Wednesday, January 30, 2013
Tuesday, January 29, 2013
እግርኳሳችን የራሷን ሙሴ ትፈልጋለች
January 29, 2013 04:58 am By Editor Leave a Comment
ስሜት ጎርፍ ነው፤ ያውም ደራሽ ጎርፍ፤ ብሄራዊ ቡድናችንን ስንደግፍም ሆነ ስናወድስ እንዲሁም ስንወቅስ በዚሁ ደራሽ ጎርፍ መወሰዳችን ይታያል። ይሄ ችግር ግን እንደ ሃገርም ችግራችን እየሆነ የመጣ ነገር ነው በስሜት መደገፍ በስሜት መቃወም፤ ዛሬ ያወደሱትን ነገ መርግም ሁሉንም ነገር በዘላቂ ጥቅም፤ በዘላቂ ስራ እና በዕውቀት መመዘን እያቃተን ነው። ከዚያም ዐልፎ ስሜታችን ጫፍ ላይ በሚደርስበት ጊዜ ሰከን ብሎ የሚያስብ ሰው ሲያጋጥመን እንደጭራቅ እንመለከተዋለን። ከእኛ በሓሳብ የተለየ አስተያየት የሰጠ እንደሆነማ በቃ ቤተክርስቲያን ውስጥ የገባ ውሻ እናደርገዋለን።…
የሰሞኑ የብሄራዊ ቡድናችን ውጤትም የዚህ ጎርፍ ሰለባዎች መሆናችን አንዱ ማሳያ ነው። መጀመሪያ ላይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አዲስ አበባ ከቤኒን ብሄራዊ ቡድን ጋር ሲጫወት አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው የአሰላለፍ ስህተት ሰርቶአል መሃል ላይ ምንም ፈጣሪ /creative/ ተጫዋች አልነበረውም በሚል ከውጤቱ በኋላ ህዝቡም ጋዜጠኞችም ሲያወግዙት ከረሙ። ልብ አድርጉ እዚህ ጋር ሁሉም የሚያወራው በስሜት የዕለቱን ጨዋታ በተመለከተ የነበረውን ችግር እንጂ በዕውቀት የሃገራችን እግርኳስ ችግር ምንድን ነው? ብሎ ስለዘለቄታው የሚያወራ እና የሚያስብ የለም። ፌደሬሽኑም ቢሆን ህልውናውን ከጊዜያዊ ውጤት ጋር አጣብቆ የተቀመጠ ስለሆነ ዘለቄታዊ ስራ ሲሰራ አይታይም እናም አቶ ሰውነት ያቺን የተችት ፍላጻ እንደምንም ሽል ብለው አሳለፏት ። …
ቀጥሎም ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ሱዳንን አሸንፈን ለአፍሪካ ዋንጫ አላፊ መሆናችንን አረጋገጥን፤ ስሜት አሁንም እንደደራሽ ጎርፍ አጥለቀለቀን ህዝቡ ”ሳላዲን ጥቁር ሰው” ተባለ። ሲሰደብ የነበረው ሰውነት በየኤፍኤም ራዲዮው ጋሼ ጋሼ መባል ተጀመረ። አንዳንዶቹም ኢትዮጵያዊው ሞሪኖ ይሉት ጀመር። አሁንም እዚህ ጋር ረጋ ብሎ በዕውቀት ይሄ ውጤት ጊዜያዊ ነው፤ ዘለቄታዊ ውጤት የምንፈልግ ከሆነ ሰከን ብለን የእግርኳሱን ችግር እንመልከት በስሜት አንነዳ የሚል ሰው ሲገኝ እንደከሃዲ ሃገሩን እንደማይወድ ተቆጥሮ መወገዝ ጀመረ በስሜት! አቶ ሰውነትም ይህቺን ስለሚያውቅ በሴካፋ ውድድር መሳተፋችን አስፈላጊ አይደለም ብሎ ራሳችንን ከሴካፋ ውድድር እንድናገልል አደረገ። ለምን? ምክኒያቱም ስሜታዊ መሆናአችንን ስለሚያውቅ በሴካፋ ላይ የሚመጣው ውጤት የእርሱን ከብሄራዊ ቡድን ጋር ቆይታ ስለምትወስን ቁማሩን መቆመር አልፈለገም። አዎ ስራዎች በዕቅድ እና በዕውቀት ሳይሆን በስሜት በሚሰሩበት ሃገር ለምን ሪስክ ይወስዳል? …
Saturday, January 19, 2013
አሜሪካ በአፍሪካ ወታደራዊ የበላይነቷን ልታረጋግጥ ነው!
ፕሮግራሙን ለማስፈጸም 35 አገሮች ተመርጠዋል
አዲስ በተያዘው የአውጳውያን ዓመት አሜሪካ በአፍሪካ ከፍተኛ ወታደራዊ የበላይነትን ሊያረጋግጥላት የሚችል ፕሮግራም ነድፋለች፡፡ ከሦስት ሳምንታት በፊት ይፋ የሆነውን ፕሮግራም ተግባራዊ ለማድረግ በሚያስችል ሁኔታ ላይ የተነደፈውን ዕቅድ የሚያስፈጽሙ 35 የአፍሪካ አገሮችም ተመርጠዋል፡፡
ምንም እንኳን ዜናው ይፋ ከሆነ የቆየ ቢሆንም የአሜሪካንን የመከላከያ ሚኒስቴር (ፔንታጎን) እንዲመሩ የታሰቡት ሪፓብሊካኑ ቸክ ሔግል ቀዳሚ ተወዳዳሪ መሆናቸው እስከሚገለጽ ድረስ የብዙዎችን ቀልብ አልሳበም ነበር፡፡ የአሜሪካንን ጦር ሠራዊት በየአገሩ በማዝመት ጉዳይ ላይ ጽኑ የተቃውሞ አስተሳሰብ የሚከተሉት ሔግል እንዲህ ዓይነቱን ፕሮግራም ለማስፈጸም ገጣሚ ሚኒስትር እንደሚሆኑ በሰፊው እየተነገረ ነው፡፡
የመከላከያ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ይፋ እንዳደረገው በአፍሪካ በየጊዜው እያገረሸ የሄደውን የአሸባሪዎች እንቅስቃሴ ለመቆጣጠርና ሌሎች በክፍለ አህጉሩ የሚነሱ ቀውሶችን ለመከላከል የሚል ዕቅድ የወጣለት ፕሮግራም በያዝነው የአውሮጳውያን ዓመት ተግባራዊ ይሆናል፡፡ ይህ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነው ፕሮግራም የሚያተኩረው ጦርነት ወይም ሁከት በተፈጠረ ጊዜ የአሜሪካንን ወታደሮች በየቦታው ከመላክ ይልቅ አፍሪካውያንን ለራሳቸው ችግር ወታደራዊ ዕርምጃ ለመውሰድ እንዲችሉ የሚያደርግ ነው፡፡ ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ እንዲያስችል የአሜሪካ ወታደራዊ መኮንኖች ለአፍሪካውያኑ የተለያየ ወታደራዊ ሥልጠና ለመስጠት ወደዚያው ያመራሉ፡፡
Wednesday, January 16, 2013
“በ2030 ከሚከሽፉ መንግሥታት አንዷ ኢትዮጵያ ነች”
ዘገባው የ15 አገራትን ዝርዝር አውጥቷል
January 16, 2013 09:29 am By Editor 1 Comment
የአሜሪካ የብሔራዊ የደኅንነት ምክርቤት እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር በ2030 የሚከሽፉ 15 መንግሥታትን (failed states) ዝርዝር አውጥቷል፡፡ “በግጭት መብዛትና በአካባቢ ጥበቃ ቀውስ ምክንያት” ይከሽፋሉ ተብለው ከተተነበዩት የአፍሪካ፣ የእስያና የመካከለኛው ምስራቅ አገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ነች፡፡
እጅግ የነጠረ፣ ያልተዛባና የተጠና ዘገባ ለአሜሪካ የስለላ ተቋማት፣ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አውጪዎችና ለዓለምዓቀፍ ግንኙነት ተመራማሪዎች በማውጣት የታወቀው የአሜሪካ ብሔራዊ የደኅንነት ምክርቤት ከተቋቋመ በርካታ ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ ምክርቤቱ በሚያወጣቸው ዘገባዎች የአሜሪካ መንግሥትም ሆነ የተለያዩ መ/ቤቶች ተጽዕኖ እንደማያደርጉበት የሚናገር ሲሆን፤ ዘገባዎቹንም ከአድልዎ እና ከአሜሪካ መንግሥት አቋም ነጻ በመሆን እንደሚያዘጋጃቸው ይናገራል፡፡
የም/ቤቱ ዘገባ በተለይ ምርጫ ከተካሄደ በኋላ ለመጪው ፕሬዚዳንት የወደፊቱን የዓለማችን መልክ ምን እንደሚመስል የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ አስተሳሰቦች እና ዓለምአቀፋዊ ዝንባሌዎች ላይ አቅጣጫ የሚጠቁም ትንበያ ያደርጋል፡፡ ለፕሬዚዳንቱ ዓለምአቀፋዊ የደኅንነት ዘገባ ያቀርባል፤ ለብሔራዊ የጸጥታ ምክርቤት እና ለአገር ውስጥ ደኅንነት መ/ቤት ምክር ያቀብላል፤ በአጠቃላይ የአሜሪካን የስለላና የደኅንነት ማኅበረሰብ ሊከተል በሚገባው ጉዳይ ላይ አቅጣጫ የሚያስይዝ ሃሳብ ያቀርባል፡፡
በዚሁም መሠረት ባለፈው የታህሳስ ወር “በ2030 የዓለም አቅጣጫ፡ አማራጭ አገራት” በሚል ርዕስ አንድ ዳጎስ ያለ ጥናት አቅርቧል፡፡ ይኸው 160ገጽ ያለው ዘገባ የዛሬ 17ዓመት የዓለማችን ገጽታ ምን እንደሚመስል ከየአገራቱ በተወሰደ ጥናትና እዚያው በሚገኙ ተመራማሪዎች የሰበሰበውን ያካተተ ነው፡፡ ዓለማችን የምታዘነብልባቸው ቀዳሚ ሁኔታዎች አንዱ ሰዎች በራሳቸው አነሳሽነት ድህነትን ለመቀነስ፣ በትምህርት ለማደግ፣ በቴክኖሎጂና በህክምና ለመራቀቅ እንዲሁም በገቢም የመካከለኛው መደብ ላይ ለመድረስ የሚያደርጉት ጥረት በከፍተኛ ሁኔታ ከተጠቀሱት አንዱ አቅጣጫ ጠቋሚ ነው፡፡
Friday, January 11, 2013
“በህወሓት ተወርረናል!” ደቡብ ሱዳኖች
ኃያልነታችን ብሔራዊ ይሁን
January 11, 2013 07:55 am By Editor 3 Comments
አዲሷ አገር ደቡብ ሱዳን እንደ መንግሥት ተመቻችታ አልቆመችም። የፋይናንስ ስርዓቱም የተረጋጋ አይደለም። የገቢና ወጪ ቁጥጥሩ ክፍተት ያለበት በመሆኑ ለሙስና የተጋለጠ ነው። የጁባ ነዋሪዎች እንደሚሉት ከሆነ የአገሪቱ ሃብት በግለሰቦች እጅ ነው። በተለያዩ መስኮችም የባለሙያና የአቅም ችግር አገሪቱ ምስጢርና የኔ የምትለው አስተዳደር እንዳይኖራት አድርጓታል የሚሉ በርከቶች ናቸው።
ይህንኑ ክፍተት ለመሙላት በሚል ኢህአዴግ ደቡብ ሱዳንን ከተወዳጀ ጀምሮ ከፍተኛ ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል። የመከላከያ መኮንኖችን አሰልጥኗል፤ የፖሊስ ኃይሉን አደራጅቷል። በአማካሪነት በተለያዩ ዘርፎች የራሱን ሰዎች ጠቅጥቆ አሁንም ይህንኑ ድጋፉን አጠናክሮ ቀጥሏል። የተመሰረተው ግንኙነት ወደፊትም እንዲሁ በቀላሉ ንፋስ የሚገባው አይመስልም። ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው እንደሚሉት ኢህአዴግ በህወሃት አማካይነት ደቡብ ሱዳንን ጠፍንጎ የያዘበት ሰንሰለት በቀላሉ ሊበጠስና ሊሸረሸር የሚችል እንዳልሆነ ይናገራሉ።
ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ እነዚሁ በጁባ የሚኖሩ ክፍሎች በፋይናንስ፣ በፖሊስ፣ በመከላከያ፣ በደህንነት፣ በተለያዩ ከፍተኛ ግዢዎችና በገንዘብ ዝውውር በኩል የደቡብ ሱዳን ማናቸውም እንቅስቃሴ ከኢህአዴግ እይታና ክትትል ውጪ አይደለም። እንደ አገር ኢትዮጵያ በቀጠናው ኃያል መሆኗ ቢያስደስትም አሰራሩ “ህወሃት በኢትዮጵያ ስም፣ የህወሃት ልጆች በኢህአዴግ ስም” መከናወኑ ቅሬታ ፈጥሯል።
“ብሔራዊ ጥቅምን በብሔራዊ አጀንዳ ማስጠበቅና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ማስኬድ ኩራቱ የሁሉም ዜጎች እንዲሆን ያደርገዋል” የሚሉት ክፍሎች በተግባር የሚታየውና በብሔራዊ ስም የሚከናወነው ስራ “ህወሃትና የህወሃት ሰዎች በብቸኛነት እንዲጠቀሙበት የሚያደርግ ነው፤ ሕዝብ የወከለውና የራሱን አገር ጥቅም የሚያስከብር አስተዳደር በኢትዮጵያ ላይ እስከለሌለ ድረስ አካሄዱን ብሔራዊ ወይም የአገር ኩራት ለማለት አይቻልም” ብለዋል። አያይዘውም ኃያልነታችን በብሔራዊ ደረጃ እንጂ በድርጅትና በጎሣ ደረጃ መሆን የለበትም በማለት ይከራከራሉ፡፡ ሲያስረዱም በብሔራዊ ሽፋን ለመበልጸግ የሚደረግ ሩጫ ዓቅምን ካላገናዘበው የኤርትራ ፍላጎትና በውጤቱም ከጎረቤት ሁሉ ጋር ከጠብ እስከ ዓይነቁራኛ መተያየት ከመድረስ ጋር ልዩነት አይኖረውም ይላሉ፡፡
ከ33ቱ የአዳማ ፔቴሽን ፈራሚ ፓርቲዎች የተሰጠ መግለጫ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫውን ሂደት እየገፋ ያለው ለገዢው ፓርቲ ብቻ በተመቻቸ ሜዳ ነው!
January 10, 2013 04:33 pm By Editor Leave a Comment
በምርጫ አስፈፃሚው፣ ከምርጫ አስተዳደርና በምርጫው ሂደት ላይ የሚታዩ መሠረታዊ ችግሮችን በማንሣት ችግሮቹ ስለሚፈቱበት መንገድ የውይይት /ምክክር/ መድረክ እንዲመቻች ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድና ለመንግሥት አካላት ጥያቄአችንን ማቅረባችን ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የማያሣምኑ ምክንያቶች በመስጠት ጥያቄዎቻችንን ሙሉ በሙሉ ውድቅ ማድረጉን በቃል የገለፀልን ሲሆን ለመንግሥት ላቀረብነው ጥያቄ ምላሹን እየተጠባበቅን ነው፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የተጣለበትን የአገርና የሕዝብ ኃላፊነት ወደጐን በመግፋት ምርጫውን ሠላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊ፣ ነፃና ፍትሐዊ ምርጫ ለማድረግ የመወዳደሪያ ሜዳውን ከማስተካከል ይልቅ የገዢው ፓርቲ ወገንተኝነቱንና ጉዳይ ፈፃሚነቱን ባረጋገጠበት አቋሙ በመግፋት ወደ ምርጫ እንቅስቃሴ መግባቱን በይፋ አውጇል፡፡
እኛ በያዝነው ሠላማዊ የትግል መሥመር በምርጫ የመሣተፍ /አለመሳተፍ ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ያለመሆኑንና የሕዝብ ዘርፈ ብዙ ውስብስብ ጥያቄዎች ምላሽ የምንሰጥበት ብቸኛው የመንግሥት ሥልጣን መያዣ መሣሪያችን መሆኑን በተደጋጋሚ በግልጽ አስቀምጠናል፡፡ የአካባቢ ምርጫ ወደ ሕዝቡ ዘልቆ ለመድረስ የሚያስችል እንደመሆኑ ከአገር አቀፍ ምርጫ ያነሰ ትኩረትና ቦታ የምንሰጠው አይደለም፡፡ ይልቁንም ለምንፈልገው የሥርዓት ለውጥና የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ መሠረቱ የሚጣለው በሕዝቡ ውስጥ ስለሆነ ለዚህ ምርጫ ተገቢውን ትኩረት ሰጥተን ጠንክረን ለመንቀሳቀስ ዝግጅታችንን በተባበረና በተቀናጀ መንገድ ለማድረግ እየተንቀሳቀስን ባለንበት ነው የጋራ ጥያቄዎቻችንን ያቀረብነው፡፡ ይሁን እንጂ ምርጫ ቦርድ በኢህአዴግ እየተመራና እየታገዘ ከጊዜ ሰሌዳ በፊት በመሠረታዊ ጉዳዮች ላይ መወያየት ይቅደም በማለት 41 የፖለቲካ ፓርቲዎች በአዳማው ስብሰባ ላይ ላቀረብነው የቦርዱ ሰብሣቢ “የውይይት መድረክ ይዘጋጃል” በማለት የመለሱትን፣ እንዲሁም 33 በሕጋዊና ሠላማዊ መንገድ የምንታገል የፖለቲካ ፓርቲዎች ፔቲሽን ፈርመን ላቀረብነው የቦርዱ ጽ/ቤት ኃላፊ “ባትጠይቁንም ማድረግ ያለብን ነው” “. . . ጉዳዩን ሣታጮሁት በትዕግሥት ጠብቁ” ማለታቸውን ክደው ከአዳማ በተመለሱ በ4ኛው ቀን አፀደቅን ባሉት የጊዜ ሰሌዳ ገፍተውበታል፡፡
Thursday, January 10, 2013
ይድረስ ለፈጣሪ!
(አሥራደው ከፈረንሳይ)
ተጣፈ ተኔ «ወተህ ወርደህ የላብህን ወዝ ትበላለህ» ብለህ ወደ መሬት ከላከው የአዳም የልጅ፤ ልጅ፤ ልጅ፤ ልጅ፤ ልጅ፤ … አንዱ፤ ላንተ በሰማዬ ሰማያት ላለኸው አምላክ::
እነሆ ይችን ደብዳቤ በመልክተኛህ በመላኩ ገብርኤል በኩል ላንተ ስልክ፤ ካገኘህ ለራስህ በእጅህ እንዲሰጥ፤ ካጣህም ለእናትህ ለወላዲት አምላክ፤ እንዲሰጣትና እሷ እንድትሰጥህ አደራ ብዬዋለሁ::
አምላክ ሆይ !
ከጭቃ አድቦልቡለህ የፈጠርከው ሰውን ያህል ጨካኝ ፍጡር አንቱ እያልኩ፤ አንተን አንቱታ በመንፈጌ ከድፍረት እንደማትቆጥርብኝና ቁጣህ እንደማይበረታ አውቃለሁ፤ አንተታዬ የመውደዴና ላንተ ያለኝ የክበር መግለጫ መሆኑን አንተው ታውቃለህና!
ይኸውልህ ጉዳዩ እንዲህ ነው:
ፈጣሪ በጆሮው ላይ ተኝቶ የሕፃናትን ለቅሶ፤ የዕናቶችን ዋይታ፤ ያባቶችን ጣር፤ አልሰማ ብሏል፤ … ሕዝብ መከራው በዝቶ፤ የበደል ገፈቱ ገንፍሎ እየፈሰሰ፤ ዋይታውና ለቅሶው እንደ እሳተ ጎሞራ ላንቃውን ከፍቶ፤ የሰማዩን በር ሲለበልብ፤ ጮኸት በርክቶ፤ ፈጣሪ አልሰማ አለ::
Subscribe to:
Posts (Atom)