Friday, September 6, 2013

አንዷለም አራጌ ከቃሊቲ ማጎሪያ የላከው መልዕክት እጃችን ደርሷል – የሐምሌ ጨረቃSeptember 5, 2013

 

አንዷለም አራጌ ዋለ (ከቃሊቲ ማጎሪያ) ክፍል ሁለት


Ato Andwalem Araga (UDJ)
በሀገሬ ሰማይ ስር በሚደረገው የተቃውሞ ፖለቲካ እንቅስቃሴ ከኢዴፓ እስከ አንድነት ፓርቲ ድረስ በመሳተፍ ለአስራ ሶስት ዓመታት ያህል የምችለውን አስተዋጽኦ አድርጌያለሁ፡፡ ይህ ኩነትም የፓርቲዎችን ጓዳ ፈትሼ ግንዛቤ እንዳገኝ ስላመቻቸልኝ፣ በቀጣይ ህዝባችን የፖለቲካና ሰብአዊ መብቶቹ ተከብረው ነፃነቱን እንዳያገኝ እንቅፋት ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ የማስባቸውን ነጥቦች እንደሚከተለው ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡

1-እንደ ገዥው ፓርቲ፣ ተቃዋሚ ድርጅቶችም ከኋላቀሩ የፖለቲካ ባህላ የተላቀቁ አለመሆናቸው ነው፡፡ እናም አዲስ የፖለቲካ ባህል ለማስጀመር ከመስራት ይልቅ ሳያውቁት ከዘመነ-መሳፍንት የተቀዳውን የፖለቲካ ባህል በተሻለ ተግባራዊ ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ ዛሬም ይታያሉ፡፡
2-የእስከ ዛሬውን የከሸፈ ሂደት የገመገመና የኢትዮጵያን ህዝብ ለአንዴና ለመጨረሻ ከተጫነበት የጭቆና ቀንበር ለማላቀቅ የሚያስችል በውል የታሰበበትና የተጠና የፖለቲካ ቀመር እጦት በተቀቃዋሚ ፓርቲዎች ዘንድ በጉልህ ይንፀባረቃል፡፡

3-የማያምኑበትን መቃወም ተገቢ የሆነውን ያህል የየራሳችንም ህፀፆች ያለርህራሄ ማየት፣ አይቶም ነቅሶ ማውጣት ተገቢ ነው፡፡ ነገር ግን በተቃዋሞ ጎራ ባለነው ፖለቲከኞች ላይ ይህንን የማድረግ ችግር ይታይብናል፡፡ ህፀፆችን ቀድሞ ማየቱ ከሌላ ወገን የሚሰነዘረው ነቀፋ ምክንያቱን ለመረዳት እድል ይሰጣል፡፡ በትችት ከመሰበርም ይታደጋል፡፡

4-ከ1960ዎቹ ጀምሮ የኢትዮጵያ ፓርቲዎች መለያ ከሆኑት አንዱ ‹ግትርነት› መሆኑ አከራካሪ አይመስለኝም፡፡ ይህ ሁኔታ በፓርቲዎች መካከል ብቻ ሳይሆን፣ በራስ ፓርቲ አባላት ውስጥም የሚፈጠሩ ችግሮች ከግትርነት የሚነሱ ናቸው፡፡ ‹‹መሸነፍ››፣ ‹‹ማሸነፍ››፤ ‹‹መንበርከክ››፣ ‹‹ማንበርከክ›› በሚለው የጫወታ ህግ ታስረን በቆምንበት ስንረግጥ በአስከፊው የመከራ ዘመን እንድንቆይ አድርጐናል፡፡ ችግር የመፍቻ ስልትም ሆነ ባህል አላዳበርንም፡፡ እንዲያውም የትግሉ እንቅስቃሴ ከአገዛዙ ጋር መሆኑ ቀርቶ በእኛ መካከል ሆኗል፡፡

Monday, September 2, 2013

ዛሬ ከሰልፉ ላይ ታፍነው የተወሰዱ ሙስሊሞች በከፊሉ (ድምፃችን ይሰማ)September 1, 2013


 
Ethiopian Muslims 1ዛሬ ከሰልፉ ላይ ታፍነው የተወሰዱ ሙስሊሞች አብዛኞቹ በኤግዝቢሽን
ማእከል ግቢ ውስጥና ከዋናው መድረክ ጀርባ ካለው የኢትዮጵያ የሰላም እና የልማት
ኢኒስቲትዩት ግቢ ውስጥ ይገኛሉ፡፡
ሙስሊሙ እየተነጠለ ሲወሰድ
Ethiopian Muslims 1
ሙስሊሙ እየተነጠለ ሲወሰድ

Thursday, August 29, 2013

ተስፋሁንን መግደል ለኢህአዴግ ተስፋ ይሆናታልን….!?


bbbተስፋሁንን መግደል ለኢህአዴግ ተስፋ ይሆናታልን….!?
አብዲሳ የብዙ ጊዜ ወዳጄ ነበር፡፡ በየገጠሩ እየዞርን በርካታ ስራ አብረን ሰርተናል፡፡ የዋህነቱ እጅግ በጣም አስገራሚ ነበር፡፡ በየክልሉ ስንዞር አበሉን የሚጨርሰው “ቸገረኝ” ላለው ሁላ መበስጠት እንደነበር አብረነው የሰራ ሁላ እርሱን የምንለይበት ባህሪው ነው፡፡ ይሄ ልጅ በአንዱ ቀን ለስራ ልንሄድ የተቀጣጠርንበት ቦታ ሆነን ስንጠብቀው ስንጠብቀው ሳይመጣ ቀረ… ስልኩን ብንደውልልት አይሰራም፡፡ ካለንበት እየተንቆራጠጥን… ወደ ሶስት ሰዓት ድረስ ዘግይተን ጠበቅነው የውሃ ሸታ ሆነብን… ምን ሆነ ብለን እየተጨነቅን እንጀራ ነውና ጉዟችንን ቀጠልን…
አብረን ስንጓዝ ከነበርነው መካከል አብዲሳን በቅጡ የምናውቀው ሰዎች “ይሄኔ አንድ የታመ ሰው አጋጥሞት ሆስፒታል ሳላደርስ አልሄድም ብሎ ነው…” ….ወይ ደግሞ “…አንዱ ገንዘብ ተቸግሮ አጋጥሞት  ምንም ሳያስቀር ገንዘቡን ሰጥቶ ወደ እኛ መምጫ ራሱ ተቸግሮ ይሆናል …” ካልሆነ ግን “…ዘራፊዎች አግኝተው ጉድ አድርገውት ሊሆን ይችላል…. እያልን መገመታችንን ተያያዝነው…
ግምታችን ሁሉ ትክክል አልነበረም፡፡
አብዲሳ በስንተኛው ጊዜ በቴሌቪዥን መስኮት መታየቱን ሰማን… በየዋህነቱ የተቸገረ በመርዳቱ የምናውቀው አብዲ “አሸባሪ” ተብሎ በመንግስት ቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ አብዲሳ “አሻባሪ” ከተባለማ እኛ ምን ልንባል ነው… ብለን ራሳችንን እንደ ነውጠኛ የምናየው እኛ በጣም ተደነቅን!
አብዲ ወደ አምስት ወራት በማዕከላዊ፣ ወደ አምስት አመት በቃሊቲ እንዲሁም ሁለት ሶስት አመት ነው መሰለኝ በዝዋይ ማሰሪያ ቤቶች ቆይቶ ነፃ ነህ ተብሎ እስኪሰናበት ድረስ በአስር ቤቱ ውስጥ ሲደርስበት በነበረው መከራ ብዙ ጉዳት ደርሶበታል፡፡ ታድያ ከእስር ቤት ሊወጣ አካባቢ አንድ ባለስልጣን ብጤ ሰውዬ ጎብኝተውት ነበር፡፡

የእኛ “መንግስት” (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ)


August 29, 2013

“በእያንዳንዱም መንግስት የሚያድሩ ብዙ ልዩ ልዩ ነገዶች ይኖሩ ይሆናል፡፡ ስለ ሆነ መንግስት አንዱን ነገድ አጥቅቶ ሌላውን ነገድ ለመጥቀም ሥራው አይደለም፡፡ አስተካክለን ካሰብን ዘንድ መንግስት መቆሙ ለሕዝቡ ሁሉ ጥቅም ነው፡፡ ጥረቱም ህዝቡን ሁሉ በትክክል ለመጥቀም ያልሆነ መንግስት ሊቆም አይችልም፡፡ ለአንዱ ነገድ ወይም ለጥቂት ሰዎች ብቻ ማድላት ለመንግስት የሚገባ ሥራው አይደለም” ይህንን መግቢያ የወሰድኩት በልዑል የኢትዮጵያ መንግስት አልጋ ወራሽ ተፈሪመኮንን ማተሚያ ቤት የካቲት 1 ቀን 1917 ዓ.ም ከታተመው የነጋ ድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ‹‹መንግስትና የሕዝብ አስተዳደር›› መፅሀፍ ነው፤ ዛሬም ያለንበትን ዘመን ይዋጃልና፤ በተለይ ስለ‹‹ነገድ›› የተጠቀሰውን አርቀን ሰቅለን፣ ‹‹ለጥቂት ሰዎች ብቻ ማድላት›› የምትለዋን ሀረግ በወጉ ካጤንናት ለጊዜያችን በልክ የተሰፋች መሆኗን ለመረዳት አስቸጋሪ አይደለም፡፡
Journalist Temasegan Dasaleg
እናም የስርዓቱን የአስተዳደር ዘይቤ ያለፍርሃት አደባባይ ካዋልነው የቀድሞ ገዥዎቻችን የተጓዙበትን ጎዳና እየተከተለ መሆኑን ለመተንተን የምሁራንን ጥናት መጠበቅ ግድ አይለም፤ ምክንያቱም ለዓመታት የተመለከትነው እውነታ የሚነግረን የአመራሩን እና በዙሪያው የሠፈሩ የጥቅም ተጋሪ ግለሰቦችን ብልፅግና ታሳቢ ያደረገ፣ ከታግሎ መጣል ህግ የተቀዳ፣ የራስ ሀገርንና የራስ ሕዝብን በምርኮ ያስገበረ ፖለቲካ መንበሩን ነው፤ ገብር፣ ገብር፣ ገብር…!!
ዛሬ መንገድ ዳር ረሀብ አዙሮ የጣለው ወንድምህ ስቃይ እንደ ጥላ የሚከተልህ፤ ህፃናት በትምህርት ገበታቸው ላይ በጠኔ ተሸንፈው መመልከቱ የሰርክ አሳዛኝ ክስተት የሆነብህ ከሰው ሰራሽ ችጋር፣ ከሰው ሰራሽ የቀዬ ፍንቀላ፣ ከሰው ሰራሽ እርዛት… የመነጨ መርገምት እንጂ የሰማይ ቁጣ አይምሰልህ፤ እመነኝ መለስም ሆነ ተተኪዎቹ ስኬት አድርገው የሚሰብኩትም ይህንን ነው፤ ‹ሀገር አቀናን!› የሚሉትም ይህንን ነው፤ ሰሞኑን የሚያሰለቹህ ተረኛ ምሁራንም ‹‹ትምህርትና ጤናን በተመለከተ መለስ ‹እልል› የሚያስብል ሥራ ሰርቷል›› የሚሉህ ጣራና ግድግዳ እየቆጠሩ ነው፤ ይህ አይነቱ መደዴ ሙገሳም ለፕሮፓጋንዳ የሚሆን ሪፖርት ለማዘጋጀት ከሚረዳ ቁጥር የዘለለ አበርክቶ አንደማይኖረው አትዘንጋ፡፡

Monday, August 26, 2013

ሕወሐት በአዜብ ጉዳይ ተወጥሯል (ኢየሩሳሌም አርአያ)


August 25, 2013

ከኢየሩሳሌም አርአያ
ለስድስት አመት ኤፈርትን ሲመሩ የቆዩት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ከሃላፊነት መነሳት ተከትሎ በሕወሐት ውስጥ ውጥረት መንገሱን ምንጮች አመለከቱ። የኤፈርት ቦርድ ሰብሳቢ በነበሩት ባለቤታቸው አቶ መለስ አማካይነት ዳይሬክተር ተደርገው አዜብ መሾማቸውን ያስታወሱት ምንጮች፣ ከመለስ ሕልፈት በኋላ ቦታውን የተረከቡት ኤርትራዊው ቴዎድሮስ ሃጎስ መሆናቸውን፣ እንዲሁም ዳይሬክተር የመሾምና የመሻር ስልጣኑ የቦርዱ መሆኑን ያስረዳሉ። አዜብ ከኤፈርት እንዲወገዱ የተደረገው ግን በነቴዎድሮስ ሃጎስ ሳይሆን ስብሃት ነጋ ባቀነባበሩት ጣልቃ ገብ ውሳኔ መሆኑን ምንጮቹ ገልፀዋል። በኤፈርት የተለያዩ ተቋማት የሚሰሩ ሰራተኞች አዜብ በመባረራቸው ደስታቸውን እየገለፁ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮች፣ አያይዘውም ደስታቸውን በስብሰባ ጭምር ከመግለፅ ባለፈ፥ « አዜብ ከኤፈርት ጀምሮ ለፈፀሟቸው የሙስና ወንጀሎች በሕግ መጠየቅ አለባቸው» በማለት አቋም እስከ መያዝ መድረሳቸውን አስታውቀዋል። ከዚህ በስተጀርባ በበቀለኝነታቸውና የጥፋት ሴራ በማቀነባበር የሚታወቁት ስብሃት ነጋ እንዳሉበትና ከኤፈርት ስልጣናቸው ያስነሷቸውን አዜብ ከጨዋታ ውጭ ከማድረግ ባለፈ በሙስና እንዲጠየቁ በየአቅጣጫው ጫና እያሳደሩ መሆኑን ምንጮቹ አስረድተዋል። በአዜብ ተፈፀሙ ተብለው ከተነሱት የሙስና ወንጀሎች በኤፈርት ስም 200 ከባድ ተሽከርካሪዎች አቶ ነጋ ገ/እግዚያብሄር ቀረጥ ሳይከፍሉ እንዲያስገቡ ማድረጋቸውን፣ በሚሊዮን የሚገመት ቀረጥ ሊከፈልባቸው የሚገቡ የተለያዩ የሕክምና መሳሪያዎች፣ በኤፈርት ገንዘብ ሶስት መርከብ ስሚንቶ የፍራንኮ ቫሉታን ሕግ በመተላለፍ ቀረጥ ሳይከፈልበት አገር ውስጥ መግባቱ፣ ክሶች እንዲቋረጡ ትእዛዝ በመስጠት..የሚሉት በዋነኛነት መነሳታቸውን ምንጮቹ አመልክተዋል። ( አዜብ ከኤፈርት እንደሚነሱ ከዚህ ቀደም በወጡ ዘገባዎች ምንጮችን በመንተራስ መገለፁ ይታወሳል)

“የኢትዮጵያውያን ህይወት በዓረብ ሀገሮች”


የልማታዊ ጋዜጠኞች አንዝህላልነት እና የአብርሃ ደስታ እማኝነት

eth women


ባሳለፍነው ሳምንት በሳውዲ አረቢያ ግፍ ተፈጸሞባቸው ወደ ባገር ቤት የሚሸኙ እህቶች የመኖራቸው መረጃ ደረሰኝ። በተለይም በቅርብ እከታተላቸው የነበሩ አህቶች እንግልት በመጠቆም በዚው በፊስ ቡክ የማለዳ ወግ ዳሰሳየ ላይ አንድ መልዕክት አስላልፊ ነበር! መልዕክቱም ለልማታዊ የሃገር ቤት ጋዜጠኞች ሲሆን የመልዕክቱ ፍሬ ሃሳብ “የምንናገረውን ማመን መቀበል አቅቷችሁ እንደ ጠላት ከምታዩን ረቡዕ ወደ ቦሌ አየር ማረፊያ ሂዱና ከፍተኛ ግፍ ተፈጸደሞባቸው ከሳውዲ ተጠርፈው ወደ ባገር የሚገቡትን የኮንትራት ሰራተኞችን ተመልክቱ !” የሚል ነበር።
ንቁ እዝነ ልቦንና ያልታደሉት ልማታዊ ጋዜጠኞች በቦታው ሄደው ከቤሩት የተመለሱትን ሻንጣ የደረደሩ እህቶች በቴሌቪዥኑ መስኮት ብልጭ አድርገው ከማጥፋታቸው ባለፈ ከሳውዲ ያለጫማና የረባ ልብስ ተደብድበውና ተደፍረው የተመለሱትን ግፉአን ሊያሳዩን እንኳ አልፈቀዱም! ጋዜጠኞቻችን አልተሳሳቱም!!! የተሳሳትኩት እኔ ነኝ!!! ያን ሰሞን “ስደት ይቅር” ምንቴስ ሰፊ ሽፋን በየሚዲያው እየሰጡ፣ የደበቁትን መከራችን እያሳዩ እያሉ ህዝበ አዳም፣ ሃገሬውን ሲያስለቅሱን የከረሙት ወደ ነፍሳቸው ተመልሰዋል ብየ በማሰቤ ስህተቱ የእኔ ግምት ነው!!! ጉዳታችን እዩት ቀሪው እንዲማርበት ፣ ሃላፊዎቻችን ይዩትና ወደ ዘነጉት የዜጎች ጉዳይ ያተኩሩ ዘንድ የተገፊ ግፉአኑን ጉዳይ ተከታትየ መጠቆሜ በአደባባይ ቃል የገቡትን ይፈጽማሉ ብየ በማሰቤ የተሳሳትኩት እኔ ነኝ!!! ስህተቴ አንድና አንድ ነው!!! የአረብ ሃገሩን የስደት መከራ የሚፈልጉት ለፕሮፖጋንዳ እንጅ ቀሪውን ማስተማርን እንደልሆነ አለማሰቤ ነው ስህተቴ!
በእንዝህላል ልማታዊ ጋዜጠኞቻችን አዝኘም ብቻ ሳይሆን አፍሬ ዝም ማለቴ ግን እውነት ነው! ዛሬ ማለዳ ግን መልካም መረጃም የሚየ ስፈነጥዝ ባይሆንም መረጃው በመሰራጨቱ የተደሰትኩበትን መጣጥፍ ተመለከትኩ። ሮብ ነሓሴ 15, 2005 ዓም ከአረብ ሃገር ወደ ሃገር የገቡትን እህቶች አብርሃ ደስታ አግኝቷ እንዳነጋገራቸው በማህበራዊ ድህረ ገጽ ካስተላለፈው መልዕክት ለመረዳት በመቻሌ ደስ አለኝ! በገዥው የኢህአዴግ መንግስት አስተዳደር ላይ በተለይም ስለ ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ከመቀሌ ሆኖ በሚያሰራጫቸው የሰሉ ሚዛናዊ ሂሶች ተወዳጅነትን እያተረፈ የመጣው አብርሃ ድስታ ግፉአን እህቶቸችን ቦሌ አየር ማረፊያ አግኝቷቸው ያየውን የሰማውን እጥር ምጥን ባለው የለመድነው መረጃ አቀባበል እንካችሁ ብሎናል። የአብርሃ እማኝነት አስደስቶኝ እኔም ለዛሬ ወግ ዳሰሳ አበቃሁት!

The Totolamo-Kofele blood bath victims named, death toll still climbing.


(Getahune Bekele-South Africa)

Totolamo-Kofele


“Wolahi, Wolahi…” swears 85 year old Totolamo village barley farmer and cattle herder Hajji Abdinur Shifa when a reporter asked him if he know  any terrorist hiding in his village. His face looks like a paint of sorrow and grief. His wife affectionately called by the villagers, Adiyo, was too fragile to talk about the August 3 2013 blood bath that turned their agriculture and livestock rich village into an inferno.
“My son took three bullets and died a day later at Sashemene general hospital. The body that was weakening by fasting could not respond well to treatment and he succumbed to his wounds without saying goodbye. His killers (federal police commandos) did not allow us entry to the hospital. My son Abdulkarim is dead but he will live in my heart until I join him in paradise…,” the respected elder said wiping his tears with a piece of garment