Wednesday, October 31, 2012

“በፖለቲካ ቂም” የተመሰረተ ክስ ውድቅ ሆነ ዳኞቹና ዓቃብያነ ህጉ በፖለቲካ ውሳኔ ተባረሩ





ጋምቤላ ሁለት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞችና ሁለት ጠበቆች “በፖለቲካ ቂም ውሳኔያችንን አናዛባም” በማለታቸው ከስራና ከሃላፊነታቸው መሰናበታቸው ታወቀ። ሁለት የክልሉ የስነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃብያነ ህግም በተመሳሳይ ውሳኔ ከሃላፊነታቸው መባረራቸው የተጠቆመ ሲሆን ውሳኔው የክልሉ ፕሬዚዳንት ወንድም የሆኑትን ዓቃቤ ህግ አላካተተም።
በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሰረተባቸውን ሶስት የጋምቤላ ክልል ባለሥልጣናት የፍርድ ሂደት ያስቻለው የጠቅላይ ፍርድ ቤት ተከሳሾቹን በነጻ የለቀቀው ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ነው። አስራ አንድ አባላት ያሉት የክልሉ አስተዳደር ስድስት ለአምስት ሆነ ውሳኔ የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ በነበሩት አቶ ጀምስ ዴንግ፣ ምክትላቸው ኮንግ ጋልዎክና የክልሉ የፖሊስ ኮሚሽነር በነበሩት ኦቲየንግ ኦቻን በሙስና እንዲወነጀሉ ውሳኔ አስተላልፎ እንደነበር በማስታወስ ለጎልጉል መረጃ ያስተላለፉት ክፍሎች እንዳሉት በተጠቀሱት የቢሮ ሃላፊዎች ላይ ክስ የመሰረተው የክልሉ ጸረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ህግ ነበር።

Friday, October 26, 2012

''ላለመማር መማር...... ፤ ከ’ራስ ክህደት እስከ ሀገር ማፍረስ.....”

በመጀመሪያ ‘ራሳቸውን ከዱ፣ ከዚያም በጥላቻ ታውሩ፣ ከዚያም ኢትዮጵያዊነትን ኢትዮጵያን አምርረው ጠሉ፣ ከዚያም
በታሪካዊ ጠላቶቻችን እየተመሩና እየታገዙ፣ የገንዛ ወገናቸውን ‘ርስ-በ’ርስ እያበጣበጡና እያለያዩ፣ ኢትዮጵያን እያፈራረሱ፣
ለባዕዳንና ለታሪካዊ ጠላቶቻችን እየቸበቸቡ አሁን ካሉበት ደረጃ ደረሱ። ወያኔ/ኢሕአዴጎች። የተከበሩት ኔልሰን መንዴላ እንዲህ ይሉናል ''..... ፍቅር አብሮን የተወለደ በተፈጥሮ ያገኘነው ነው። ጥላቻ ግን በትምህርት ያገኘነው ነው። ስለዚህ ጥላቻን በትምህርት ልናስወግደው እንችላለን።...."። ግን በ'ኛ ሀገር ለወያኔ ገዥዎቻችን ጥላቻና ክህደት አብሮ'ቸው የተፈጠረ ይመስላል። ያለፈው አልበቃቸው ብሎ አሁንም የጥላቻንና የዘረኝነትን መርዝ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ በህዝብ ላይ ይረጫሉ። ''ለምን?.." ያለውን ደግሞ ያስራሉ፣ ያሳድዳሉ፣ ይዘርፋሉ፣ ይገላሉ፣ ያስገድላሉ። እንደ’ነሱ ጠበንና አንሰን፣ ሀገራዊነትን አውግዘን፣ ስብእናችን ሁሉ ''ጎጠኝነት'' አንዲሆን ሌት ተቀን ይደክማሉ። ለመሆኑ ከዘመናት በፊት ''ዘሬ የሰው ልጅ ነው፤ ሀገሬም ዓለም ነው።'' ያለው ደራሲ (ስሙን ማስታወስ ስላልቻልኩ ይቅርታ።) በዚህ ዘመን ወያኔወችን እጅ ቢጥለው ምን ይል ይሆን? እነሱስ ምን ያደርጉት ይሆን?
በቅርቡ የወያኔው ''የበኩር አባት'' አቶ ስብሐት ነጋ ''….. ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሾመው ኢሕአዴግ ዱሮም አስቦበት ወንበሩን ከአማራና ከኦርቶዶክስ አማኞች ለማጽዳት በተዘጋጀበት እቅድ ነበር…….." ሲሉ ተሰምተውል። ይህ በ'ርግጥ የለመደነው ክህደትና ሸፍጥ ነው። ታዲያ አኒህ ሰው ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊያን ያላቸው ጥላቻ ይበልጥ በሽበታቸው ዘመን ስር እየሰደደና እየተባባሰ መምጣቱን ያሳያል። ብዙውን ግዜ በሌሎች ላይ ጥላቻ ያለባቸው ሰዎች ለራሳቸው ከሚሰማቸው የበታቸነት ስሜት የሚመጣ ሲሆን መድረኩንና አጋጣሚወን ሲያገኙ ደግሞ እንደወያኔ ሀገረንና ህዝብን ከማዋረድና  ይዘው ከመጥፋት  ወደ ኋላ አይሉም። የአቶ ስብሐት የክህደትና የጥላቻ የበኩር ልጃቸው የሆነው አቶ መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያን አፍርሶና ሕዝቦቿ 'ርስ-በርስ
አባልቶ ሳይጨርስና ሳይሳካለት ወደ ማይመለስበት ስለሄደ፤ እሱ ያላያትን ''የፈራረሰች ኢትዮጵያን" እሳቸው ለማየት ካላቸው ጉጉት አንጻር የሚያደርጉትን አ'ተው ግራ ተጋብተዋል። ምክንያቱም ''ታላቋን ትግራይ" የመመስረት "ቅዥት''፣ "ቅዥት'' ሆኖ እንደቀረ ሁሉ፣ ኢትዮጵያን የማፈራረሱም እኩይ ምግባራቸው ደግሞ ‘’ቅዥት’’ ሆኖ ሊቀር መሆኑ እንቅልፍ ነስቷቸዋል።