Sunday, May 19, 2013

የዜጎች መብት ረገጣና አፈና በኢትዮጵያ



መሠረት አባተ ከኖርዌይ ግንቦት 2005 

እንደምናውቀው አገራችን ኢትዮጵያ የዜጎች መብት ከማይከበርባት አገር አንዷ ናት ብል ሁሉም 
የሚስማማበት እውነት ነው። ዜጎችን ለትምህርት፣ ለልማት እንዲሁም መልካም ዜጋን ከመቅረጽ ይልቅ 
ቦዜኔ፣ ተረጂ፣ በራስ ከመተማመን ይልቅ ተመጽዋች ዜጎች ያሉባት አገር እንድትሆን ከወያኔ ቡድን 
የተሰጣቸው ገጸ በርከት ከሆነ ብዙ አመታትን አስቆጥሮአል። 

በአረብ አገራቱ ኢትዮጵያዊያን እህቶቻችን ላይ እየተፈጸመ ያለው ጥቃት ምን ይገርማል! ምክንያቱም ወያኔ 
በዜጎች ላይ እያደረሰ ያለው ከብዙ በጥቂቱ ይህንን ይመስላል። አንዲት ሴት እንደዜጋ ለአገሯ በሙያዋ 
ማገልገል እየቻለች ነገር ግን የሴቷ ጥቃት የሚጀምረው ከወያኔ ባለሥልጣናት የሚቀርብላትን ጥያቄ 
ከማሰተናገድ ይጀምራል። በኢትዮጵያ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለመከላከልና ግንዛቤ ለመጨበጥ 
ዋንኛው መንገድ መደራጀት እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል። ለዚህም አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ሴቶች 
ማህበር International Ethiopian Woman Organization (IEWO) በአለም አቀፍ ደረጃ በሴቶች ላይ 
የሚደርሰውን ግፍና እንግልት እንዲሁም በየአገሩ በስደት ላይ መብታቸውን የሚያስከብርላቸው አተው 
የወገን ያለ እያሉ ሲጮሁ እየደረሰላቸው ያለው ይኔው ድርጅት ነው። 

የሴቶችን መብት ከመጠበቅ እና በሕግ እስከማረጋገጥ ድረስ በታሪክም በቁርጠኝነት የታገለ እንዲሁም 
የሴቶች አስተዋጾ ከወንዶች እኩል ነው ብሎ በትግሉም እኩል አላፊነት እና ድርሻ እንዳላት ያረጋገጠ 
ፓርቲ ሕዝባዊ አብዮታዎ ፓርቲ ኢሕአፓ ለመሆኑ በፓርቲው ተዘጋጀተው ለሕዝብ ለንባብ የበቁ የታሪክ 
መጽሐፍቶችን መመርመር በቂ ይሆናል።


ወያኔ ለማፈን እና ለማስፈራራት እንዲያመቸው የአሸባሪ ሕግ በማለት ዜጎች አሳባቸውን እንዳይገልጹ፣ 
እንዳይጠይቁ፣ እሺ እንጂ ለምን የሚባል ነገር ለገዥው ቡድን የማይስማማ ሰለሆነ ይህንን ሲያደርጎ የተገኙ 
ሁሉ እጣፈንታቸው እስር እንደሆነ እያየነው ነው። እስቲ ከዓፈናና ረገጣው ዙሪያ ጥቂቱን ላውጋቹ፤ 
ብርቂያዋና ቆራጧ የሴቶች አርያ የነበረችውን እህታችን አበራሽ በርታን ፋሽስቱ ወያኔ ከገባ ጀምሮ 
እንደያዛት እስካሁን የደርሰችበት አልታወቀም። 

ጋዜጠኛና መምህርት ርዕዮት ዓለሙ ያለምንም ጥፋት ማሰሩ ሳያንሰው ባጋጠማት የጤና መታወክ 
ምክንያት ሕክምና እዳታገኝ የተለያዩ ሰንካላ ምክንያቶችን እየደረደሩ ጠባቂ የፖሊስ ኃይል የለም እና 
የመሳሰሉትን በማለት ሕመሟ ጸንቶባት ትገኛለች። እንዲሁም የእስር ቤቱ ጠባቄዎች በመዛትና 
በማስፈራራት አልታዘዝ ብለሻል ጨለማ ቤት ውስጥ ነው የምናስርሽ በማለት ሰው የመሆን መብቷን 
ገፈው በመጥፎ ቃላታቸው ሲደበድቧት ትንሽ እንኳን በአስነዋሪ ምግባራቸው የማይጸጸቱ ናቸው ። 

በአገራችን ኢትዮጵያ የዜጎች ጥቃት መች ይሄ ብቻ ሆነና በአንድ ብሔር ላይ የሚደረገው ዘመቻ እየተባባሰ 
እንጂ እየተሻሻለ አልመጣም። ክልላቹ ወይም ቦታቹ አይደለም ይህንን ቦታ ለቃቹ ሂዱ በማለት 
የአማራውን ሕብረተሰብ እያጉላሉት መሆኑ ግልጽ ነው። ይህ የዘር ፖለቲካ ያሰከራቸው ወያኔዎች ምንም ዓይነት ኢትዮጵያዊነት ስሜት ስለሌላቸው በአማራው ላይ ያላቸውን ጥላቻ በጉልህ እያሳዩ ነው። ዜጋን 
በማፈናቀል ሂደት ውስጥ በተለይ በተለይ ተጠቄ የሆኑት ሴት እህቶቻችንና ሕጻናቶች ናቸው። የሚያጠቡ 
እናቶች፣ የደረሱ እናቶች ምንም ዓይነት ዕርዳታ በሌለበት ሁኔታ በጎዳና ላይ ነው የወለዱት። በተጨማሪ 
ሌላው ደግሞ ከቢኔሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው ከፍኖተ ሰላም የተመለሱት የአማራው ተወላጆች በቁር እና 
በርዓብ እየተሰቃዩ መሆኑ እና እንዲሁም እናትና ልጅ ተነጣጥለዋል እስካሁንም ያልተገናኙ ብዙ የቤተስብ 
አባላቶች አሉ። 

እነዚህ ዜጎች ሰርተው የሚያድሩና ቤተሰቦቻቸውን የሚያሰተዳድሩ ሆነው ሳለ፤ አሁን ግን እርጥብ 
አጥተው ሥራስር ለመብላት ተገደዋል። አርሰው እንዳላበሉ እና ማድጋቸው ሙሉ እንዳልነበር አሁን ግን 
የሰው እጅ ጠባቄ እንዲሆኑ ተፈርዶባቸዋል። የወያኔ የእድገት ትርጉሙ ይህ ይሆን እንዴ? 

የአገር መሪ ተብዬው ኃይለማርያም ደሳለኝ በዘረፋ ላይ የተሰማሩ ባለሥልጣናት ናቸው ይህንን የማፈናቀል 
ሥራ የሰሩት ብለው የሚሉት እንደው አሁንስ ውሸት አልቆባቸው ካልሆነ በቀር እንዴት ነው አንድ ተራ 
የወረዳ ካድሬ ዜጎችን ከቦታ ቦታ ማፈናቀል የሚችለው? በኢትዮጵያ ውስጥ መንግስት የለም ማለት ነው? 
የሚዋሹት ወሸት መልሶ እራሳችውን ጥያቄ ውስጥ የሚከት እንደሆነ አይረዱም እንዴ? የውጪ ጉዳይ 
ሚኒስትር ዴኤታ ደግሞ እንዲህ ይላል የተባረሩበት ምክንያት ደን ጨፍጭፈው ነው በማለት የሐሰት 
ናዳውን ያወርዳል ነገር ግን እውነቱ ይህ ነው። የዘር ማጥፋት ወንጀል በደን ምክንያት አድርገው 
ኘሮግራማቸውን ለማስጸም እንደ ሽፋን የተጠቀሙበት የጅል ብልጠታቸው ነው። የከማሼ ዞን አስተዳደር 
በበኩሉ ማባረሩ በክልል ደረጃ በዕቅድ የተያዘ እንደሆነ ይናገራል። የአማራውን መፈናቀል አስመልክተው 
ለሚዲያ የሚሰጡ መግለጫ እርስ በርሱ የሚጣረዝ እና ወጥነት የሌለው እንደሆነ እያየንና እየሰማነው ያለ 
አቅ ነው። መለስ ሳይጨርሰው ያለፈውን የመብት ረገጣ የዛሬዎቹ ሥልጣን ተረካቢዎች የባለ ራዕዩን 
ጅምር ተቀብለው የዘር ማፀዳት ዘመቻ ተያይዘውታል። 

የወያኔ የገደል ማሚቱ የሆኑ ጥቂት ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን የማይውክሉ ዜጎች ልክ እንደ ኤርትራዋ 
ሚሚ ስብሐቱ ዓይነት የስርዓቱ ፖለቲካ ለማስፈጸም አንዳንድ ቦታ ላይ ጣል ጣል የተደረጉበት ሁኔታ 
እንዳለ እናውቃለን። ይህ ማለት ግን የዜጎች መብት እና እኩልነት ተጠብቋል ወይም የተሻሻለ ደርጃ ላይ 
ነው ያለው ብሎ ለመናገር የወያኔን ውሸት መድገም ነው የሚሆነው። ለሥረዓቱ አገልጋይነት የተመረጡ 
ሲሆኑ፤ የፖለቲካ ኘሮፓጋንዳ ማራገብ እንዲሁም ብቻ እንጂ ስለራሳቸው መብትና እኩልነት የመጠየቅ 
አቅሙም ሆነ ብቃቱ የላቸውም። 

በመጨረሻ::::---- ቆራጥና አገር አድን ከሆነው ከኢሕአፓ ድርጅት ጋር አብሮ በመቆም፤ ይህንን በሕዝባችን 
ላይ እየደረሰ ያለውን ቅኝ ግዛት እያየን ዝም የሚል ህሊና የለንምና፤ የአቅማችንን አስተዋጾ በማደርግ 
ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችንን እንታደጋቸው። ድር ቢያብር አንበሳ ያሥር ነውና ዜጎችን ለማዳንና 
አገራችንንም ከአንባገነኑ የወያኔ ሥርዓት ነጻ ለማውጣት አንድ እንሁን። 

እግዛብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!! 

No comments:

Post a Comment