August 9, 2013
ዳኛቸው ቢያድግልኝ
አረም ማለት ያልተዘራበት የሚበቅል ገበሬ የዘራውን ሰብል የሚሻማ፣ ውሀውን የሚጠጣበት፣ ለበሽታና ተባይ መጠለያ በመሆን ለሰብል ጉዳት ምክንያት የሚሆን እጽዋት ማለት ነው። አረም በስሮቹ አማካይነት የሰብሉን ስር አንቆ የሚገድል፣ አንዳንዱም እንደ ፓራሳይት ሰብል ላይ ተጣብቆ የሚበቅል እንደ አቀንጭራ ያለ ማለት ነው። አረሞች በፈጣን አስተዳደጋቸው ሳቢያ አልሚ ንጥረ ነገሮችን ከመሬት የፀሀይ ብርሃን ከሰማይ በመሻማት የሚያቀጭጩና የሚገድሉ ናቸው። የስንዴ ማሳ ውስጥ የበቀለ በቆሎም እንኳ ቢሆን አረም ነው፣ ገብስም ቢሆን አረም ነውና ተነቅሎ ይጣላል።
አረም ዘሩን በማባዛትና የመኖር እድሉን ለማራዘም በርካታ ዘዴዎችን እየተጠቀመ በብዛት የሚንሰራፋና በወቅቱ ካልታረመ ሰብል የሚያጠፋ ነው። ጎበዝ ገበሬ አርሞና ኮትኩቶ ሰብሉን ካልተንከባከበ በሰብል ምርት ምትክ አረሙን ማፈስ ይገደዳል። ልክ እንደ ምሳሌው ኢትዮጵያዊነትን የሰው አረም ውጦታል። ፀረ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት አቋምን የያዘ በሌሎች ስም ይልቁንም በትግሬ ስም ኢትዮጵያዊነት ላይ ተጣብቆ አገር እያፈረሰ ያለ የዘራፊ ቡድን አገርና ሕዝብ እያቀጨጨ ነው። ወያኔ በቆሎና ማሽላ ላይ ተጣብቆ እንደሚበቅል አቀንጭራ (ፓራሳይት፣ ጥገኛ አረም) ኢትዮጵያዊነትን ተጣብቶ ኢትዮጵያን እየገደለ ያለ ቡድን ነውና ተነቅሎ መጥፋት አለበት። በምስሉ የተቀረጹ ‘ኦፖርቹኒስት’ ገንጣዮችና ከፋፋይ ድርጅቶችም እንዲሁ።