(ገብረመድህን አርዓያ)
April 29, 2013 04:04 am By Leave a
Comment
ስብሃት ነጋ ባለፈው ሳምንት አዲስ አበባ በሚታተመው የአዲስ አድማስ
ጋዜጣ ላይ የሰጠውን ቃለ መጠይቅ አነበብኩት:: ስብሃት ነጋ “ኢህዴግን የመሰለ ፓርቲ በአፍሪካ የለም” እና ሌላም ብዙ ፣ ብዙ
ይላል:: ይዘብታል ፣ ይፎክራል ፣ ይሸመጥጣል ፣ ያቀረሻል ፣በህዝብ ሞራል ላይም ያላግጣል:: ብዙም አልደነቀኝም:: ስብሃትም
ሆኑ የዚህ ፋሺስታዊ ስርዓት አንቀሳቃሾች በብዙሃን ደም ላለፉት አርባ አመታት ታጥበዋል ፣ ታሪክ አውድመዋል ፣ እጅግ ከፍተኛ
ዘረፋ ፈጽመዋል ፣ አገር ቆርሰው ሸጠዋል:: በጣም ከፍተኛ ወንጀል የሰሩ ሰዎች እንደመሆናቸው በአገሪቷ የፖለቲካ ለውጥ
ከመቼውም ጊዜ በላይ መቀጣጠሉ እንቅልፍ እንደነሳቸው እያየን ነው:: አዎን ስብሃት ገና ፣ ገና ከዚህም በላይ ብዙ ይናገራል ፤
ቁጣው እያየለ በሄደ ቁጥር ብዙ ወንጀሎችም ይሰራል::
ዛሬ ወያኔ ኢህአዴግ ከመቼውም ጊዜ በበዛ ፍጥነት እና ማን አለብኝነት
ኢትዮጵያዊ የሆኑ መሰረቶችን የመናዱን ስራ አጠናክሮ እየሰራ ለመሆኑ በየእለቱ የምንሰማቸው ዜናዎች እና ዘገባዎች ያሳያሉ::
እንደ እኔ ፣ እንደ እኔ የወያኔ የጥፋት ስራ ሳይሆን የጨመረው ይልቁንስ ረጅም እድሜ ለኢሳት ይስጠውና የዜና ዘገባ ብዛት እና
አይነቱ መጨመሩ ይመስለኛል:: ወያኔ ሲፈጠር ጀምሮ ኢትዮጵያዊ መሰረት ያላቸውን እሴቶችን የማጥቃት ስራን እንደ መጨረሻ
ግብ(strategic goal) አስቀምጦ የሚንቀሳቀስ ድርጅት መሆኑን ቀድመን ላወቅን እና ለተረዳን ሰዎች ግን እምብዛም አዲስ
ነገር አይደለም:: ዛሬ ላይ ከኢትዮጵያ ከሚወጡ ዜናዎች በብዛት የምንሰማው ብዙዎች ሲያለቅሱ እና ጥቂት ዘረኞች ደግሞ ያለ
ይሉኝታ ሲዘርፉ ፣ ሰዎችን አስረው ሲያሰቃዩ፣ እና ኢትዮጵያውያንን ዘር ቆጥረው ከቀያቸው ሲያፈናቅሉ ሆኗል::
የኢትዮጵያውያን ገበሬዎች ዋይታ በቤኒሻንጉል እና ጉራፈርዳ፣ የባህታውያን ለቅሶ
በዋልድባ ፣ የእስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን የፍትህ ጥያቄ በመላ ሃገሪቱ ፣ ሌላም ፣ ሌላም:: ወያኔ ኢህአዴግ በአገር
እና በወገን ላይ የሚያደርሰው ጥቃት በግብ ደረጃ የተያዘ በመሆኑ ይብሱን ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚችል በእርግጠኝነት መናገር
ይቻላል:: ዛሬ ላይ ከዳር ቆመው የሚመለከቱ ሰዎችም ሆነ በስርዓቱ ውስጥ ያሉ ካድሬዎች እና አገልጋዮች ይህንን ሃቅ በደንብ ልብ
ብለው ሊመለከቱት ይገባል:: የጥቃት ዱላው በአንድ ወይም በሌላ በኩል አይደርስ የሚመስልበት ቦታ ሁላ ይደርሳል::