድም በሚል የኡ ኡ ታ ጩሀት በማሰማት ተቃውሞቸውን ሲገልጽ የሳውዲ ፖሊሶች የአካባቢውን ጸጥታ ያደፈርሰውን የህዝብ ኡ ኡታ ጩህት ለማርገብ ጥረት በሚያደርግበት ወቅት ድንጋይ ውርወራ መጀመሩን የሚገልጹ እማኞች በፖሊስ እና በህዝቡ መሃከል በተነሳው ግጭት አያሌ ህጻናት እና አረጋውያን መረጋገጣቸውን በመጥቀስ እስካሁን በወገኖቻችን ህይወት ላይ የደረሰው አደጋ በውል ባይታወቅም ብዛት ያላቸው አምቡላሶች ኢትዮጵያውያኑ ከተጠለሉበት ግቢ «ሳይረን» እያሰሙ ሲወጡ መታየታቸውን አክለው ገልጸዋል።

ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ሚንዛህሚያ እየተባለ ከሚጠራው መጠለያ በ17 አውቶብሶች ተጭነው የመጡት ወገኖቻችን ከአውቶብሶቻቸው እንዳልወረዱ እና በአሁኑ ሰአት ብጥብጡ ተባብሶ መቀጠሉ ተገልጾል። ቀደም ሲል ለፖሊስ አሻራ ትሰጣላችሁ ተብለው ከተለያየ አካባቢ ሪያድ ከተማ መለዝ እየተባለ የሚጠራ አካባቢ የሚገኝ አንድ ትልቅ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ እስከ 7 ሺህ የሚጠጉ ወገኖቻችን ያለዳስ «ድንኳን» ሜዳ ላይ ተጠለው ፀሃይ ብርድ እና ዝናብ እይተፈራረቀባቸው መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሎል።
በዚህ ዙሪያ ጉዳዩ ወደ ሚመለከታቸው በሪያድ የኢትዮጵያ አምባሳደር መሃመድ ሃሰን ስልክ በመደወል ስለጉዳዩ ለማነጋገር ያደረኩት ጥረት እስካሁን አልተሳካም! የዲያስፖራው ሃላፊ ዲፕሎማት አቶ ተመስገን ኡመር ቴሌፎን ቁጥር ይህ ሁከት ከተቀሰቀስ ወዲህ መስመሩ ከአገልግሎት ውጭ ነው የሚል መለዕክት የሚያስተላልፍ በመሆኑ የኤምሲውን ተጠሪዎች እስካሁን ማግኘት አልተቻለም ።
Ethiopian Hagere በፌስቡክ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ከጅዳ በዋዲ የላኩት

No comments:

Post a Comment