Friday, June 14, 2013

ይድረስ ለአባይ ባለበት… (ከአቤ ቶኪቻው)


June 13, 2013
አቤ ቶኪቻው
ጉዳዩ፤ በጣም አበዛኸው…!

Abe Tokichaw's letter to Abbay (Nile) River.
ይቺ ለአባይ የተፃፈች ደብዳቤ ናት፡፡ አፃፃፏ “ስዲ ወ ግጥሚ” አይነት ናት፡፡ ትንፋሽ ያለው ሰው እንደ ግጥም ቢወርዳት ግጥም ግጥም ትመስላለች፡፡ ትንፋሽ የሌለው ሰው ደግሞ እንዲሁ ቢዘልቃት ስድ ንባብ ትሆናለች፡፡ እስቲ እንደዚህ አዳዲስ ፈጣራዎችን እናስተዋውቅ… ብዬ አካብጄ በአዲስ መስመር እጀምራታለሁ ትድላችሁ…!!
ውድ አባይ፤ ከእናታችን ማህጸን ተገኝተህ ገና በቅጡ ሳትጠና እና ሳትጠናና በልጅነት አፍላ ፍቅር ድንገት አየተሃት ከወደድካት ግብጽ ጋር ከተጋባህባት ዕለት አንስቶ ለጤናህ እንደምን አለህ… ከቶ!
እኛስ እንዳለን አለነው፡፡ አንተን ያኽል ወንድም፤ አንተን ያኽል አጋር፤ ውጪ ሀገር የሚኖር ታላቅ፣ እጅግ ታላቅ፣ ሃብታም የናጠጠ፤ ጥሩ ስርፋ ደህና ቦታ ይዞ የተቆናጠጠ፤ ዘመድ ቢኖረንም ዛሬም አልጠገብንም፡፡ ዛሬም አልወዛንም፡፡ ዛሬም አልወፈርንም፡፡ እንዲሁ እንደቀጠን፣ እንዲሁ እንደራበን፣ አመድ እንደመሰልን አለን አባይ፡፡ እንዲሁ አለን፡፡

Wednesday, June 12, 2013

አባይ የፖለቲካ ግለት ማብረጃ ወይስ?


June 12, 2013
ጥላሁን ዛጋ
አባይ መነሻ ምንጩን ሰሜናዊ የኢትዮጵያን ክፍል በተለይም ጣና ሃይቅንና በዙሪያው ያሉ አፍላጋት አድርጎ ረጅም ጉዞውን ጣና ሃይቅ ላይ በሚፈጥረው ንብርብሮሽ የአለምን ህዝብ በሙሉ አስደምሞ ይጀምራል፣ እግረ መንገዱን ሌሎች ገባር ወንዞችን በጉያው ሸክፎ እስከሜዲትራኒያን ባህር ያለውን በማይልስ የሚቆጠረውን የርቀት ጉዞ ይቆርሰዋል፣ በ75᎖912 ስኩዌር ኪሎሜትር የተፋሰስ ስፋትና በ23᎐6 ቢሊየን ሜትርኪዩብ አመታዊ አማካይ የፍሰት መጠን ጋምቤላንና ሌሎች የኢትዮጵያን ሰሜናዊ ክፍሎች የሚያዳርሰው ባሮ ወንዝ እንዲሁም በ82᎖350 ስኩዌር ኪሎሜትር የተፋሰስ ስፋትና በ9.6 ቢሊየን  ሜትር ኪዩብ አመታዊ አማካይ የፍሰት መጠን ከላስታ ተራሮች ተነስቶ ወደምዕራብ በመፍሰስ እንደገና አቅጣጫ ቀይሮ ወደ ሰሜን የሚመለሰው የተከዜ ወንዝ በአባይ ጉያ የሚሸከፉ ዋናዎቹ ገባሮች ናቸው።
በመሆኑም አባይ ይህን የታላቅነት ግርማውን እንደያዘ ያለከልካይ ለዘመናት ሲፈስ የኖረና የህብረ-ኢትዮጵያዊነት መገለጫ እንዲሁም የሁሉንም ብሔር-ብሔረሰቦች ስሜት በአንድነት የሚነካ የኢትዮጵያ ወንዝ ነው። እንደየክፍለዘመኑ እንዲሁም  ማህበረሰባዊ የእውቀትና ብስለት ደረጃ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ያወያየ፣ ያነጋገረና ያከራከረ ስሜት ቀስቃሽና የሀገር ወዳድነትም መገለጫ ሆኖ ለዘመናት የዘለቀ ወንዝ ነው፣ በተመሳሳይም በሀገራችን በተለያዩ ጊዜያት የተነሱ መሪዎች ለፖለቲካቸው ውበት ማድመቂያ እንዲሁም ለኢትዮጵያዊነታቸው መሃላ ማህተም ሆኖላቸው ቆይቶአል።

Saturday, June 8, 2013

ኢህአዴግ ጣና በለስን ለምን አፈራረሰው?


"በሩ ይከፈት፣ በአባይ ጉዳይ አገራዊ አቋም እንያዝ"

BELES inlet
June 8, 2013 02:31 am By  Leave a Comment
በግብጽ ረዳትነት፣ በሱዳን መሪነት መንግስት ለመሆን የበቃው ህወሃት/ኢህአዴግ ግዙፉን የጣና በለስ ፕሮጀክትና ንብረቱ እንዲዘረፍ ያደረገበትን ምክንያት በማንሳት መከራከር እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ። የግብጽ ፕሬዚዳንት ሙርሲ እንዳደረጉት በአገር ጉዳይ ሁሉንም ያሳተፈ ግልጽ አቋም እንዲያዝና አጋጣሚውን በመጠቀም ብሔራዊ ህብረት እንዲፈጠር ኢህአዴግ በሩን ሊከፍት እንደሚገባ ተገለጸ።

በተለያዩ ጉዳዮች ምክንያት ስማቸው እንዳይጠቀስ በማሳሰብ ለጎልጉል አስተያየት የሚሰጡት የኢህአዴግ ሰው እንዳሉት በርካታ ጉዶች ያሉበትን የአባይን ግድብ ተከትሎ ከግብጽ ጋር የተነሳው ውዝግብ አስቀድሞ የሚታወቅ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ስልትና ውጤት ነው።

አሁን ድረስ አገር እየመራ በነጻ አውጪ ስም የሚጠራው ህወሃት/ኢህአዴግ አዲስ አበባ ሲገባ “ዲሞክራሲ አመጣሁ” በማለት ኢትዮጵያን መምራት እንደጀመረ የሚያወሱት የኢህአዴግ ሰው፤ አቶ መለስ ብቻቸውን ይነዱት የነበረው ኢህአዴግ እንደፈለገ ቆዳውን እየቀያየረ የተጠቀመበትንና በእስስት በመመሰል “ከሽፏል የሚሉትን” ስልት ያብራራሉ።

በዲሞክራሲ ስም የተጀመረው የኢህአዴግ አገዛዝ ቆየት ብሎ “ልማታዊ ነኝ፣ ልማት ግቡን የሚመታው በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ቀመር ነው” በማለት ፕሮፓጋንዳውን አሰፋ። የልማት ህልመኛነቱ ሲነቃበት “የትራንስፎርሜሽን ዘመቻ” በማለት አዲስ የፕሮፓጋንዳ እቅድ ነድፎ ህዝብና አገር ሲያታልል ቆየ። ይህም አላራምድና በህዝብ የመታመን ድል ሊያስገኝለት እንደማይችል ሲታመን “የህዳሴያችን ግድብ” ተብሎ አባይ አጀንዳ እንደተደረገ ያመለከቱት ዲፕሎማት፤ “ኢህአዴግ አገር ውስጥ የሚያምታታባቸው መንገዶች ሲጠናቀቁበት የፕሮፓጋንዳውን ዘመቻ አንድ ደረጃ ከፍ አደርገው” በማለት አሁን ከግብጽ ጋር ስለተጀመረው ውዝግብ አስተያየታቸውን ይጀምራሉ።

Thursday, June 6, 2013

በሰላማዊ ሠልፉ ሰማያዊ ፓርቲና መንግሥት እየተወዛገቡ ነው


selfegnoch
June 6, 2013 08:09 am By  Leave a Comment
ሰማያዊ ፓርቲ ከአንድ ወር በፊት በጠራውና ባለፈው እሑድ የተደረገውን ሰላማዊ ሠልፍ መንግሥት ሲያወግዝ፣ ሰላማዊ ፓርቲ ደግሞ የመንግሥት ውግዘት በተቃውሞ የተነሳውን ሕዝብ ከማሸማቀቅ ባለፈ የሕግ ድጋፍ እንደሌለው እየገለጸ ነው፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ሚያዝያ 29 ቀን 2005 ዓ.ም. ባስተላለፈው የሰላማዊ ሠልፍ ጥሪ፣ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም. በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጐች ወጥተው ተሰተውለዋል፡፡ አራት ኪሎ ቀበና አካባቢ ከሚገኘው የሰማያዊ ፓርቲ ጽሕፈት ቤት መነሻውን ያደረገው ሰላማዊ ሠልፉ በአራት ኪሎ፣ በፒያሳና በቸርችል ጐዳና አድርጐ ኢትዮ ኩባ የወዳጅነት መናፈሻ ደርሶ፣ እስከ ቀኑ ስምንት ሰዓት ድረስ የተለያዩ መፈክሮችንና ተቃውሞዎችን በመንግሥት፣ በመንግሥት መገናኛ ብዙኅንና በአንዳንድ የግል መገናኛ ብዙኅን ላይ አሰምተዋል፡፡

ሠልፈኞቹ ለመንግሥት ካቀረቧቸው ጥያቄዎችና መፈክሮች መካከል፣ ‹‹ዜጐችን ማፈናቀል የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው፡፡ የህሊናና የፖለቲካ እስረኞች በአስቸኳይ ይፈቱ፣ የመደራጀት መብታችን ይረጋገጥ፣ በኑሮ ውድነት የጐበጠው ትከሻችን እረፍት ያስፈልገዋል፣ ሕገ መንግሥትን የሚፃረሩ አፋኝ አዋጆች ይሰረዙ፣ የመንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ መግባትን አጥብቀን እንቃወማለን፣ የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊዎች በአስቸኳይ ይፈቱ፣ ለፍትሕና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መስፈን የሚታገሉ ጋዜጠኞች ይፈቱና አትነሳም ወይ አትነሳም ወይ . . . ወኔ የሌለው የአገረ ሸክም ነው፣ ውሸት ሰለቸን . . . ›› የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

“ይህ መንግሥት አይመጥነንም”


የ“ምርቃና” መግለጫ ለኢህአዴግ ድንጋጤ

shemelis2-
June 6, 2013 08:17 am By  Leave a Comment
ሰሞኑን ኢትዮጵያ የዓለም መገናኛ አጀንዳ ሆናለች። ለዘመናት እጇን ኢትዮጵያ ላይ ተክላ የኖረችው ግብጽ የምትዝተው ዛቻና፣ በቅርቡ ተቋቁሞ ታላቅ ታሪክ በማስመዝገቡ የተረጋገጠለት ሰማያዊ ፓርቲ ያዘጋጀው ሰላማዊ ሰልፍ አጀንዳዎቹ ናቸው።

በወጣት አመራሮች የተገነባውና በርካታ ሴት አባላት እንዳሉት የሚነገርለት ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በዋናነት የተገኘው ድል የፍርሃት ደመና መገፈፉ ነው። አቶ መለስ ባስተላለፉት ትዕዛዝ በ1997 ዓ.ም ዜጎች አልመው በሚተኩሱ የአጋዚና ታማኝ የህወሃት አባሎች ደረትና አናታቸው እየተወጋ እንዲገደሉ ከተደረገ በኋላ የተቃውሞ ሰልፍ የማይታሰብ ሆኖ ላላፉት ስምንት ዓመታት ቆይቶ ነበር።

ከዳር እስከዳር ድምጽ አልባ ሆኖ የተሸነፈው ኢህአዴግ በጠመንጃ ፣ በወቅቱ የነበሩት የቅንጅት አመራሮች ታሪካዊና ሊረሳ የማይችል ስህተት ተዳምረው የህዝቡን ቅስም የሰበረው የ1997 ዓ ም ምርጫ ጣጣውና ቆፈኑ እንዲሁ በቀላሉ የሚለቅ እንዳልሆነ በወቅቱ አስተያየት ተሰጥቶ ነበር።
“ሁለት አስርት ዓመታት ወደኋላ ተመልሰናል” ተብሎ የተዘጋውን በር የበረገደው ሰማያዊ ፓርቲ ከህዝብ ባገኘው ድጋፍ አዲስ አበባን የተቃውሞ ጎርፍ አጎረፈባት። ሰላማዊ ሰልፉ ሰላማዊና የተሳካ እንደነበር ኢህአዴግ ራሱ ተናገረ። ህዝብ ተቃውሞውን ገልጾ የሶስት ወር ጊዜ ከሰጠ በኋላ ወደ ቤቱ ተመለሰ።

አዲስ አበባ አንድ ለአምስት፣ የጎንዮሽ፣ የሽቅብ፣ የህቡዕ፣ የገሃድ፣ የዘር፤ የታማኞች፣ የበጣም ታማኞች፣ የልማት፣ የአነስተኛ ስራ ፈጠራ፣ የጾታ፣ የዘር፣ የእድሜ፣ የተፈጥሮ ሁኔታ፣ የጥቅም ወዘተ የፈጠረው አደረጃጀት አፈር ድሜ መብላቱ ያስጨነቀው ኢህአዴግ ሰልፉ ተበትኖ ሲያበቃ ላንቃውን አላቀቀ።

Monday, June 3, 2013

በህዝብ አቆጣጠር አሁን ጨዋታው ተጀመረ!


ወደ "ሻርኮቹ" ይቀጥል!! (ርዕሰአንቀጽ)

shark
June 3, 2013 08:34 am By  Leave a Comment
ሙስናው ላይ የተጀመረው ዘመቻ ሙስናን በስንጥር የሚያሰኝ ቢሆንም አቶ መለስ ያልደፈሩትን ሰፈር አቶ ሃይለማርያም ነክተውታልና በኢህአዴግ ታሪክ የሙስናን ሰፈር በማንኳኳት ግንባር ቀደሙ ሰው ያደርጋቸዋል። እኛም ጅምሩ መልካም ነው እንላለን። ግን ጥያቄም ማሳሰቢያም አለን። ለማንኛውም በህዝብ አቆጣጠር አሁን ጨዋታው የተጀመረ ይመስለናል።

በሙስና የተጠረጠሩ ነጋዴዎች፣ ደላሎች፣ አቀባባይ የተባሉና የመንግስት ሃላፊዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ከተሰማ ጀምሮ ህዝብ በስፋት እየተቸ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ የተደላደለውን ሙስና ህዝብ ጠንቅቆ ከነባለቤቶቹ ያውቃል። ይረዳል። ያሸታል። ባለፈ ባገደመ ቁጥር ለድህነቱ ማስታገሻ ያላምጣቸዋል።

ሙስና ሲባል ሙስና ነው። ወንጀል ሲባል ወንጀል ነው። ህግ መተላለፍ ያስጠይቃል። አሁን እንደሚታየው ግን የጸረ ሙስናው ዘመቻ ሰፈር የለየ ይመስላል። ዋናዎቹ “ሻርኮች” አልተነኩም። ዋናዎቹ “የማበስበሻው ባህር” ፊታውራሪዎች አሁንም እያገሱ ነው። እነዚህ አገር ወዳድ የሚመስሉ  የሙስና መፈልፈያ ማሽን አምራቾች ለምን ዝም ተባሉ? የህዝብ ጥያቄ ነው? የምስኪን ዜጎች ጥያቄ ነው። በተለይም “ጠቁሙኝ እርምጃ እወስዳለሁ” በማለት ለተናገሩት አዲሱ መሪ፡፡

ምርመራው ወደ አቃብያነህጉ ተዛወረ!


የሙስናው “ሻርኮች” በዒላማ ውስጥ?

berhane
June 3, 2013 08:40 am By  Leave a Comment
* “አዲስ ነገር የለም” ጸረ ሙስና ኮሚሽን
በተለያዩ ከፍተኛ ወንጀሎች በተጠረጠሩ ሰዎች ላይ የተከፈቱ ክሶችን በማፈንና በመመሪያ ፍትህ በማዛባትና በማቋረጥ ወንጀል የተጠረጠሩ አቃቤያነህግ ላይ ምርመራ መጀመሩ ከፍተኛ ድንጋጤ መፍጠሩ ተሰማ። በተለይም ከወንጀል ጋር ቁርኝት እንዳላቸው በህዝብ የሚታወቁ ክፍሎች ክፉኛ መደናገጣቸው ተሰምቷል።

በሙስና የተጠረጠሩት የጉምሩክ ባለስልጣናት፣ ተባባሪ ነጋዴዎችና ደላሎች መታሰራቸውን ተከትሎ ከተፈጠረው ስሜት በላይ ከፍተኛ መደናገጥ የፈጠረው ዜና አዲስ አድማስ ጋዜጣ ቅዳሜ እለት ለንባብ ያበቃው ዜና ነው።

በቅርቡ ከሃላፊነታቸው የተነሱት የፍትህ ሚኒስትር አቶ ብርሀነ ሃይሉና ከአስር በላይ አቃብያነህግ በተለያዩ ጉዳዮች የተመሰረቱ ክሶች እንዲቋረጡ አድርገዋል በሚል ተጠርጥረው መመርመራቸው በትክክል ከተሰራበት ዋንኛ የሚባሉትን የሙስና ወንጀል “ሻርኮች” በቁጥጥር ስር ለማዋል እንደሚያስችል ከፖሊስ ያገኘነው ጥቆማ ያመለክታል።

“የበርካታ ጉዳዮች ክስ እንዲቋረጥ መደረጉን እናውቃለን” በማለት ለጎልጉል ጥቆማ የሰጡት የፖሊስ አባላት “ይህ ጉዳይ ከተነሳና በትክክል ከተሰራበት የማይጎተት የለም” በማለት በትዕዛዝና በመመሪያ የተቋረጡ የምርመራና የክስ ፋይሎች በርካታ መሆናቸውን ያስረዳሉ።